- 29Apr
እውነትን ለመናገር ድፍርት ያላቸው ሰዎች አሉ
በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚፈፀሙት ገብረሰዶማዊ ድርጊቶች ቤኔዲክት ፲፮ ባለፈው ሳምንት ከጻፉ በኋላ፣ የፊላደልፊያ ጳጳስ አቡነ ቻፑት (Chaput) የሚከተለውን አስተያየት አቅርበዋል። (…) “በአጭር ጽሑፋቸው ውስጥ የዮሴፍ ራፂንገር (Joseph Ratzinger) እውቀትና ማስተዋል በምድረ በዳ ውስጥ እንደሚዘምብ ዝናብ ነው። ለምሳሌ፥ “አካላዊ ሕይወት ከማዳን በላይ የሆኑት መቼም እማንተዋቸው እሴቶች አሉ። ሰማዕትነት አለ። እግዚአብሔር አካላዊውን ሕይወት ከማትረፍ በላይ ነው። እግዚአብሔርን በመካድ የተገዛ ሕይወት፣ በመጨረሻ ውሸት ላይ የተመሠረተ ሕይወት፣ ሕይወት አይደለም… ከእግዚአብሔር ውጭ የሆነ ዓለም ትርጉም የለሽ ዓለም ብቻ ሊሆን ይችላል… ከዘመናችን ሁከት መመነጨት ያለበት መሠረታዊ ተግባር እንደገና ለእግዚአብሔር ብቻ መኖር እንድንጀምር ነው” “ዛሬ ቤተክርስቲያን እንደ አንድ ፖለቲካዊ ተቋም ተደርጋ ትቆጠራለች። ብዙ ጳጳሳት እንኳን ስለ ቤተክርስቲያን ያላቸው አመለካከት ፖለቲካዊ አመለካከት ነው” በመጨረሻም፥ “በራሳችን የተፈጠረ ቤተክርስቲያን እቅድ በእርግጥ ሕያው ከሆነው አምላክ እንድንርቅ ይሚፈልግ የዲያብሎስ ዕቅድ ያለው ነው። ይህ…
20Aprከዲያቢሎስ ጋር የፈፀምነው ስምምነት ዋጋ እያስከፈለን ነው
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት Pius ፲፩ “አንድ መንግስት በማሕፀን ውስጥ ያለውን ህፃን ለመከላክል ካልቻለ፣ እግዚአብሔር ከምድር ወደ ሰማይ የሚጮኸውን የንጹሐን ደም እንደሚበቀል አስታውሱ”። አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ፍርሃት ይገልጻሉ፥ ፅንስ ማስወገድ የተለመደ ነገር እንዲሆን ስለተደረገ፣ ማኅበረሰባችን ከባድ ቅጣት ይደርስበታል። ማኅበረሰባችን ቅጣት ይደርስበት ይሆን? እኔ የምመልሰው ይህ ነው፥ ዙሪያውን ተመልከቱ! ቀደም ብለው አለማችን የሚገባውን ቅጣት ተቀብሎአል፥ ዘርኝነት፣ የቤቶች መውደም፣ የቤተሰቦች ድህነት፣ ወንጀል፣ ባልና ሚስት መለያየት፣ ስራ አጥነት፣ የዕፅና የመጠት ሱስ። ወጣቶችም ስቃያቸው ለማሳየት ፀጉራቸው ቀይና ቢጫ ይቀባሉ። በነዚህ ችግሮችና ፀንስን በማስወረድ መካከል ምንም አይነት ግንኙነት ላይኖር ይችላል። የተቆጣም አምላክ እነዚህን ቅጣቶች በኛ ላይ እንዳደረሰ መጠቆም አልፈልግም። በእርግጥ የነዚህ ቅጣቶች ምክንያት ማኅበረሰባችን ራሱ ነው፥ ፅንስ ማስወረድን በመቀበሉ ከዲያቢሎስ ጋር ስምምነት ተፈራርሞአልና እነዚህ ችግሮች ሁሉም የስምምነቱ አካል ናቸው።
20Aprየቤኔዲክት መድሃኒት፥ ወደ እግዚአብሔር መመለስና ቅዱስ ቁርባንን መከላከል
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት ፲፮ በቅርብ ጊዜ ከጻፉት ማስታወሻዎች አጫጭር ትርጓሜን አቀርብላችኋለሁ። እዚህ ላይ የርሳቸው ፅሑፍ ሙሉ በሙሉ ማንበብ ትችላላችሁ (here)። ቤኔዲክት ፲፮ በተለያዩ የአሜሪካና የጀርመን ገዳማት ውስጥ የግብረሰዶማውያን ክለቦች የሚሰሩ እንደነበረና ቤት ውስጥ ተጽዕኖ ያደርጉ እንደነበረ ይገልፃሉ። “ምን መደረግ አለበት? ለዚህ መፍትሔ ሌላ ቤተክርስቲያን መፍጠር አለብን ወይ? በሰው ልጅ ታሪክ እንዲህ አይነት ሙከራ አስቀድሞ ተካሄዶ ነበረ፣ ግን ስኬታማ አልሆነም። ይልቁንስ መንገዱን ሊያሳየን የሚችል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማፍቀርና ለርሱ ብቻ መታዘዝ ነው…” “በዘመናችን ባለው የሥነምግባር ውድቀት ላይ ዋነኛው ተግባራችን ለእርሱ ብቻ በመኖር ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን የሕይወታችን መሰረት ለማድረግ እንደገና መማር ነው። እኛ ግን በተደጋጋሚ ጊዜ ፍሬ እንደሌለው ቃል አድርገነው እግዚአብሔርን ጥለን እንሄዳለን። ስልክርስቶስ ስናጠና ክርስቶስ ራሱ የአስተሳሰባችን፣ የቃላታችንና የድርጊቶቻችን ምንጭ ካልሆነ፣ በስተጀርባውን የምንተው ጥላ ይሆናል…” “ስለዚህ ምን አይነት እርምጃ…
13Aprየተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ አውጥተዋል፥ የሰው ዘር ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ ነው
ይህ አጀንዳ ዓለምን የሚያቅፍ አምባገነናዊ መንግሥት (New World Order) መጀመሪያው ይፋዊ አዋጅ ሊባል ይችላል። ይህ አዲስ አጀንዳ ሙሉ በሙሉ የሰው ዘር እንቅስቃሴዎችን ያካትታል። በመጀመሪያ ሲታይ ይህ አጀንዳ እያንዳንዱን ከባድ ችግር በአለምአቀፍ ደረጃ ላይ የሚታገል ይመስላል። እስከ ዛሬ ድረስ ድህነትን ለማስወገድ በይፋ የሞከረ ሰው እንዳልኖረ ያስመስላል። ይህ ደግሞ ሌላ ጥያቄ ያስነሳል፥ ተሳታፊ ላለመሆን ለሚወስኑት አገሮች ምን ይሆናል? ድህነትን ከሚያስወግደው አለምአቀፋዊ እቅድ ነጻ ይሆናሉ ወይ? በእነዚህ ዓለም አቀፋዊ ግቦች ላይ ለተመለከቱ ብዙዎቹ በጣም ጥሩ ይመስላሉ። ለመሆኑ ረሃብን ማቆም የማይፈልግስ ማን አለ? ዋናው ቁም ነገር ከቋንቋው በስተጀርባ ያለውን ማየትና ምን እየተባለ እንዳለ መረዳት ነው። በእውነት እየተባለ ያለው ደግሞ ዓለምን የሚቆጣጠሩ ሀይሎች የአንድ ዓለም መንግሥት ሕልማቸውን ወደ ቀጣዩ ደረጃ መውሰድ እንደሚፈልጉ ነው። የ2030 አጀንዳ ድብቅ ዓላማ አላማ 1፥ ድህነትን በሁሉም ቦታ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት…