- 28Mar
የአብይ ጾም 4ኛ እሁድ (A LENT-4)
ወንገል፥ ዮሐንስ 9፥1-41 ቁ7 “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው”፥ … “እግዚአብሔርም ደግሞ ተናገረኝ እንዲህም አለኝ፥ ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚሄደውን የሰሊሆምን ምንጭ ውኃ ጠልቶአልና…” ብርቱና ብዙ ውኃ ባለው በኤፍራጥስ ወንዝ ተደስተዋል (ትንቢተ ኢሳይያስ 8፥5-7)። “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል” (መዝሙረ ዳዊት 23)። እምነት በጸጥታ በሚሄድ ውኃ ውስጥ፣ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይገኛል። እንቁም፣ ፀሎትን እንጨምር፣ ወደ ራሳችን እንግባ። እግዚአብሔር የሚገኘው በጸጥታ በሚፈስ ውሃ ውስጥ ነው እንጂ በኤፍራጥስ ወንዝ ብርቱ ግፊት ውስጥ አይገኝም። 1ኛ ንባብ፥ 1ኛ ሳሙኤል 16፥1-13 ሳሙኤል ዳዊትን ይቀባል፣ ከዚህ ቀን ጀምሮ ዳዊት ንጉሥ ነው። ነገር ግን ዳዊት እንደ ንጉሥ የሚገለጸው ከሳኦል ሞት በኋላ ብዙ ችግርና መከራ ካሸነፈ በኋላ ብቻ ነው። ሆኖም ግን ከዚያ በፊት እግዚአብሔር አስቀድሞ በስውር መርጦት ነበረ። ማንም እንደማያስተውለው እግዚአብሔር በስውር ይሠራል።…
20Marየአብይ ጾም 3ኛ እሁድ (A LENT-3)
ወንገል፥ ዮሐንስ 4፥5-42 ቁ6 “በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ የተነሳ ስለደከመው በጕድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ”፥ … እዚህ ላይ ሁለት ነገሮች ይጠቁማሉ፥ ድካምና ስድስተኛ ሰዓት። ስድስተኛ ሰዓት ክርስቶስ የተሰቀለበት ሰዓት ነው፣ ድካም ደግሞ የመስቀሉ ድካም ነው። በሰማርያ ጕድጓድና በመስቀል ላይ የተከሰተውን ማነጻጸር እንችላለን፥ በሰማርያ ጕድጓድ ኢየሱስ ውሃን ይጠይቃል፣ በመስቀል ላይ “ጠማኝ” ይላል። በሰማርያ ጕድጓድ ኢየሱስ የውሃን ጥማት ለዘላለም የሚያረካ የሕይወትን ውሃ ይሰጣል፣ በመስቀል ላይ ጎኑ ራሱ የሕይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል። “ለሁሉ ሰው የሕይወት እስትንፋስ ምንጭ የሆነው ክርስቶስ በጉዞ ምክንያት ደክሞ ስለነበረ በሰማርያ የውሃ ምንጭ አጠገብ ተቀመጠ። ጊዜውም የሚያቃጥል ሙቀት ውቅት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ። መሲሑ በጨለማ ያሉትን ሊያበራላቸው የመጣው እኩለ ቀን ነበር። ውሃን የፈጠረ ለመጠጣት ሳይሆን ለማንጻት ወደምንጩ መጣ። የዘላለማዊነት…
13Marየአብይ ጾም 2ኛ እሁድ (A LENT-2)
ወንገል፥ ማቴዎስ 17፥1-9 ቁ1 “ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው”፥ … “ከስድስት ቀንም በኋላ”፥ … ከባርነት ነፃ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት ለመድረስ እስከ ዛሬ ድረስ አብሮ በምጥ ጭንቀት ተይዞ በመቃተት ላይ ያለው የፍጥረት ፍጻሜ ሰባተኛው ቀን (ሮሜ 8፥21-22) የሁሉ ፍጥረት አላማ ነው። “ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ”፥ … “ጴጥሮስ ያዕቆብና ዮሐንስ ከርሱ ጋር ባላቸው ቅርበትና ፍቅር ምክንያት ኢየሱስን ወደ ተራራ ይሸኛሉ” (JOHN CHRYSOSTOM 344-407) ታቦርና ደብረዘይት ማነፃፀር እንችላለን። በታቦር ላይ አብ ልጁን ሲጠራ፣ በደብረዘይት ላይ ኢየሱስ አባቱን ይጠራል። ታቦር ላይ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ያሳያል፣ በደብረዘይት ደግሞ ኢየሱስ ሰው መሆኑን ያሳያል። ቁ2 “በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ”፥ … ይህ መለወጥ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ሁሉ ያቀደ…
05Marየአብይ ጾም 1ኛ እሁድ (A LENT-1)
ወንገል፥ ማቴዎስ 4፥1-11 የኢየሱስ ፈተናዎች ከሦስት ጣዖታት ጋር የተዛመዱ ናቸው፥ እነሱም ድንጋዮችን ወደ እንጀራ የሚቀይር የኢኮኖሚ ጣዖት አምልኮ፤ እግዚአብሔርን መግዛት የሚፈልግ የሃይማኖት ጣዖት አምልኮና ሁሉን ሰው መግዛት የሚፈልግ የፖለቲካ ጣዖት አምልኮ ናቸው። ቁ1 “ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው”፥ … “ይፈተን ዘንድ”፥ … “ልጄ ሆይ፣ እግዚአብሔርን ለማገልገል ራስህን ካቀረብህ ለፈተና ተዘጋጅ” (ሲራክ 2፥1)። ጥሩ ውሳኔ ከተወሰነ በኋላ የመፅናት ትግል አለ። በግሪክ ቋንቋ “ፈተና” “peiro” ይባላል፣ “peiro” ማለት ማቋረጥ ማለት ነው፥ experience በማድረግ (experience = “peiro”), expert (“peiro”) እንሆናለን። በድሮ ታሪክ ፈተናዎች እንዲሁ ትምህርት ይባሉ ነበር፥ እሱም ልጆች መሆናችንን እንጂ ዳቃሎላዎች አለመሆናችንን የሚያረጋግጠው የልጅ ሕይወት ሥልጠና ነው (ዕብራውያን 12፥8) ፣ በእምነት ደረጃ የመጣራት ሥልጠና ነው (ያቆብ 1፥2-4፣ 1ጴጥሮስ 1፥6)። “ከዲያብሎስ”፥ … በግሪክ ቋንቋ “ዲያብሎስ” ማለት የሚከፋፍል ማለት…