- 03Jun
ችግሮችን ማስወገድ ወይስ ህፃናትን ማጥፋት? የ2030 አጄንዳ እና የህይወት መብት
ህይወትን በተመለከተ፣ በተባበሩት መንግስታት ላይ ጥርጣሬ ውስጥ የምንወድቀው እኛ ብቻ አይደለንም። በ 1994 GC ካይሮ ውስጥ በተካሄደው የሕዝብና ልማት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ጀምሮ (International Conference on Population and Development)፣ የabortion ተሟጋቾች በተባበሩት መንግስታት ሰነዶች ቋንቋ በመጠቀም አጀንዳቸውን ማራመድ ከጀመሩ ቆይተዋል። ብዙን ጊዜ በተባበሩት መንግስታት ሰነዶች ውስጥ በሚገኘው “የወሲብና የስነ ተዋልዶ መብቶችና ጤና አገልግሎት” (“sexual and reproductive rights” and “sexual and reproductive health care services”) በሚል ሀረግ ትርጉም ላይ እስካሁን ያልተቋረጠ ትግል ተካሄዶአል። የabortion ተሟጋቾች የወሲብና የስነ ተዋልዶ መብቶች የውርጃን መብት እንደሚያካትቱ ያምናሉ። የተባበሩት መንግስታት በ2015 GC በጻፉት የዘላቂ እድገት አላማዎች አጄንዳ ዙርያ (Agenda 2030) ይህ ፊልሚያ አሁንም እንደገና ተፋፍሟል.። እንዲያውም በአጄንዳ ቁትር 3.7 እና 5.6 ውስጥ ከላይ የጠቀስኩትን ቋንቋ እናገኛለን። ምንም እንኳን abortion የሚል ቃል በሰነዱ ውስጥ ባይኖርም፣ አጄንዳን 2030…