- 30Nov
የሦስታኛ አመት 33ኛ እሁድ (C OT-33)
ወንገል፥ ሉቃስ 21፥5-19 ቁ5 “አንዳንድ ሰዎች “ይህ ቤተመቅደስ እንዴት ውብ ነው፣ በከበሩ ድንጋዮችና ለእግዚአብሔር በቀረቡ ስጦታዎች አጊጦአል” እያሉ ይነጋገሩ ነበር”፥ … ሄሮድስ በአስር ዓመታት ውስጥ በ 100,000 ሠራተኞችና ቅድስተ ቅዱሳንን ለመስራት እንደ ጠራቢ በሰለጠኑት 1,000 ካህናት ተጠቅሞ የገነባው እጅግ አስደናቂ ቤተመቅደስ ነው። በ 20 ዓ.አ የተጀመረው ሥራ ለረጅም ጊዜ ቀጥሎአል፥ ከመፍረሱ ስድስት ዓመት በፊት በ 64 ዓ.ም ውስጥ ያበቃል። “በከበሩ ድንጋዮች”፥ በነጭ የኖራ ውብ ድንጋይ ከተሠራ ከጥንታዊው ቤተመቅደስ ምንም አያንስም፥ የክርስቶስ አካል በመስቀል ላይ እንደሚጠፋ ቤተመቅደስም ይፈርሳል። የአዲሱ ቤተመቅደስ የማዕዘን ድንጋይ የተሰቀለ ክርስቶስ ነው። ወደ ጌታችን ቀርበው እንደ ህያው ድንጋይ ደቀመዛሙርቱ ለአዲሱ መንፈሳዊ ቤተመቅደስ ግንባታ ተቀጥረዋል (1ኛ ጴጥሮስ 2፥4)። ቁ8 ደቀመዛምርቱ ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋ በሰሙ ጊዜ ይህንን ክስተት የሚያውጅ ምልክት የትኛው እንደሆነ ይጠይቁታል። ኢየሱስ በማስጠንቀቅ ይመልስላቸዋል፥ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ” ምንም ማስጠንቀቂያ አትጠብቁ፣ ሐሰተኛ ነብያት እንዳያታልሉአችሁ…
22Novእናንተም ደግሞ መሄድ ትፈልጋላችሁ? (ዮሐ 6፥68)
1. አንዳንድ ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ሁለት የተለያዩ አማልክት አሉ ብለው በማወቅ ወይም ባለማወቅ ያምናሉ። ሁለተኛው አምላክ የመጀመሪያው አምላክ “ዝግመተ ለውጥ” ነው ብለው ያምናሉ። አንዱ ህጉን የሚያስገድድ ብርቱው ፈራጅ የሆነው የብሉይ ኪዳን አምላክ ሲሆን፣ አንዱ ደግሞ የአዲስ ኪዳን አምላክ ነው። ሁለቱም ከምህረትና ይቅር ባይነት አንፃር እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ናቸው። እስከዚህ ያብራራሁት “ግኖሲስ” ተብሎ የሚጠራ በክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው መናፍቅ ነው (በእንግልዝኛ Gnosis ወይም Gnosticism)። የመጀመርያ ክርስቲያን ግኖሲስ ኢየሱስን እንደ “አዲስ ሰይጣን” አድርጎ ያስበው ነበር። ምንም እንኳ የማይረዳ ቢመስልም፣ በግኖሲስ ትምህርት መሰረት፣ በክፉ ፈጣሪ (የብሉይ ኪዳን አምላክ) ለተፈጠረ ለአዳም ዕውቀትና ነፃነት በማሳየት (“ግኖሲስ” በግሪክ ቋንቋ “እውቀት” መለት ነው)፣ ሰይጣን የብርሃን ምንጭ ነው ይለዋል። እንደ ግኖሲስ አስተሳሰብ፣ ዓለም በክፉ አምላክ የተፈጠረች የሰው ዘር የታሰረባት እስር ቤት ናት ብሎ ያምናል። ስለዚህ የፈጣሪ አምላክ ሕግ የሰው…
16Novየሦስታኛ አመት 31ኛ እሁድ (C OT-31)
ወንገል፥ ሉቃስ 19፥1-10 ቁ1 “ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮም ከተማ ገብቶ ያልፍ ነበር”፥ … ቀደም ባለው ምዕራፍ (ሉቃስ 18) ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ቀርቦ ዓይነሰውሩን ፈውሷል። አሁን ገብቶ ከተማውን እንደ አሸናፊ ሆኖ ያቋርጣታል። ሊደፈር የማይችል የኢያሪኮ ምሽግ ፈርሶአል። ዐይን ተፈወሰ፣ ብርሃንም ወደ ልብ የሚገባ ሲሆን ድንዛዜውን ይቀልጣል። የሰው ጨለማ ተቀደደ። ቁ2-4 “እነሆም ዘኬዎስ የሚባል ሰው፥ እርሱም የቀራጮች አለቃ ነበረ፥ ባለ ጠጋም ነበረ። ኢየሱስንም የትኛው እንደ ሆነ ሊያይ ይፈልግ ነበር፤ ነገር ግን ቁመቱ አጭር በመሆኑ ከሕዝብ ብዛት የተነሳ አቃተው። ኢየሱስ በዚያ በኩል ያልፍ ስለነበር ዘከወዎስ ያየው ዘንድ ወደ ፊት በመሮጥ በአንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ”፥ … ሰዎቹ መንገድ ውስጥ ስለገቡ ኢየሱስ እንዳይታይ ዘኬዎስን ከልክለውት ነበር። ዘኬዎስ ግን ሕዝቡን ችላ በማለት “ሞኝ ፍሬ” የሚያፈራ የሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረው፥ “እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም…
01Novየሦስተኛ አመት 29ኛ እሁድ (C OT-29)
ወንገል፥ ሉቃስ 18፥1-8 see here ቁ3 “በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች”፥ ሙሽራው ተወስዶባት መቼ እንደሚመለስ የማታውቅ መበለት የሉቃስ ቤተክርስቲያን ናት ”(5፥35፤ ሐዋ 1፥9-11)። መመለሻውን በመመኘት ብቻዋንና በሐዘን የምትኖር ናት። ለዚህም “ማራናታ” (1ቆሮ 16፥22፤ ራዕ 22፥20) ብላ ትለምናለች። መበለቲቱ ምንም ስጦታ የላትም። እንደ ሰው ምኞት ድሀ ናት። ፍላጎቷን ማሟላት የምትችለው አጥብቆ በመጠየቅ ብቻ ነው። 1ኛ ንባብ ዘጸአት 17፥8-13 see here ቁ8 “አማሌቅም መጥቶ ከእስራኤል ጋር በራፊድም ተዋጋ”፥ አማሌክ ወደ ቅድስት ምድር የሚመራውን መንገድ ይክዳል። ሙሴ እጆቹን በክርስቶስ መስቀል መልክ በመዘርጋት ይከፍተዋል። (AUGUSTINE) ቁ12 “የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ጠነከሩ”፥ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ግን በገዛ ኃይሉ በመስቀል ላይ እጆቹን ወደ ላይ ዘረጋ። ምስል እንዴት እንደተሰጠና እውነት እንዴት እንደሆነ…