- 24Aug
ድንግል ማርያም ከዚህ ሕይወት እንዴት እንዳለፈችና በመላእክት እጅ ወደ ሰማይ እንደፈለሰች እናስባለን።
ቅድስት ድንግል ማርያም የሞተችው በንጹህ ፍቅር ተጠምቃ ነው እንጂ በህመም ምክንያት አይደለም። ልጆችዋ ደግሞ የእናታቸውን ምሳሌ መከተል ስላለባቸው ከዚህ አለም ስትለይ በአስደሳቸ ሞት መለየት ከፈለክ እግዚአብሔርን ውደድ። ነፍሷ ሁልጊዜ በዓለም ውስጥ ካሉ ነገሮች ሁሉ ተለይታ የምትኖርና ሁልጊዜም ከእግዚአብሔር ጋር የምትዋሐድ ስለነበረ፣ የቅድስት ማርያም ሞት አስደሳች ነበር። ፀሐይን የለበሰች፣ ጨረቃን ከእግሯ በታች ያደረገች፣ የዚህን ምድር ሀብት ትረግጣለች። አንተም በሞት ጊዜ መደሰት ትፈልጋለህ? ከሁሉም ነገር፣ ከዘመድም፣ ከክብርም፣ ከሀብትም፣ ከስጋህም ተለይተህ ኑር። ምክንያቱም ከእነዚህ ነገሮች ጋር በመያያዝህ ሞትህ መራራ ይሆናል። ሁልጊዜ ቅድስት፣ ሁልጊዜም ንፁህ፣ ሁልጊዜም ከኃጢአት ጥላ ነፃ ስለነበረች፣ የቅድስት ማርያም ሞት አስደሳች ነበር። አንተም ከኃጢያት የጸዳ የሆነውን ቅዱስ ሕይወት በመምራት፣ ሞትህ አስደሳችና ጣፋጭ እንዲሆን ታደርጋለህ። በሰማይ ክብር በእግዚአብሔር እንደምትደሰት እርግጠኛ ስለነበረች፣ የቅድስት ማርያም ሞት አስደሳች ነበር። ከዚህ አለም ስትለይ በአስደሳቸ ሞት መለየት…