- 17Apr
[WW3] የመስቀል ርዕስ (Titulus Crucis)
“ጲላጦስ የናዝሬቱ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ የሚል ጽሑፍ ጽፎ በመስቀሉ ራስጌ ላይ አኖረው። ኢየሱስ የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ስለነበረ፣ ከአይሁድ ብዙዎቹ ጽሑፉን አነበቡት፤ ጽሑፉም የተጻፈው በዕብራይስጥ በላቲንና በግሪክ ቋንቋ ነበረ” (ዮሐንስ 19፥19-20) ⇒ ወንጌላዊው ዮሐንስ በመስቀሉ ላይ የተጻፈው ጽሑፍ በዕብራይስጥ፣ በላቲንና በግሪክ ቋንቋ መሆኑን ሊነግረን ለምን ፈለገ? ለዚህ መልስ ለመስጠት፣ በመጀመሪያ በብሉይ ኪዳን ጊዜ በእግዚአብሔር ስም ዙሪያ የነበረ የቅድስናን ግንዛቤ መመልከት ያስፈልጋል። በኦሪት ዘጸአት መጽሐፍ ውስጥ እንደሚነበብ፣ በሲና ተራራ ላይ ራሱን በገለጸበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ህዝቡን ከግብጻዊያን ቀንበር ነፃ እንዲያወጣ ሙሴን አዘዘ። በዚህ ታላቅ ትእዛዝ ፊት፣ ሙሴ ብዙ ጥያቄ ያቀርባል፥ ሕዝቡን እንዴት ያሳምናል? የእግዚአብሔር ስም ማን ነው? “እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፥ ‘እኔ ያለሁና የምኖር ነኝ’፤ ስለዚህም ‘እኔ ነኝ ወደ እናንተ ልኮኛል’ በላቸው” (አሪት ዘጸአት 3፥14)። ትምህርተ ክርስቶስ እንደሚያስተምረው፣ ይህ ስም “እግዚአብሔር የሕላዊና…
16Aprፋሲካ፥ የነገሮችን ይዘት ለመገምገም እንማር (EASTER: seeing the essence of things)
የእግዚአብሔር ህግ ፍጹምነት በአሮጌው እና በአዲሱ መካከል ባለው አስደናቂ አንድነት ይገለጻል። በዘላለማዊ አምላክ ጥበበኛ እጅ (ማለትም በመንፈስ ቅዱስ) የሚደረግ ሁሉ በዋጋ የማይተመን ስፌት ይመስላል። ✓ ፋሲካ የሚለ ቃል ከዕብራይስጥ ‘ፐሳህ’ ከሚል ቃል የመጣ ነው። ትርጉሙም ‘ሽግግር’ ማለት ነው። ስለሆነም፥ ሁለቱም ክስተቶች በሽግግር ተለይተው ይታወቃሉ፥ 1. የአይሁድ ፋሲካ፣ ከአራት መቶ ዓመታት ስደት በኋላ ከግብጽ ባርነት ወደ ስጋዊ ነፃነት በሙሴ አማካይነት ተፈጽሞአል። 2. የክርስትና ፋሲካ፣ ከአዳም ኃጢአት በኋላ ከሰይጣን ባርነት ወደ መንፈሳዊ ነፃነት በክርስቶስ መሥዋዕት አማካይነት ተፈጽሞአል። ክርስቶስ የሰማይን በር ስለከፈተልን፥ እንደየትጋታችን ቢሆንም ወደ መጀመርያው ገነት መመለስ እንችላለን። ✓ አሁን የሁለቱን ተመሳሳይነት እንመልከት። የአይሁድ ሕግ በአይሁድ ፋሲካ ወይም በቂጣ በዓል ቀን ለመስዋእት ከቀረበ በግ ጋር፣ እርሾ ያልገባበት ቂጣ እና መራራ እፅዋት እንዲበላ ያዝዛል፥ 1. በግ የንጽህናና የየዋህነት ምልክት ነው፣ በዚህ ምክንያት በግ…
03Aprየአብይ ጾም 5ኛ እሁድ (A LENT-5)
ወንገል፥ ዮሐንስ 11፥1-45 ቁ3 “ጌታ ሆይ፥ እነሆ ወዳጅህ ታሞአል”፥ … “ብዙዎች የእግዚአብሔር ወዳጆች በመጥፎ ነገር ሲሰቃዩ ማየት ያናድዳቸዋል። ለምሳሌ፣ የታመሙ ወይም ድሃ የሆኑ ወይም ሌሎች አሳዛኝ ሁኔታዎችን የተቋቋሙ አሉ። በዚህ ምክንያት የሚሰናከሉት የእግዚአብሔር ልዩ ወዳጅ እንደነዚህ ያሉትን ነገሮች ለመቋቋም የእርሱ ድርሻ እንደሆነ አያውቁም። የአልዓዛርን ታሪክ ማየት እንችላለን፥ እርሱ የክርስቶስ ወዳጅ ነበረ ግን ታሞአል” (JOHN CHRYSOSTOM 344-407) “እዚህ ላይ ለወዳጅ የሚያስፈልገው አንድ ትእዛዝ ብቻ ነው፥ ነገር ግን ሴቶቹ ኢየሱስን ’ና’ ብለው አላዘዙም። ደግሞም ‘እዚያ እዘዝ እና እዚህ ይፈጸማል’ ለማለት አልደፈሩም። እነዚህ ሴቶች የተናገሩት ‘ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሞአል’ የሚል ቃል ብቻ ነው፤ ማለትም፥ አንተ ማወቅህ በቂ ነው፣ ምክንያቱም ሰውን ወደህ ለብቻ አትተውም” (AUGUSTINE 354-430) ቁ6 “እንደ ታመመም በሰማ ጊዜ ያን ጊዜ በነበረበት ስፍራ ሁለት ቀን ዋለ”፥ … “ለሞት ሙሉ በሙሉ ቦታ እንዴት እንደሰጠ ትመለከታለህ።…