የኢትዮጵያ ገና (Ethiopian Christmas)

የኢትዮጵያ ገና (Ethiopian Christmas)

 

የክርስቶስ ልደት ስርዓተ አምልኮ ከሁለት ሺ አመት በፊት በቤትለሔም ከተማ የተወለደውን ጌታችን እንድናስታውስ ይጋብዘናል፤ እያስታወስን እንሰግድለታለን፥ የክርስቶስ መጀመርያ መፅኣት መታሰቢያ ነው።

የ“መጀመርያ መፅኣት” ሲባል ሌላ መፅኣት እንዳለ መረዳት ይቻላል። እንዲያውም መጽሐፍእ ቅዱስ በሰው ታሪክ መጠረሻ ስለሚፈፀም ክርስቶስ የ”ዳግመኛ መምጣት” ይነግረናል።

የመጀመሪያ ክርስቲያኖች፣ የጌያችንን ልደት በሚያከብሩበት ወቅት፣ ለዘላለም ከእርሱ ጋር ለመኖር ስለሚፈልጉ፣ የክርስቶስ መመለስ በፍጥነት እንዲፈፀም ይመኙ ነበር።

ከዚያ በኋላ ግን የቤተክርስቲያን ታሪክ ለብዙ ዘመናት ስለተስፋፋ፣ የዚህ መፅኣት ምኞት ቀንሷል። የኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት በጣም ሩቅ እየሆነ ያለ ይመስል ነበር። በእርግጥ እንዲህ ሆኖአል ምክንያቱም ቤተክርስቲያን፣ እንደ እናት…

– ብዙ ቅዱሶን መውለድ ጊዜ እንዲኖራት፣ ከሁሉም ነገር በላይ እግዚአብሔር አምላክህን ውደድ የሚል ትዕዛዝ በታላቅ ገዳማዊ ተውፊት መተግበር ጊዜ እንዲኖራት

– ባለንጀሮችህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ትዕዛዝ በታላቅ የበጎ አድራጎት ሥራ መተግበር ጊዜ እንዲኖራት

– በታላላቅ የስነ ህንፃና የስነ ጥበባት ስራዎች ውስጥ ለድንጋይ ድምፅ መስጠት ጊዜ እንዲኖራት (ሉቃስ 19፥40 “እነርሱ እንኳ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ”)

– በቤተክርስቲያን ሙሁራን ጽሑፎች አማካይነትና ሌሎች ብዙ አስተምህሮና ጸሎት በማዋሐድ ለሰው ልጅ አእምሮ ብርሃን መስጠት ጊዜ እንዲኖራት

– በሰማዕታትና በደናግላን አማካይነት የክርስቶስን መስቀል ምስክርነት መስጠት ጊዜ እንዲኖራት

– በስብከቷና በአስተምህሮዋ ሰው ሁሉ እንዲድን፣ ለክርስቶስ ቃልና ለእውነተኛ ብርሃን እስትንፋስ መስጠት ጊዜ እንዲኖራት

– በቅዳሴ ሥርዓት በቅዱስ ቁርባን ምስጥር አማካይነት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ሁልጊዜ በሁሉም ስፍራ እንዲኖር ማድረግ ጊዜ እንዲኖራት።

አሁን ግን ይህ ሁሉ ምልክት ወደ ፍፃሜ የቀረበ ይመስላል፣

– ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ውስጥ ሳይቀር የገዳም ህይወት ጊዜው እንዳለፈበት ተደርጎ ይታሰባል

– ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ውስጥ ሳይቀር በክርስቶስ ፍቅር ላይ ተመሰርቶ የነበረ የበጎ አድራጎት ሥራ በማህበራዊ ስራ ብቻ (social work) ተተክቶአል (ይህም ራሱ ከተግባር ይልቅ በወረቀት…)

– ምክንያቱም የድንጋዮች ውበት ችላ ተብሏል

– የእውነት ብርሃን በባህል፣ በዩኒቨርሲቲዎችና በፖለቲካ ውስጥ ጠፍቷልና

– ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ድንግልና በሕብረተሰብ ተፌዞበታል እንዲሁም ተንቆአል።

በተቃራኒው አሁንም በዓለም ሁሉ ላይ በቁጥር ተባዝተው ያሉት፣ በእምነት የታወቁት የክርስቶስ ሰማዕታት፣  ሌሎች የወደቁትን ሁሉ የመተካት ኃላፊነት ያላቸው ይመስላል።

ስለዚህ በልደት በዓል ቀን እምነት ባላቸው ሰዎች የክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት እንዲፈፀም ለመጸለይ ጥልቅ ፍላጎት እንዲኖረን የሚያደርግ የጌታ “ናፍቆት” ተመልሶ ይሰማናል። በታሪክ ሂደት ውስጥ ክርስቶስ ይህን “ናፍቆት” የሚያረጋጋ በቅዱስ ቁርባን አማካይነት በመገኘቱ ነው።

በልደት በዓል ሌሊት በሚነበበው ወንገል፣ እረኞች በፍጥነት ማርያምና ዮሴፍ ወደሚገኙበት ብርሀን ተስበው ይሄዳሉ (ሉቃስ 2፥16)። በዚያ “ፍጥነት” የፍፃሜ ናፍቆታችን ሁሉ፣ ጊዜው እንዲፈጥን ያለን ፍላጎት ሁሉ  ይጠቃለላል፥ “እነዚያ ቀኖች ባያጥሩማ ኖሮ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን ስለ ተመረጡት ሰዎች እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ” (ማቴዎስ 24፥22)።

የማርያምና የዮሴፍ ቅርበት ይደግፈናል፣ ጊዜውን ያሳጥራል፣ ክርስቶስ እስኪመጣ ድረስ ይሸኘናል። ከእነሱ ጋር፣ ከዋሻው ደጃፍ አልፎ በመራመድ፣ እኛ ወደ ሰው ዘር እውነተኛ መኖርያ ወደ አስተማማኝ ቤታችን ቀርበናል።

ሕፃን ተወልዶልናልና ኑ እንስገድለት!

Leave a reply