- 24Feb
“ህብስትና ወይን ጠጅ ከተቀደሱ በኋላ፣ እግዚአብሔር በመንግሥተሰማይ እንዳለ እዚህም ነው። ሰው ይህን ቢረዳ ኖሮ በፍቅር ይሞት ነበር” (Benedict XVI)
23Febዘወትር በስውር እንደተመኙት መልስ
“ሰዎች በቃላት ሊገለጽ በማይችል ብቸኝነት ውስጥ የሚኖሩ መሆናቸውን ይገነዘቡና የድህነታቸውን ፍርሃት ከተሰማቸው በኋላ፣ ልክ እንደ አዲስ ነገር ሆኖ ለክርስቶስ ታማኝ የሆነውን ያማኞች ታናሽ መንጋ ያገኛሉ፥ እርሱንም ዘወትር በልባቸው እንደተመኙት የውሃ ምንጭ የራሳቸውን ተስፋ አድርገው ያገኙታል” (Benedict XVI)
23Febየመንፈስ ኃይል
“ዛሬ ራስን መቻል ይባላል፣ በጥንት ዘመን የመንፈስ ኃይል ተብሎ ይጠራ ነበር፣ ፕላቶ መኖሪያዋ በሰው ልብ ውስጥ እንደነበረ ብሎ ፅፎአል፣ ልብ የስሜት ተምሳሌት ነው። ስሜት ግን ድክመት አይደለም፣ የነፍስ መጽናናትን የማያገኝ ሐዘንም አይደለም። ስሜት ድፍረት ነው። ስሜት ሁሉን ጥቅሞችና መሰናክሎች ካመዛዘንን በኋላ በእያንዳንዳችን ውሳኔ መነሻ ላይ የምናውቀው ድፍረት ነው። በጥቅም ወይም በድክመት ምክንያት የራሳችን ያልሆነ ውሳኔ ብናደርግ ግን ወዮልን! በራሳችን ሕይወት የውጭ ዜጋ ሆነን ከቀረን ወዮልን! ቤታችን! የመንፈስ ኃይል በራሳችን ቤት ውስጥ የውጭ ዜጋ ከመሆን ይጠብቀናል፣ ከራሳችን ጋር እና የቤታችን ነዋሪዎች መሆናችን እንዲሰማን ያደርጋል። ከራሳችን ጋር ተመሳሳይ የሚያደርገን የአእምሮ ጤንነት እዚህ አለ” (Romano Guardini 1885-1968)