[UR1] ኢየሱስ ባለተወለደ ቢሆንስ? What if Jesus was never born?

[UR1] ኢየሱስ ባለተወለደ ቢሆንስ? What if Jesus was never born?

የስልጣኔአችን ሥሮች በእሱ ላይ የተመሰረቱ ናቸው እና በአጭሩ ያለ እሱ አይሆኑም ነበር። አንዳንድ ምሳሌዎች እነሆ፥

ሆስፒታል

የሆስፒታሎችና የህሙማን እንክብካቤ እድገት ድሆችንና የህሙማንን ከክርስቶስ ስቃይ ማነጻጸር ከእምነት የመነጨ ነው፣ በምድራዊ ሕይወቱ ኢየሱስ የሥጋና የነፍስ ፈዋሽ ሆኖ ራሱ ሕመምተኛ ነበረ፤ የመካከለኛው ዘመን የሥነ-መለኮት ምሁራን እንዳሉት ኢየሱስ ራሱ ሐኪምና ህመምተኛ ነበረ። በመካከለኛው ዘመን የተሠሩ ብዙ ሆስፒታሎች (አብዛኛውን በገዳማት አጠገብ) “Domus Dei” (የእግዚአብሔር ቤት) ተብለው ይጠሩ ነበር። በላቲን አሜሪካ፣ እስያና አፍሪካ የመጀመሪያ ሆስፒታሎች በካቶሊክና በፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያን ተመሰርተዋል፥ ዛሬም ቢሆን የአብያተ ክርስቲያናት ጤና አገልግሎት በብዙ አገሮች ውስጥ ትልቅ ሚና አላቸው።

የሕፃናት ክብር

ክርስትና በተስፋፋ ቁጥር፣ ፅንስ ማስወረድ እና ሕፃናትን ማስወገድ በሕብረተሰብ ተቀባይነት ባለማገኘታቸው ተገድበዋል። በሮማ ግዛት ውስጥ የማይፈለጉ ሕፃናትን በገበያ መሸጥ በስፋት ተለምዶ ቢሆን ኖሮ፣ ክርስቲያኖች ይህንን ድርጊት እንደ ግድያ ያወግዙት ነበር። ዮስቲኖስ ሰማዕት (100-165 ዓ.ም.) እንደተናገረው፣ “የሕፃናት ገበያ ላይ መዋል መጥፎ እንደሆነ ተምረናል […] በዚህ ድርጊት ገዳዮች እንሆናለን”። ከንጉሥ ኮንስታንቲኖስ ጀምሮ ሕጎች ሕፃናትን መግደል ይከለክሉና እንዲሁም ልጆቻቸውን በኢኮኖሚ ምክንያት እንዳይሸጡ የተቸገሩ ቤተሰቦችን ይረዱ ነበር።

የሴት ክብር

ብዙውን ጊዜ በግሪክ ሕብረተሰብ ክብር የማይሰጣትና የምትናቅ፤ በሮም ሕብረተሰብ ውስጥ በአባትና በባለቤት ቁጥጥር ስር የነበረች፤ በጀርመን ሕዝቦች መካከል በወንድ ኃይል ታፍና የነበረች፤ በአይሁድ ዓለም ውስጥ ያለ ሕጋዊ ከለላ መወገድ የምትችል፤ በቻይናና በሕንድ ውስጥ ገና ሳትወለድ እስክትገደል ድረስ የብዙ ጥቃት ሰለባ የምትሆን፤ በሂንዱ ሀይማኖት ውስጥ እንደ ዝቅተኛ የተፈጥሮ ቅርፅ የምትገመት፤ በእስልምናና በባህላዊ ሀይማኖት ውስጥ የራሷ በታችነት አዋራጅ ማረጋገጫ ሲሆን አንድ ባለቤት ከሌሎች ሴቶች ጋር መከፋፈል ያለባት፤ በተለያዩ ባህሎች የብዙ አካል ጉዳት ሰለባ የምትሆን፤ በሁሉም ጥንታዊ ባሕሎች ለክህደት ተጋልጣ የነበረች፣ በክርስትና ውስጥ ሴት ልጅ ከወንድ ጋር እኩል ሆና የእግዚአብሔር ፍጡር ትሆናለች።

ገብቻ

የክርስትና ጋብቻ በአንድ ወንድና በአንድ ሴት መካከል ብቻ ስለሆነና መፋታት ስለማይቻል፣ በሙሽራዎች መካከል ባለው እኩል ክብር ላይ ይመሰረታል፥ ብዙ ሚስቶች ማግባት በሕግ ያልተፈቀደ ነው! ወንድ በጉልበቱ በመጠቀም ሚስቱን ልክ እንደ እቃ በመቆጠር መካድ ወይም በሴት ባርያ መተካት አይችልም! ወንድ በሴት ላይ የነበረውን ማንኛውንም የሕይወትና የሞት መብት በመከልከል፤ የሙሽራዎችን ነጻ ፍቃድ በተቻለ መጠን በመጠበቅ (ቅዱስ አውጉስቲኖስ “የወላጅ ጣልቃ ገብነት መለኮታዊ መብት አይደለም” በማለት አስፈላጊ እንዳልሆነ ያስገነዝል)፤ ከሀላፊነትና ከነፃነት አንፃር ሲታይ የሙሽርነትን ጋብቻ ዕድሜ ከፍ በማድረግ፤ አብኣኛውን ጊዜ ሴት ልጅን የሚጎዳ የግዳጅ ጋብቻን በየትኛውም መንገድ በመቃወም፤ የልጆችን ጤና እንዲጠበቅ የሥጋ ዘመድ ጋብቻ በመከልከል፥ የቤተክርስቲያን ታሪክ በሙሉ፣ ከጋብቻ ሕግ አኳያ፣ ይህንን እኩል ክብር ለማዳን የቆመ ነው።

ባርነት የሚወገድበት

ሁላችንም የአንድ አባት ልጆች ከሆንን፣ በእርሱ ፊት እኩልነታችንን መገንዘብ ያስፈልጋል። ባሪያ   “የአባታችን” ልጅ በመሆኑ የእግዚአብሔርም ልጅ ነበረ። Lactantius ጌታና አገልጋይ ወንድማሞች ስለሆኑ እኩል ናቸው በማለት አረጋግጠዋል፤ የእስክንድርያው ቅዱስ ክሌመንት እንዳስተማረው “አገልጋዮችን እንደራሳችን መቆጠር አለብን፣ ምክንያቱም እንደኛ ሰዎች ናቸው፣ እግዚአብሔርም ለሁሉም &ለባርያም ለነፃም) እኩል ነው”። የሮማዊያን የባርነት ባህል ደረጃ በደረጃ የፈረሰው በዚህ ክርስቲያናዊ አመለካከት ምክንያት ነው። ንጉስ ቆስጠንጢኖስ በዚሁ እምነት ምክንያት ስቅለትን ከልክሎአል፣ ባሪያዎች በአውሬ ይገደሉበት የነበረውን የስታዲየም ጨዋታ ተቃውሞአል፣ በባሪያዎች ላይ ይታተም የነበረውን የእሳት ምልክትና ሕፃናትን ሽያጭ አስወድዶአል።

የተፈጥሮ ሳይንስ

በተፈጥሮ ፊት የምንገናኝበት አስተሳሰብ ወሳኝ ነው። የክርስቲያን አእምሮ ዓለም መልካም እንደሆነ ያምናል። “ቃል ሥጋ ሆኖ፤ በመካከላችንም ባደረ ጊዜ”፣ ተፈጥሮአዊ ዓለም ይበልጥ ከፍ ያለ ክብር አገኝቶአል (ዮሐ 1፥14)። አለም የአእምሮ ምንጭ በሆነው በእግዚአብሔር ስለተፈጠረ፣ ሥርዓትና አእምሮአዊ ሕግ ተፅፎበታል። በመካከለኛው ዘመን በጣም ከተጠቀሱት ሐረጎች ውስጥ አንዱ በመጽሐፈ ጥበብ፣ ፈጣሪ “ሁሉን ነገር በመጠን፣ በስሌትና በክብደት ሚዛን አደራጅቷል” (ጥበብ 11፥20) የሚል ነበረ። ሥርዓትና ነፃነት በአንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ናቸው ተብሎ ይታመናል። ክርስቲያኖች ተፈጥሮአዊው ሥርዓት ለሰው ልጆች አእምሮ ተደራሽ መሆኑን ያምናሉ፣ ስለ ዓለም ዕውቀት ማግኘት እንደሚቻልም ያምናሉ። የመጀመሪያ የታሪክ ዩኒቨርሲቲ በመካከለኛ ዘመን አውሮፓ ውስጥ በካቶሊክ ተጀምሮአል።

የፖሊቲካ አስተዳደር

በእግዚአብሔር ግልጸጥ የተረጋገጠው “የሕብረተሰብ ጥቅም” እና “የተፈጥሮ ሕግ” በክርስቲያናዊ የፖለቲካ አስተዳደር ሀሳብ መሠረት ነው። “የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ” (ማቴ 22፥21) በማለት፣  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር የሆነው ሁሉ ለእግዚአብሔር እንዲሰጥ አዝዞአል። ይህ ትእዛዝ ደግሞ በየትኛውም ባለስልጣን ላይ ይሠራል። በዚህ መንገድ ቤተክርስቲያን የክርስቲያን እምነት በማይሻማ ሕዝባዊ ሚና ለራሷ በመያዝ፣ እራሷን የመንግስት የመሰረታዊ እሴቶች መመሪያ አድርጋ ታቀርባለች። ታሪክ እንደሚያሳየው፣ ያለዚህ መመሪያ፣ ግዛቶች ሰብዓዊነትን በሚገድል አስተዳደር ውስጥ ይወርዳሉ። በሌላ በኩል፣ ኢየሱስ እምነትንና የሕብረተሰብን ጥቅም ለሚያከብር መንግሥት ታማኝ አባል የመሆን ግዴታው ይገልፃል። ይህ አስደናቂ የክርስትና ትምህርት የብዙ ከፍለዘመን የፖለቲካ አስተዳደር መሠረት ነበረ፤ ነገር ግን ዛሬ፣ ከዚህ እይታ አንጻር፣ ዓለም ሙሉ በሙሉ ሌላ ጎዳና ይዞአል።

Leave a reply