- 17Jul
የአንደኛ አመት 14ኛ እሁድ (A OT-14)
ወንገል፥ ማቴዎስ 11፥25-30 1 “አባት ሆይ! … አመሰግንሃለሁ” (25)፥ … በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወልድ ወልድ የሚሆንበት “አባባ” የሚል ቃል በልባችን ውስጥ ይመነጫል (“አባባ” ሕፃን ልጅ አፍ መፍታት በሚጀምርበት ጊዜ የሚናገረው ቃል ነው)። በአብና በወልድ መካከል ባለው መግለጽ በማይቻል ውይይት ውስጥ እንገባለን። በቅድስት ሥላሴ ውስጥ እንገባለን። > ፍጥረት ሁሉ አላማውን ይፈጽማል፥ የእግዚአብሔር ልጅ እና የሰው ልጅ በሆነው በኢየሱስ ዋሽንት ድምጽ ተደስተን፣ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያዋሕደውን የሰርግ ግብዣ እንሳተፋለን። በስጋው አማካይነት እያንዳንዱ ስጋ ከክብር ጋር ይዋሐዳል። > አባባ ተብሎ የሚጠራ “የሰማይና የምድር ጌታ ነው” (25)። ለእኛ ቅርብና አፍቃሪ የሆነ አባታችን ልዑልና ሁሉን የሚችል ነው። እንደ ጣዖት እንዳይታይ፣ እግዚአብሔር የሚገለጸው በተቃራኒ ቃላት አማካይነት ነው፥ እርሱ ቅርብና ልዑል፣ አፍቃሪና ኃያል፣ ትሁትና ታላቅ፣ እናትና አባት ነው። > የአለም ጥበበኞችና ብልጦች ስልጣን ያለውን ጥበበኛ አምላክ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ። ትሁታንና ታናናሾች ግን…