- 27Dec
የሰብከተገና 3ኛ እሁድ (A ADV-3)
ወንገል፥ ማቴዎስ 11፥2-11 ድምፅ ከቃሉ፣ ምኞት ከሚጠበቅ፣ ውሃ ከመንፈስ ቅዱስ፣ ጥያቄው ከመልሱ መለየት እንደማይቻል፣ የዮሐንስ ሕይወትም ከኢየሱስ ሕይወት መለየት አይቻልም። ቁ3 “ይመጣል የተባለው መሲሕ አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ?”፥ … “ዮሐንስ ይህንን የጠየቀው ባለማወቅ ሳይሆን፣ የማያውቁትን ለመምራትና እነሱን “እንሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያጠፋ የእግዚአብሔር በግ ይህ ነው” (ዮሐ 1፥29) ለማለት ነው” (JEROME) ዮሐንስ ደቀመዛሙርቱን ወደ ኢየሱስ ለመላክ ያሰበው፣ የመሲሑ ሕያው ቃል ራሱ እንዲያሳምናቸው ነው። ቁ4-6 “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት፤ ዕውሮች ያያሉ፣ አንካሶችም ቀጥ ብለው ይሄዳሉ፣ ለምጻሞችም ይነጻሉ፣ ደንቆሮችም ይሰማሉ፣ ሙታንም ይነሣሉ፣ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከሉት ሁሉ ብፁዓን ናቸው”፥ … እንደ ዮሐንስ እኛም “ይመጣል የተባለው መሲሕ አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” በማለት እንጠይቃለን። መልሱ ደግሞ በተግባር ይታያል፥ “ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት”። የሚታየውና የማያምኑትም ሁሉ ሳይቀሩ መገንዘብ…
13Decየሰብከተገና 1ኛ እሁድ (A ADV-1)
ወንገል፥ ማቴዎስ 24፥37-44 ቁ37-39 “የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያን ዘመን ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም ነበረ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል”፥ … በአጭር ቃላት ጌታችን ሰዎች በመንፈሳዊ ነገሮች ፊት ያላቸውን የግድየለሽነት ሁኔታ ያብራራል። መብላትና መጠጣት፣ ሚስት ወይም ባል ማግባት ይበልጥ አስፈላጊ እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠራል። በዚህ መንገድ ሲኖሩ ግን ሰዎች ከሁሉ የሚበልጥ ነገር የዘላለም ሕይወት መሆኑን ይረሳሉ። ሰዎች ጥሩ ቢሆንም መጥፎ በንግዳቸው ላይ እያሉ፣ ሁለተኛ የሰው ልጅ መምጣት ባልተጠበቀ ሰዓት ይፈጸማል። “የክርስቶስ ተቃዋሚ ሲመጣ፣ ራሳቸውን ማዳን ተስፋ መቁረጥን ከለመዱ አመጸኞች መካከል፣ ሕገወጥ ደስታን መፈጸም በጉጉት ይጠብቃሉ። ሆዳምነት መናፈቅና ስካር ይኖራል” (CHRYSOSTOM) “በመርከቧ ውስጥ ካመለጡት በስተቀር የምድር ፍጥረታት ሁሉ በጥፋት ውኃ…
08Decያለ ኃጢአት የተፀነሰች ማርያም (Immaculate Conception)
“ድንግል ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፣ የአገሬ ልጅ፣ የነፍሴ እህት፣ የደስታዬ ደስታ ደስ ይበልሽ። እኔ በሌሊት እንደሚጓዝ ነኝ፣ አንቺ ግን ከጠፈር በታች መጠለያ ነሽ። እኔ የተጠማ ጽዋ ነኝ፣ አንቺ ግን የእግዚአብሔር ክፍት ባህር ነሽ። ድንግል ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፣ የአገሬ ክንፍ፣ የነፍሴ አክሊል፣ የደስታዬ ደስታ ደስ ይበልሽ። የተባረክሽ ነሽ የሚሉሽ ሁሉ ደስ ይበላቸው” (Gertrud Von le Fort)
06Decየሦስታኛ አመት 34ኛ እሁድ (C OT-34) ክርስቶስ ንጉሥ
ወንገል፥ ሉቃስ 23፥35-43 የዚህ እሁድ ንባብ የመዳን መርህ የሆነውን የኢየሱስን ንግሥና ይገልጽልናል። ኢየሱስ ንጉሥ ከመስቀል አናት ሆኖ በምን ዓይነት ሁኔታ ሊያድነን እንድሚችል እንረዳለን። እሱ የሚያገለግል ንጉሥ ነው፤ ያለው ስልጣን እስከ ሞት መውደድ ብቻ ነው። በመስቀል ላይ፣ ኢየሱስ መንግሥቱን ይፈጽማል፣ እሱ ንጉስ ነው። ድሃ፣ የተራበ፣ የሚያለቅስ፣ የተጠላ፣ የተሰደደ፣ የተሰደበና ተቀባይነት ያላገኘ፣ ጠላቶቹን የሚወድና የሚባርካቸው፣ ክፉን በመሸከም ክፉን የሚያሸንፍ ነው። ቁ35 “ሕዝቡ ቆሞ ይመለከት ነበር”፥ … ስለስቅለቱ ማሰላሰል የአዲሱ ጥበብ መርህ ነው። በጎልጎታ ላይ የፊቱ መጋረጃ ስለሚነሳ ክርስቶስን ልንመለከተው እንችላለን፥ እርሱ ገደብ የሌለው ፍቅር ነው። ቁ36 “ሆምጣጤ ሰጡት”፥ … “በምግቤ ውስጥ ሐሞት ቀላቀሉ” (መዝሙር 69፥21)። ጥማቱ የሕይወትን ውሃ እንዲሰጠን ነው። እኛ ደግሞ በምላሹ ሞታችንን እንሰጠዋለን። ቁ38 “ይህ የአይሁድ ንጉሥ ነው”፥ … ጲላጦስ “ይህ የአይሁድ ንጉሥ ነው” በመጻፍ የፍርዱ ምክንያት መግለጽ ፍለጎ ነበረ (ማርቆስ…