- 26Oct
የሦስተኛ አመት 28ኛ እሁድ (C OT 28)
ወንገል፥ ሊቃስ 17፥11–19 see here ቁ14 “እነርሱም በመሄድ ላይ ሳሉ ከለምጻቸው ነጹ”፥ እኛ ቅዱስ ጉዞውን ለሚመራን ለቃሉ በመታዘዝ እንነጻለን። ቁ15 “ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ ተመለሰ”፥ ይህ “አንድ ብቻ” የእውነተኛው እስራኤል የቤተክርስቲያን ምስል ነው። ቁ17-18 “አሥሩ አልነጹምን? ዘጠኙስ ወዴት አሉ? ከዚህ ከልዩ ወገን በቀር እግዚአብሔርን ሊያከብሩ የተመለሱ አልተገኙም?”፥ አንድ እና ዘጠኝ እናነፃፅር። ብዛትን በተመለከተ ዘጠኝ ከአንድ ይበልጣል፥ ዘጠኝ ለማግኘት ዘጠኝ ጊዜ አንድ ያስፈልጋል። ነገር ግን ጥራትን በተመለከተ አንድ ቁጥር ከዘጠኝ ቁጥር ይበልጣል፥ አንድ ቁጥር የሙላት ስሜት ይሰጣል። ዘጠኝ ቁጥር ግን፣ አሥር ለመሞላት አንድ ስለሚጎድለው፣ የእጥረት አምሳያ ነው። አንድ ሲባል ከሌላ ሁሉ የተለየ ነው። እግዚአብሔር ከነፍስ ወደ ነፍስ ለያንዳንዱ ልብ ይናገራል። የክርስቶስ ፀጋ በእያንዳንዱ ሰው ነፍስ ውስጥ ይከሰታል እንጂ ለዘጠኝ ወይም ለአሥር ወይም ለጋራ አይከሰትም። ይህ ማለት በክርስትና ሕይወት ውስጥ ዋጋ ያለው…
17Octስለአየር ንብረት ያለው ክርክር የፖለቲካ መሣሪያ ነው
የሙቀት መጠን። በአሜሪካ ውስጥ በሙቀት መጠን ላይ ያሉትን መረጃዎች ከተመለከትን፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በእውነት የሙቀት መጠን ያደገ ይመስላል፣ ግን ከዚህ በታች ያለው ግራፍ እንደሚያሳየው፣ መረጃዎችን በረጅም እይታ ውስጥ ማየት ያስፈልጋል፤ የሁለት ክፍለዘመን ጊዜ ጥናት ውስጥ የምናስገባ ከሆነ፣ በሙቀት መጠን ላይ ያሉት መረጃዎች አይያሳስቡንም። የሰው ስራና የሙቀት መጠን። ከ 1940 እስከ 1975 ባለው ጊዜ ውስጥ፣ የኢንዱስትሪ ከፍተኛ እድገት እየታየ፣ ዓለም አቀፍ የሙቀት መጠን ዝቅ ያለበት ምክንያት ለምን ነው? ታሪክና የሙቀት መጠን። ያለፉት 1000 ዓመታት ከተመረመሩ፣ አለም አቀፍ የሙቀት መጠን ወደ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰው ከኢንዱስትሪ ዘመን በፊት ነው (በመካከለኛ ዘመን ላይ!)። ለምንድነው? CO2 የፀሐይ እንቅስቃሴእና የሙቀት መጠን። ከአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ከጀመርን፣ የሙቀት መጠን ከፀሐይ እንቅስቃሴ ጋር እንጂ ከCO2 እንቅስቃሴ ጋር አይሄድም። ለምንድነው? እንቁላል ወይስ ዶሮ ይቀድማል?። ሙቀት ወይስ የCO2 ልቀት ይቀድማል?…
10Octየአማዞን የጳጳሳት ጉባኤ (ሲኖዶስ)
ባለፈወ ጥቅምት 4 በቫቲካን ጋርደን በአማዞን ሲኖዶስ መክፈቻ ስነ-ሥርዓት ላይ የሆነውን ነገር አስተውላችኋል? ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አረማዊ ንጥረ ነገሮችን ያካተተ ሥነ ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል። የተለያዩ የአማዞን ሕዝብ መሪዎች ለእናት ምድር ጸሎት አቀረቡ። አንድ ዛፍ ተተክሎአል። አንድ ሰው በጉልበቱ ተንበርክኮ የቆሻሻ አቧራ ስሞአል። ከዝግጅቱ በኋላ ተሳታፊዎች ነፍሰጡር ሴቶች እና እናት ምድር የሚመስሉትን ሐውልቶች በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው ሲሰግዱ ታይተዋል። የእግዚአብሔር ቃልና የቤተክርስቲያን ትምህርትና ምስጥራት እስካሉ ድረስ፣ ወንጌልን መስበክ ይቻላል። ነገር ግን ወንጌላዊ ተልእኮ በአረማውያን ሥነ-አምልኮ ውስጥ መሳተፍን ያካትታል ብሎ የሚያስተምር መመሪያ አላውቅም። ከአረማውያን ጋር መነጋገር አለብን ከሚሉ ሰዎች ጋር መሄድ አያስፈልግም። ሚሽነሪዎች በአማዞን አካባቢ ገብተው እግዚአብሔር ዓለምን ስለወደደ አንድ ልጁን አሳልፎ እንደሰጠ ከልብና በፍቅር እንዲናገሩ ይገባል። የቤተክርስቲያን ተውፊት ክርስቶስን እንድንሰብክ ያስተምረናል። ይሁን እንጂ ከአረማውያን ጋር እንድንወያይ፣ በአረማውያን አምልኮ ውስጥ እንድንሳተፍም…
08Octቤታችን በእሳት ላይ አይደለም
በCO2 እና በአየር ብክለት መካከል ውስጥ ያለው ግንኙነት ምንድነው? CO2 ከአየር ብክለት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ደግሞ በአየር ንብረት ውስጥ የCO2 ብዛትና የሙቀት መጠን ግንኙነት እንዳላቸው የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማረጋገቻ የለም። እንዲያውም ባለፉት 5000 ዓመታት ውስጥ በአየር ንብረት ውስጥ አነስተኛ የCO2 መጠን ሲኖር ትልቅ የሙቀት ለውጥ ተመዝግበዋል። እውነት ለመናገር በምድር ላይ ያለው ሙቀት እየጨመረ መምጣቱ እውነት ነውን? የሰው ስራ በነዚህ ለውጦችላይ ምን ያህል ተጽዕኖ ያሳድራል? በ1400 ዓ.ም. አካባቢ ሳይንቲስቶች “የበረዶ አነስተኛ ዘመን” ብለው የጠሩት የብርድ ዘመን ነበር። ከ1400 እስከ 1700 ዓ.ም. ድረስ የሙቀት መጠን እየወረደ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን በ1700 ተመዝግቦአል። ከ1700 ዓ.ም. ጀምሮ በምድር ላይ ያለው የሙቀት መጠን ደጋሚ ወደ ላይ ከፍ ማለት ጀምሮአል። ይህ የሚያመለክተው የተፈጥሮ የአየር ንብረት ስርዓት በአሁኑ ጊዜ “በሙቀት” ደረጃ ላይ መሆኑን ነው። ሆኖም፣ አሁንም ቢሆን…