- 18Dec
ለምን የከሪት እንጀራ?
“ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምስራቅ ሂድ” (1 ነገሥት 17፡2-7)። ምስራቅ ክርስቶስ ማለት ነው ወይም ደግሞ በመጀመሪያ የነበረ ወይም መነሻው ነው። ኤልያስ ወደ ክርስቶስ ዘወር ይላል፣ በተመሳሳይ ጊዜ ግን ወደ መነሻውም ይመለሳል። የትኛው መነሻ? በእውነቱ የከሪት ወንዝ በአብርሃምና በያዕቆብ ታሪክ ውስጥ የተከናወኑትን የመጀመርያ ክስተቶች ከሚያመለክቱ ወንዞች ከያርሙክና ከያቦቅ ወንዝ አጠገብ ይገኛል። የወንዝ ውሃም፣ ቁራዎቹ የሚያመጡ ሥጋና ዳቦ ደግሞ የሙሴን ታሪክ የሚያመለክቱ ምሳሌዎች ናቸው። እንዲያውም በምድረ በዳ ውስጥ እስራኤላዊያን ከዓለት የሚፈልቅ ውሃ ይጠጡና ከሰማይ በወረደ እንጀራና ሥጋ ይመገቡ ነበረ። ስለዚህ ኤልያስ የተባለው ማለት “ከዚህ ተነሥተህ ወደ መጀመሪያህና ወደ መነሻህ ሂድ” ማለት ነው። በኤልያስ ሕይወት ውስጥ እንዲህ ባለ አሳዛኝ ወቅት፣ ምግብና ዉሃ የእግዚያብሔር ፍቅር ምልክቶች ናቸው። “ከሪት ተብሎ በሚጠራው ሸለቆ ተሸሸግ”። እግዚያብሔር ኤልያስን ይሸሽጋል፣ ኤልያስ የእግዚያብሔር ሰው ነው፣ በርሱ ብቻ የእግዚያብሔር ቃል ይስተጋባል፣ ነገር…