- 26Jan
[UR2] ከመድረክ በስተጀርባ፥ እንዴት እንደ ሆነ እነሆ። የፍራንሲስ ቁጣ በካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ላይ። Background: this is how things went. The despot’s fury against the Catholic pope
“ከልባችን ጥልቀት” የሚል መጽሐፍ፣ በትክክል በቤኔዲክት ፲፮ እና በካርዲናል ሣራህ የተጻፈ ነው፣ ምክንያቱም መጽሐፉን ለማጀጋጀት ሁለቱ የተፃፃፉት ደብዳቤዎች ያለምንም ጥርጣሬ ማስረጃ ናቸው። ከመጀመሪያ ጀምሮ ሁሉም ነገር በጋራ ስምምነት የታቀደ ነበረ። የካህናትን ምንኩስና (ትዳርን መያዝ የሚከለክለው ተውፊት) የሚገልጽ ጽሁፍ አስቀድሞ ከታወቀ በኋላ፣ በፍራንሲስ ንዴት ምክንያት በቫቲካን ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ብጥብጥ ተጀመረ። ምክንያቱም የቤኔዲክት ፲፮ ከፍተኛ ቃል፣ ፍራንሲስ በቀጣይ ድህረ-ሲኖዶስ ማሳሰቢያ ውስጥ የካህናትን ምንኩስና እንዳያፈርሱ ይከለክላል። ስለዚህ ፍራንሲስ የቤኔዲክት ፲፮ ፀሐፊን ጠርተው፣ የቤኔዲክት ፲፮ ስም ከዚያ መጽሐፍ ሽፋን እንዲሰረዝ በንዴት አዘዙት። ፍራንሲስ ሙሉ በሙሉ ቤኔዲክት እንዲክዱ ጠይቀው ነበረ። በዚህ ምክንያት በማለዳ የተነበበ ዜና “ቤኔዲክት ከካርዲናል ሣራህ ጋር ምንም መጽሐፍ አልፃፉም ወይም ሽፋኑን አልፈቀዱም (ማለትም ምንም አልፈረሙም)” በማለት አስታወቀ። ይህ ግን እውነት ስላልነበረ፣ ቤኔዲክት ፲፮ “ካርዲናል ሣራህ በመጽሐፉ ሽፋን ላይ ያለኔ ፈቃድ ስሜን…
24Jan[K2] Boeing 737 Max “በሰርከስ ክበብ ታቅዶ፣ ተራ በተራ በጦጣዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ የተዘጋጀ ነው” Boeing 737 Max “designed by clowns and supervised by monkeys”
Boeing 737 Max ላይ ስለደረሱ አደጋዎች ምርመራ፣ የኩባንያው አስተዳደር ቸልተኝነትንና ስግብግብነትን የሚገልጹ አስደንጋጭ ዝርዝሮች ብቅ እያሉ ነው። RT እንደዘገበው፣ የኩባንያው አንድ ባለሙያ አውሮፕላኑ “በሰርከስ ክበብ (circus clown) ታቅዶ፣ ተራ በተራ በጦጣዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ የተዘጋጀ ነው” በማለት ገልፆ ነበር። ሌላ ባለሙያም “ባለፈው ዓመት ስለደበቅኩት ነገር እስካሁን ድረስ በእግዚአብሔር ዘንድ ይቅርታን አላገኘሁም” ብሏል። ሌሎች ችግሮች ደግሞ ከ“በረራ አስመሳይ” (flight simulator) ብቃት ጋር የተገናኙ ናቸው፤ አንድ ሠራተኛ ሌላውን፥ “በ flight simulator ብቻ በሰለጠነውን የአውሮፕላን አብራሪ ታምናለህን? ሚስትህንና ልጆችህን ለርሱ ታሰረክባለህን?” በማለት ጽፎአል። መልሱ “አይ” የሚል ነው። የሚያሳስበው ነገር ቢኖርም፣ እነዚህን ወሬዎች በጥልቀት ከመመርመር ይልቅ እየተወገዱ መሆናቸውን ነው። የአሜሪካ ፌዴራል በረራ ድርጅት (FAA America Federal Aviation Agency) እስካሁን ድረስ flight simulator ፍጹም በቂ እንደሆነ ከመግለጽ አያርፍም። የ 737 Max ትንተና የበራሪዎችን ህይወት አደጋ…
22Jan[WW1] ምንም የማያጣ (ቅዱስ ባስልዮስና ግሮጎርዮስ) Who has nothing to lose (Saint Basil and Gregory Nazianzus)
ቅዱስ ባስልዮስና ቅዱሰ ግሮጎርዮስ “ክርስቶስ አምላክ አይደለም” በሚል በአርዮስ መናፍቅነት ጊዜ በሰሜናዊ ቱርክ ቀጰዶቅያ በሚባል ክልል ውስጥ ጳጳሳት ነበሩ። ስለ አርዮስ የሚገልፅ የኒቂያ ጉባኤ ግልጽ ማረጋገጫ ቢኖርም፣ መናፍቃን ተስፋ አልቆረጡም ነበረ። ባስልዮስና ግሮጎርዮስ መናፍቅነትን ለማጥፋት ባከናወኑት ትግል ውስጥ ለእውነት በመቆም የማይሸነፉ ሀይሎች ነበሩ። ራሱ የአርዮስ ተከታይ የነበረ ንጉሥ ዩልያኖስ ለመናፍቃን ቅዱስ ቁርባን እንዲፈቀድላቸው ጳጳሳትን ለማስገደድ በሞከረ ጊዜ፣ ባስልዮስና ግሮጎርዮስ ለመታዘዝ አልቻሉም። አንድ ቀን በባስልዮስና በክልሉ አስተዳዳሪ መካከል የተከሰተ ክርክር፣ በአሁኑ ጊዜ ያልተለመደ የአንድ ጳጳስ ጥንካሬና ምሳሌነት ያሳያል። የክልሉ አስተዳዳሪ፣ የባስልዮስ ተቃውሞ ሲያጋጥመው፥ “መላው ዓለም የሚሰግድለትን የንጉሠ ነገሥቱን ፈቃድ ለመቃወም እብዳችኋልን? የንጉሠ ነገሥቱን ቁጣ፣ ስደት ወይም ሞት አትፈሩምን?” ሲል፣ ባስልዮስ ረጋ ብሎ “ምንም ንብረት የሌለው ንብረትን ማጣት አያስፈራራውም፤ ምድር ሁሉ ቤቴ ስለሆነች ልታሳድዱኝ አትችሉም፤ ሞት እንኳን ቢሆን ለእኔ መስጠት ከምትችሉት ታላቅ…
0 comments Read more21Jan[LR1] በውጪ አቆጣጠር 2019 የሞት ዋና መንስኤ? ልጅ ማስወረድ The world’s leading cause of death in 2019? Abortion.
ምንም እንኳን ማወቅ በጣም ተገቢ ቢሆንም፣ በመደበኛ ሚዲያዎች ችላ የሚባሉ ዜናዎች አሉ። በምድር ላይ እጅግ ዘመናዊ የሆነ Worldometer የሚባል የሒሳብ ማሽን ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ 58.6 ሚሊዮን ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጦአል። ታድያ አዲስ ነገር የት አለ? በእውነቱ ሁለት ዜናዎች አሉ፣ የተደራረቡም ናቸው። የመጀመሪያው፥ በ2019 ከሞቱት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ የሞቱት በተፈጥሮ ምክንያት ሳይሆን በሰው ፍቃድ ምክንያት ነው። አለምን ያደናቀፉት ጦርነቶች ከታሰቡ፣ ግድ ነው ትሉ ይሆናል!!! ግን አይደለም፣ ስህተት ነው! እንዲያውም፣ አሳዛኝና የማይነበበው ሁለተኛው ዜና እንሆ፥ በዓለም ላይ በሰው ፍቃድ ከሞቱት ሰዎች፣ አብዛኞቹ የሞቱት በሰው በተነሳ ግጭትና ጦርነት ሳይሆን በፍቃደኝነት ፅንስን በማስወረድ ነው። ባለፈው ዓመት 42.4 ሚሊዮን የሰው ልጆች በውርጃ ምክንያት ተገድለዋል። ግልጽ ለማድረግ፣ 42 ሚሊዮን ሰለባዎች ማለት፣ በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ጊዜ አውሮፓ በጥፋት፣ ቦምብና በማጎሪያ ካምፖች በተናወጠች ጊዜ ከነበሩት ሲቪልና ወታደራዊ ሰለባዎች…
18Janየጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት (Baptism of the Lord)
ይህን የዮርዳኖስ ትዕይንት ከጎልጎታ ጋር ማነፃፀር እንችላለን። እዚህ ላይ ኢየሱስ በውሃ ውስጥ ሲጠመቅ፣ እዚያ በሞት ይጠመቃል፤ እዚህ ላይ የሰማይ መጋረጃ ሲቀደድ፣ እዚያ የቤተመቅደስ መጋረጃ ይቀደዳል፤ እዚህ ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን ሲቀበል፣ እዚያ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣል፤ እዚህ በአባቱ ሲጠራ፥ እዚያ አባቱን ይጠራል፤ እዚህ በአባቱ ልጅ ተብሎ ይጠራል፣ እዚያ ልጅ ተብሎ ይሚጠራ በሮማዊ ወታደር ነው (27፥51-54)። መላው የኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት፣ በሥጋው በመገለጹ በዚህ ሁለት ትዕይንቶች መካከል ይገኛል፣ እንዲሁም የእነዚህ ሁለት ትዕይንቶች ማብራሪያ ነው። የጥምቀት ዘር አድጎ የመስቀል ዛፍ ይሆናል። ቁ13 “በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ”፥ … እርሱ ለምን መጣ? ቅዱሱ ምን ኃጢአት አለው? ምንም! በዚህ ምክንያት የሁሉን ሰው ኃጢአት ይሸከማል። የሌሎችን ክፋት የሚሸከመው ክፋትን ሳያደርግ የሚያፈቅር ነው። የጥምቀቱ አላማ ከልደቱ ጋር አንድ ዓይነት ነበር፣ ማለትም ከኃጢተኛ ሰው ዘር…
10Jan[UR1] ኢየሱስ ባለተወለደ ቢሆንስ? What if Jesus was never born?
የስልጣኔአችን ሥሮች በእሱ ላይ የተመሰረቱ ናቸው እና በአጭሩ ያለ እሱ አይሆኑም ነበር። አንዳንድ ምሳሌዎች እነሆ፥ ሆስፒታል የሆስፒታሎችና የህሙማን እንክብካቤ እድገት ድሆችንና የህሙማንን ከክርስቶስ ስቃይ ማነጻጸር ከእምነት የመነጨ ነው፣ በምድራዊ ሕይወቱ ኢየሱስ የሥጋና የነፍስ ፈዋሽ ሆኖ ራሱ ሕመምተኛ ነበረ፤ የመካከለኛው ዘመን የሥነ-መለኮት ምሁራን እንዳሉት ኢየሱስ ራሱ ሐኪምና ህመምተኛ ነበረ። በመካከለኛው ዘመን የተሠሩ ብዙ ሆስፒታሎች (አብዛኛውን በገዳማት አጠገብ) “Domus Dei” (የእግዚአብሔር ቤት) ተብለው ይጠሩ ነበር። በላቲን አሜሪካ፣ እስያና አፍሪካ የመጀመሪያ ሆስፒታሎች በካቶሊክና በፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያን ተመሰርተዋል፥ ዛሬም ቢሆን የአብያተ ክርስቲያናት ጤና አገልግሎት በብዙ አገሮች ውስጥ ትልቅ ሚና አላቸው። የሕፃናት ክብር ክርስትና በተስፋፋ ቁጥር፣ ፅንስ ማስወረድ እና ሕፃናትን ማስወገድ በሕብረተሰብ ተቀባይነት ባለማገኘታቸው ተገድበዋል። በሮማ ግዛት ውስጥ የማይፈለጉ ሕፃናትን በገበያ መሸጥ በስፋት ተለምዶ ቢሆን ኖሮ፣ ክርስቲያኖች ይህንን ድርጊት እንደ ግድያ ያወግዙት ነበር። ዮስቲኖስ ሰማዕት (100-165…
10Jan[K1] የሰሜን magnetic ዋልታ ወደ ሳይቤሪያ እየሸሸ ነው፥ ሳይንቲስቶች ስጋት ላይ ናቸው Magnetic North Pole fleeing to Siberia
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሳይንቲስቶች እንዲደናገጡ የሚያደርግ፣ በአርክቲክ ውስጥ በጣም ፈጣን እንቅስቃሴ እየተከሰተ ነው። የአለም አቀፉን ማህበረሰብ የሚያሰጋ በቋሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኝ የሰሜን magnetic ዋልታ በማይገመት ፍጥነትና ባልተጠበቀ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰ ነው። በቅርብ ጊዜ ልዩ ጥናት እንዳስታወቀ፣ የሰሜን magnetic ዋልታ ወደ ሳይቤሪያ እየሸሸ እንደሆነና በዓለም ዙሪያ ያሉት የባሕርና የአየር ትራንስፖርት ወታደራዊና ሲቪል ሲስቴሞች (በsmartphones ውስጥ ያሉ apps ጨምሮ) የመበላሸት ዕድላቸው ከፍተኛ እየሆነ ነው። እንዲያውም የባሕርና የምድር ኮምፓስ ሲስቴም ማስተካከያዎች ዋልታ በተቀመጠበት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የቅርብ ጊዜ ታሪክ እንደሚያሳየው፣ የሰሜን magnetic ዋልታ በካናዳ የአርክቲክ ውቅያኖስ ውስጥ ለብዙ ክፍለዘመናት በአነስተኛ እንቅስቃሴ ከተዘዋወረ በኋላ፣ ከ1990 ጀምሮ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተንቀሳቀሰ ነው (በዓመት 50 km)። በዚህ ዓመት magnetic ሰሜን ወደ ሳይቤሪያ በመሄድ ብዙ ባህር አቋርጦአል። ይህ ክፍተት በአንድ ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ተመራማሪዎችን World Magnetic…
07Janየኢትዮጵያ ገና (Ethiopian Christmas)
የክርስቶስ ልደት ስርዓተ አምልኮ ከሁለት ሺ አመት በፊት በቤትለሔም ከተማ የተወለደውን ጌታችን እንድናስታውስ ይጋብዘናል፤ እያስታወስን እንሰግድለታለን፥ የክርስቶስ መጀመርያ መፅኣት መታሰቢያ ነው። የ“መጀመርያ መፅኣት” ሲባል ሌላ መፅኣት እንዳለ መረዳት ይቻላል። እንዲያውም መጽሐፍእ ቅዱስ በሰው ታሪክ መጠረሻ ስለሚፈፀም ክርስቶስ የ”ዳግመኛ መምጣት” ይነግረናል። የመጀመሪያ ክርስቲያኖች፣ የጌያችንን ልደት በሚያከብሩበት ወቅት፣ ለዘላለም ከእርሱ ጋር ለመኖር ስለሚፈልጉ፣ የክርስቶስ መመለስ በፍጥነት እንዲፈፀም ይመኙ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን የቤተክርስቲያን ታሪክ ለብዙ ዘመናት ስለተስፋፋ፣ የዚህ መፅኣት ምኞት ቀንሷል። የኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት በጣም ሩቅ እየሆነ ያለ ይመስል ነበር። በእርግጥ እንዲህ ሆኖአል ምክንያቱም ቤተክርስቲያን፣ እንደ እናት… – ብዙ ቅዱሶን መውለድ ጊዜ እንዲኖራት፣ ከሁሉም ነገር በላይ እግዚአብሔር አምላክህን ውደድ የሚል ትዕዛዝ በታላቅ ገዳማዊ ተውፊት መተግበር ጊዜ እንዲኖራት – ባለንጀሮችህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ትዕዛዝ በታላቅ የበጎ አድራጎት ሥራ መተግበር ጊዜ እንዲኖራት…
04Janየሰብከተገና 4ኛ እሁድ (A ADV-4)
ወንገል፥ ማቴዎስ 1፥18-24 ቁ18 “ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ሁኔታ እንዲህ ነው፥ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ እያለች፣ ሳይገናኙ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች”፥ … “ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ሁኔታ”፥ … እግዚአብሔር በሰው ሊፈጠር አይችልም፥ ሰው ግን ሊቀበለው ይችላል። “ዮሴፍ” በዕብራይስ ማለት “እግዚአብሔር ይጨምር” ማለት ነው። እግዚአብሔር ትሑት የጽዮን ልጅ በሆነች በማርያም አማካይነት “በጨመረ” ልደት ስላመነ፣ ዮሴፍ ወደ እግዚአብሔር ልጅ ትውልድ ሐረግ ገብቶአል። ዮሴፍ ለራሱ ስለማይበቃ (Pascal) እራሱን ለታላቅ ምስጥር ክፍት የሚያደርግ ሰው ሁሉ አምሳል ነው። “እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ ሳለች”፥ … የሙሴ ሕግ ባዘዘው መሠረት፣ ከእጮኝነት ዝግጅት እስከ ሠርግ አንድ ዓመት ያልፍ ነበር። በመደበኛ ሠርግ ቀን ሙሽራይቱ ወደ ሙሽራ ቤት ትወሰድ ነበር። ሆኖም እጮኝነትና ጋብቻ በሕብረተሰብ ፊት ተመሳሳይ ናቸው። እንደ ዮሴፍ ሁሉ ሰው የክርስቶስን እናት እጮኛ አድርጎ እንዲኖር ይጋበዛል። ለእሷ “እሺ” ሲል ለእግዚአብሔር ስጦታ “እሺ”…