-
22Nov
እናንተም ደግሞ መሄድ ትፈልጋላችሁ? (ዮሐ 6፥68)
1. አንዳንድ ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ሁለት የተለያዩ አማልክት አሉ ብለው በማወቅ ወይም ባለማወቅ ያምናሉ። ሁለተኛው አምላክ የመጀመሪያው አምላክ “ዝግመተ ለውጥ” ነው ብለው ያምናሉ። አንዱ ህጉን የሚያስገድድ ብርቱው ፈራጅ የሆነው የብሉይ ኪዳን አምላክ ሲሆን፣ አንዱ ደግሞ የአዲስ ኪዳን አምላክ ነው። ሁለቱም ከምህረትና ይቅር ባይነት አንፃር እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ናቸው። እስከዚህ ያብራራሁት “ግኖሲስ” ተብሎ የሚጠራ በክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው መናፍቅ ነው (በእንግልዝኛ Gnosis ወይም Gnosticism)። የመጀመርያ ክርስቲያን ግኖሲስ ኢየሱስን እንደ “አዲስ ሰይጣን” አድርጎ ያስበው ነበር። ምንም እንኳ የማይረዳ ቢመስልም፣ በግኖሲስ ትምህርት መሰረት፣ በክፉ ፈጣሪ (የብሉይ ኪዳን አምላክ) ለተፈጠረ ለአዳም ዕውቀትና ነፃነት በማሳየት (“ግኖሲስ” በግሪክ ቋንቋ “እውቀት” መለት ነው)፣ ሰይጣን የብርሃን ምንጭ ነው ይለዋል። እንደ ግኖሲስ አስተሳሰብ፣ ዓለም በክፉ አምላክ የተፈጠረች የሰው ዘር የታሰረባት እስር ቤት ናት ብሎ ያምናል። ስለዚህ የፈጣሪ አምላክ ሕግ የሰው…
-
20Apr
የቤኔዲክት መድሃኒት፥ ወደ እግዚአብሔር መመለስና ቅዱስ ቁርባንን መከላከል
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት ፲፮ በቅርብ ጊዜ ከጻፉት ማስታወሻዎች አጫጭር ትርጓሜን አቀርብላችኋለሁ። እዚህ ላይ የርሳቸው ፅሑፍ ሙሉ በሙሉ ማንበብ ትችላላችሁ (here)። ቤኔዲክት ፲፮ በተለያዩ የአሜሪካና የጀርመን ገዳማት ውስጥ የግብረሰዶማውያን ክለቦች የሚሰሩ እንደነበረና ቤት ውስጥ ተጽዕኖ ያደርጉ እንደነበረ ይገልፃሉ። “ምን መደረግ አለበት? ለዚህ መፍትሔ ሌላ ቤተክርስቲያን መፍጠር አለብን ወይ? በሰው ልጅ ታሪክ እንዲህ አይነት ሙከራ አስቀድሞ ተካሄዶ ነበረ፣ ግን ስኬታማ አልሆነም። ይልቁንስ መንገዱን ሊያሳየን የሚችል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማፍቀርና ለርሱ ብቻ መታዘዝ ነው…” “በዘመናችን ባለው የሥነምግባር ውድቀት ላይ ዋነኛው ተግባራችን ለእርሱ ብቻ በመኖር ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን የሕይወታችን መሰረት ለማድረግ እንደገና መማር ነው። እኛ ግን በተደጋጋሚ ጊዜ ፍሬ እንደሌለው ቃል አድርገነው እግዚአብሔርን ጥለን እንሄዳለን። ስልክርስቶስ ስናጠና ክርስቶስ ራሱ የአስተሳሰባችን፣ የቃላታችንና የድርጊቶቻችን ምንጭ ካልሆነ፣ በስተጀርባውን የምንተው ጥላ ይሆናል…” “ስለዚህ ምን አይነት እርምጃ…