- 30May
የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት (A-PHASIKA-Ascension)
1ኛ ንባብ፥ የሐዋርያት ሥራ 1,1-11 √ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ አይን ተለይቶ ቀረ። እስከዚያ ቀን ድረስ እየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ይኖርና ይበላ ነበር፤ በገሊላ መንገዶች ላይም ከእነርሱ ጋር ይራመድ ነበር፣ ድምጹን ለመስማት እና ተዓምርን ለማግኘት ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ይሰባሰቡ ነበር። አሁን ግን ከእነርሱ ተለይቶ ቀርቷል። ነገር ግን እየሱስ ደቀመዛሙርቱን አልተወም፣ ይልቁን በውስጣቸው መኖር ጀምሯል። ካረገ በኋላ እየሱስ ከአይናቸው ቢለይም በነፍሳቸው ውስጥ መኖር ጀምሯል። በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ክርስቶስ በደቀመዛምርቱ ይኖራልና ደቀመዛሙርቱም በእርሱ ይኖራሉ። “በእኔ ኑሩ፣ እኔም በእናንተ እኖራለሁ” የሚል የኢየሱስ ቃል እና ትእዛዝ እንደሁ ተፈጽሟል (ዮሐንስ 15፥4)። √ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ሲያናግሩ ለመጀመርያ ጊዜ “ጌታ ሆይ!” ብለው ይጠሩታል (6)። ‘ጌታ’ በግሪክ ቋንቋ ‘ኪርዮስ’ (κύριος) ይባላል። ‘ኪርዮስ’ ማለት ደግሞ በሲና ተራራ ላይ እግዚአብሐር ለሙሴ የገለጸለት ስም ነው። ይህ ስም በብሉይ ኪዳን ማንበብ የተከለከለ ስለነበረ፣…
16Mayየፋሲካ 5ኛ እሁድ (A-PHASIKA-5)
ወንገል፥ ዮሐንስ 14,1-12 √ መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ (6)፣ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም፥ ኢየሱስ ወደ አብ የሚመራ መንገድ ነው። ወደ ሰማይ መድረስ የምንችል፥ > ትእዛዞቹን በመፈጸም > በእምነት አማካይነት፣ ምክንያቱም ጌታችን የመጣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኝ ነው” (ዮሐንስ 3,15) > የእርሱን ምሳሌ በመከተል፣ ምክንያቱም ክርስቶስን ካልመሰለ ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም > ከሁሉ በላይ፣ ክርስቶስ ስጋን ለብሶ በመስቀል ላይ ስለሞተ > ክርስቶስ ከእርሱ ጋር አንድ ተፈጥሮ ያለውን አባቱ ስለገለጸ። √ ኢየሱስ መንገድ ነው። እርሱ ሰማይና ምድርን የሚያገናኝ ብቸኛው መንገድ ነው። በመካከላችን በኖረበት ጊዜ በዚህ ምድር ላይ የእርምጃዎቹን ግልጽ ዱካዎች ትቶአል። የእርሱ እርምጃዎች የዘመናት ብልሽትና የጠላት ሸፍጥ ማጥፋት ያልቻሉ የማይሰረዙ እርምጃዎች ናቸው። “መንገድ የሆነው የሰው ፋና ወደሌለው ቆሻሻ አይመራንም። እውነት የሆነው በሐሰት አያፌዝብንም። ሕይወት የሆነው…
15May[LR2] About Bill Gates
Bill Gates ለአለም ጤና ድርጅት (WHO) ቀዳሚ የገንዘብ ምንጭ ነው። ቀደም ብሎ በ 2018 ከዳቮስ ጓደኞቹ ጋር ተሰማምቶ ወረርሽኝ እንደሚከሰት ትንቢት ተንብዮ ነበረ። ለረጅም አመታት ህዝብን በማጥፋት በአለም ላይ የቁጥጥር እቅዶችን ሲያበረታታ መቆየቱ ይታወቃል። “በአዳዲስ ክትባቶች አማካይነትና በስነ ተዋልዶ ጤና ላይ ጥሩ ሥራ ከሠራን፣ የአለምን ህዝብ በ 10-15% መቀነስ እንችላለን” (B.G.) “አለምን ማዳን የሚቻለው የሰው ዘር በማጥፋት ዘመቻ ብቻ ነው (genocide)” (B.G.) በክትባቶቹ ምክንያት በአፍሪካ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች መካን ሆነዋል። በክትባቶቹ ምክንያት ሕንድ ውስጥ 500,000 ሕፃናትን ሽባ ያደረገ የፖሊዮ ወረርሽኝ ተከስቷል። በአፍሪካ ውስጥ የአለም ጤና ድርጅትና Bill Gates ‘የለገሱት’ DPT ክትባቶች የሕጻናትን ህይወት ቀጥፏል፤ በMonsanto ታቅደው በBill Gates ‘የተለገሱት’ ምግቦች፣ ሕዝብን በሙሉ መካን የሚያደርጉ ናቸው። ለኮሮና ቫይሩስ ክትባት አያስፈልግም፥ sero-therapy ቀደም ብሎ 100% ታካሚዎችን እየፈወሰ ነው። ወጪ ስለሌለው ግን…
09Mayየፋሲካ 4ኛ እሁድ (A-Phasika-4)
ወንገል፥ ዮሐንስ 10፥1-10 √ ወደ በጎች በረት በበር የማይገባ ሰው ሌባና ዘራፊ ነው (1)፥ መንጋውን ቀስ ብሎና በድብቅ መጉዳት ይቻላል፣ ወይም በግልጽና ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም መጉዳት ይቻላል። የክርስቶስ ጠላቶች በሁለቱም ዘዴዎች ተጠቅመው ያውቃሉ። “ውጭ ስንት በጎች አሉ፣ ውስጥ ስንት ተኩላዎች አሉ? ውስጥ ስንት በጎች አሉ፣ ውጭ ስንት ተኩላዎች አሉ?” (Augustine of Hippo †430) √ እረኛ የራሱን በጎች በየስማቸው ይጠራቸዋል (3)፣ በጎቹም ድምጹን ስለሚያውቁ ይከተሉታል (3-5)፥ ምሽት ላይ ብዙ መንጋዎች በዘበኛ እየተጠበቁ ሌሊቱን በሙሉ ያድሩበት በነበረ በአንድ በረት ውስጥ ይሰበሰቡ ነበር። በማለዳ እያንዳንዱ እረኛ ወደ አጥሩ በር መጥቶ በጎቹን አንድ ላይ ይጠራል። በጎቹ ተሰብስበው በረቱን ትተው እረኛውን ይከተላሉ። በጎቹ እንዳይጠፉ ደጋግሞ እረኛው ድምፁን እያሰማ እነሱን ወደ መስክ ስፍራ ለመምራት ከፊት ለፊታቸው ይጓዝ ነበር። መለኮታዊ ትምህርት ለመግለጽ ጌታችን ኢየሱስ ለአድማጮቹ በጣም የታወቀ የነበረውን ይህ…
02Mayየፋሲካ 3ኛ እሁድ (A PHASIKA-3)
ወንገል፥ ሉቃስ 24፥13-35 √ ሁለት ደቀመዛሙርት (13)፥ አንዱ ቀለዮጳ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ አይታወቅም፣ በስሙ ፋንታ የእያንዳንዳችንን ስም መወከል እንችላለን። ሁለቱ ደቀመዛሙርት ይጓዙ ነበር፥ ሰው በምኞቱ ተመርቶ ሁል ጊዜ መንገደኛ ነው። እየተጓዙ እርስ በእርሳቸወ ይወያዩ ነበር (14)፥ እኛ የምንወያይ በልባችን ስላለው የምንመኘውና የምንወደው ነገር ነው። √ ኢየሱስ ራሱ ወደ እነርሱ ይቀርባል (14)፥ ከሞት የተነሣ ክርስቶስ ወገኖቹን አይተውም፣ አሁን ለሁሉም ሰው እና በሁሉም ቦታ ለእነርሱ ቅርብ መሆን ይችላል። እንዲሁም በተዘጉ በሮች፣ በተሰወሩ አይኖች እና በደነደኑ ልቦች መግባት ይችላል። ወንጀለኛውን እስከ መስቀል ድረስ እንደፈለገ፣ አሁንም መንግሥቱን ይሰጠን ዘንድ እያንዳንዳችንን ይፈልጋል። √ ኢየሱስ በቅዱሳት መጽሐፍት ሁሉ ስለ እርሱ የተነገረውን እየጠቀሰ ያስረዳቸው ነበር (27)፥ ቅዱሳት መጻሕፍት አንድ መጽሐፍ ብቻ ናቸው እናም ይህ መጽሐፍ ራሱ ነው፣ ምክንያቱም ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ስለ ክርስቶስ ይናገራሉና በእርሱ ፍፃሜን ያገኛሉ። √ ከእነርሱ እንዳይለይ አጥብቀው…