- 24Sep
ባለፈው ሰኔ ወር ውስጥ ለአንድ ትልቅ የምዕራብ አገር ፓርላማ የአየር ንብረት ለውጥ (global warming) ምክንያት ሰው መሆኑ የመንደር አፈታሪክ ነው ብሎ የሚከራከር አቤቱታ ተልኳል። አቤቱታው ከፍተኛ እውቀት ባላቸው በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 200 የሳይንስ ሊቃውንት ተፈርሞአል። ሰነዱ የሚከተለውን ይገልጻል፥ ከ1950 እስከ 2000 ባነበሩት ዓመታት የታየው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ አስደንጋጭ ጉዳይ አይደለም፥ ቀደም ብለው በነበሩት ጊዜያት ይበልጥ ሞቀታማ ወቅቶች ተከስተዋል። ደግሞም ከ2000 ጀምሮ እስከ ዛሬ በምድር ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ቆሞአል። የአየር CO2 ማደግ የጀመረው ከፍተኛ ሰው ሰራሽ ልቀቶች ከመኖራቸው በፊት ነው (ማለትም ከ 1700ዎቹ ዓመታት በኋላ ከተጠቀሰው የአየር ልውጥ ጋር ተያይዞ ነው)። በተቃራኒው በኢንዱስትሪ ዘመን በአየር ንብረት ውስጥ የተከሰተው የCO2 ጭማሪ በአለም አቀፍ አማካይ የሙቀት መጠን ላይ ፋይዳ የለውም (የCO2 ክምችትና የሙቀት መጠን ተመጣጥነው አያድጉም)። የCO2 መጨመር በዓለም አቀፍ ዕፅዋት…
21Sepጌታችን ሆይ፣ ስለ እኛ ሳይሆን፣ ስለስምህ ክብር ይሁን። (መዝሙረ ዳዊት)
ጌታችን ሆይ፣ ስለ እኛ ሳይሆን፣ ስለስምህ ክብር ይሁን። (መዝሙረ ዳዊት) ስለሚያቃጥለን ፀሐይ፣ ስለሚያርሰን ዝናብ፣ እንከን የለሽ ስለሆነው የጀግኖች ትግል፣ እናመሰግንሀለን። ስለሚያሠቃየን ረሀብ፣ ስለሚያደርቀን ጥማት፣ እጅና እግር ሲዳከም፣ እናመሰግንሀለን። ስለሚያሳውረን ነፋስ፣ ስለሚያነደን አሸዋ፣ በጭቃ ውስጥ ስለፈሰሰ ደማችን፣ እናመሰግንሀለን። በውጊያ እያለን እንቅልፍ ባጣን ሌሊት፣ ልብን በእውነተኛ ደስታ ስለሚሞላ ጽሞናና ጸሎት፣ እናመሰግንሀለን። ስለጠላታችን እንባ፣ በጦር ሜዳ ስንጋለብ፣ ድግሳችን በሆነው በውጊያ እልልታ፣ እናመሰግንሀለን። በሰዎች ልብና በግምቦች ጫፍ ጎልቶ ስለሚታይ እምነት፣ ስለሚጠብቀን አዳኝ ሞታችን፣ እናመሰግንሀለን። ከፊትህ ለመምጣት ስላለን አስደሳች ተስፋ፣ ደረታችን ቆስሎ ስንጸዳ፣ እናመሰግንሀለን። በልባችን ውስጥ ስለሚያነቃቃን የጦር መሳሪያ ፍቅር፣ ስለታላቁ ክብርህ ክቡር ጌታችን ሆይ፣ እናመሰግንሀለን። ጌታችን ሆይ፣ ስለ እኛ ሳይሆን፣ ስለስምህ ክብር ይሁን። (መዝሙረ ዳዊት) (የቤተመቅደስ ፈረሰኞች መዝሙር Templars’ Hymn)