- 20Mar
አድሜ ለአፍሪካ ተወካዮች፣ የተባበሩት መንግስታት ኮሚሽን ፅንስ ማስወረድና ሰዶማዊነትን የሚደግፈውን ውሳኔ ሊተው ነው
ሰዶማዊነትን የሚደግፈውን ውሳኔ ይጠበቅ ነበረ። ነገር ግን ባለፈው የካቲት መጨረሻ በተደመደመው የተባበሩት መንግስታት ማህበራዊ እድገት ኮሚሽን ፅንስ ስለ ማስወረድና ሰዶማዊነትን በተመለከተው ጉዳይ ምንም ፍንጭ እንኳን አልሰጠም። እንዲሆም የኮሚሽኑ የመጨረሻው ስምምነት “የወሲብና የስነ ተዋልዶ ጤና” የሚሉትን ቃላት ትቶ የቤተሰብን ብልጽግና የሚደግፉ መመሪያዎችን አካቶአል። በምላሽ የውርጃ ደጋፊ የሆነኑት የሜክሲኮ ተወካይ “ከመካከለኛ ዘመን ለመውጣት ያግዱናል” በማለት የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ተወካዮችን ወቅሰዋል። እንደሚታወቀው በተባበሩት መንግስታት አነጋገር “የወሲብና የስነ ተዋልዶ ጤና” (sexual and reproductive health) ማለት ፅንስ ማስወገድን ማመቻቸት እንደ ማለት ነው። የአፍሪካ አገራት በመወከል የጂቡቲ ተወካይ “ቤተሰብ በማህበራዊ እድገት ውስጥ መሠረታዊ ሚና ይጫወታል፤ ቤተሰቦችን የሚደግፉት ፖሊሲዎች ማህበራዊ እኩልነትን ለማሳደግና ድህነትን ለማስወገድ ይረዳሉ” በማለት የኮሚሽን ስምምነት መልካም ገጽታዎችን ጎላ አድርገው ገልጸዋል። በቅርብ ዓመታት ውስጥም የተባበሩት መንግስታት ማህበራዊ እድገት ኮሚሽን “ብዙ አይነት ቤተሰብ አለ” በሚል አስተያየት…