- 19Jun
የቅዱስ ቁርባን (A-OT-CorpusDomini)
√ ሁሉም ነገር በአንድ ቁራጭ። የቅዱስ ቁርባን ክብረ በዓል በአንድ ቁራጭ ህብስት ውስጥ ሁሉም እንደሚገኝ የሚገልጽ ክብረ በዓል ነው። ምክንያቱም ሁሉም ነገር በአንድ ፍርፋሪ ውስጥ ይገኛል። ሁሉም ነገር እንዲኖር ትንሽ የህብስት ቁራጭ በቂ ነው። > የክርስቶስ ሥጋና ደም ክብረ በዓል ነው። ግን ክርስቶስ ሕያው ነው ወይስ ሞቷል? ክርስቶስ ሕያው ነው። ሥጋውስ ሕያው ነው ወይስ ሞቷል? የክርስቶስ ሥጋ ሕያው ነው (የሞተ ቢሆን አስከሬን ይባል ነበር)። ሥጋው ሕያው ከሆነ ደግሞ ከሥጋው ጋር ነፍስም አለች። ስለዚህ የኢየሱስ ሥጋ ባለበት የኢየሱስ ነፍስም አለች፣ ምክንያቱም ነፍስ ለሥጋ ሕይወት የሚሰጥ ምንጭ ከሆነ፣ ሥጋ ባለበት ነፍስም ደግሞ አለች። > የኢየሱስን ሥጋና ደም ስንቀበል የኢየሱስን ነፍስም እንቀበላለን። ስለዚህ የኢየሱስ ሰብአዊነት በሙሉ (ሥጋ ደምና ነፍስ) በቅዱስ ቁርባን ይገኛል። የኢየሱስ ሰብዓዊነት ደግሞ ከመለኮቱ ፍጹም ተለይቶ አያውቅም፥ የናዝሬቱ ኢየሱስና የእግዚአብሔር ልጅ ሁለት የተለያዩ…
14Jun[K3] An event awaited for centuries: Solar Annular Eclipse, Pyramids and Lalibela
“By the word of the LORD the heavens were made, And by the breath of His mouth all their host” (Psalm 33:6) √ The solar eclipse of June 21 takes place simultaneously with the summer solstice and in alignment with the galactic equator (in the northern hemisphere). It is a unique event, destined not to occur again for hundreds or thousands of years. The schematic study of this majestic stellar event does not cease to surprise: it can be found encoded in the most archaic monuments of the planet: Stonehenge, Giza, Lalibela, Sana’a … √ The megalithic complex of Stonehenge was built in Great Britain, around 3200 BC, at the time when the great pyramids of Egypt were built. The…
14Jun[K3] ለዘመናት የተጠበቀ ክስተት፥ የፀሐይ የቀለበት ግርዶሽ፣ የጊዛ ፒራሚድና ላሊበላ
“እግዚአብሔር ሰማያትን በቃሉ፣ በሰማይ የሚገኙትን ፍጥረቶች በትእዛዙ ፈጠረ” (መዝሙረ ዳዊት 33፥6) √ በሚቀጥለው ሰኔ 14 የሚታይ የፀሐይ ግርዶሽ በዓመት ረጅሙ ቀን ውስጥ (በአስትሮኖሚ መሰረት ይህ ቀን የ summer solstice ሲባል፣ በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ላይ የፀሐይ ጨረሮች ለሰሜን ዋልታ ቅርብ በሚሆኑበት ጊዜ በአመት አንድ ጊዜ የሚከሰት ነው) እና በጋላክቲክ የወገብ መስመር ላይ የሚፈጸም ነው (galactic equator ደግሞ የ Milky Way የወገብ መስመር ነው)። ይህ ክስተት በመቶ ወይም በሺ ለሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ የማይደገም ልዩ ክስተት ነው። የዚህ ታላቅ የሰማይ ክስተት ጥናት አስገራሚ ሆኖ አልቀረም፥ በምድራችን ጥንታዊ ሐውልቶች ውስጥ በምስጢር ተጽፎ የሚገኝ ክስተት ነው፣ በተለይም ከ Stonehenge (UK)፣ ከ Giza (Egypt)፣ ከ Lalibela (Ethiopia) እና ከ Sana’a (Yemen) ጋር ይገናኛል። √ የ Stonehenge የድንጋይ ሐውልት በ Scotland ውስጥ ታላቁ የግብፅ ፒራሚድ በተሠሩበት ዘመን…
12Junቅድስት ስላሴ (A-OT-Trinity)
1ኛ ንባብ፥ ዘጸአት 34፥4-6.8-9 √ “እግዚአብሔር በደመና ወርዶ ከሙሴ ጋር በዚያ ቆመ” (ኦሪት ዘጸአት 34፥5)። እግዚአብሔር በደመና ምስል ይገለጻል። ደመና ግን ጭጋግና ጨለማ ነው፥ ምንም ነገር ማየት አይቻልም። በጭጋግ ውስጥ ግን ምንም ባይታይም፣ ሰው በውስጡ እየኖረ አለማየትን ይለምዳል። ዋናው ነገር ማየት አይደለም፣ አለማየትን መልመድ ነው እንጂ። √ እግዚአብሔር በደመና ምስል ውስጥ ይገለጻል፣ ደመና የመለኮታዊ ጭጋግ ምስል ነው፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር የማይመረመር አምላክ እና የማይታወቅ ምስጢር ነው። በሚገለጽበት ጊዜ በደመና ተደብቆ ምስጢር መሆኑን አይተውም። ይልቁንም ነፍሳችንን በምስጢሩ ያሳትፋል። > እኛ በደመና ውስጥ አናይም እንጂ በደመና ውስጥ እንደገባን እናውቃለን። እግዚአብሔር አይታይም እንጂ ወደ እርሱ ስንቀርብ በመለኮታዊ ደመና እንደገባን እንገነዘባለን። ነገር ግን እግዚአብሔር በሚገለጽበት ጊዜ ምስጢሩን አያስወግድም እንጂ በምስጢሩ ያሳትፈናል። ደመና እግዚአብሔር ምስጢሩን ሳይተው በምስጢሩ እንደሚያሳትፈን የሚገልጽ ምስል ነው። እግዚአብሔር ከእኛ በላይ ነው፥ በእርሱ…
10JunSolemnity of the Body and Blood of Christ
√ The whole in one fragment. The solemnity of the Body and Blood of Christ is the solemnity of the whole in a fragment. Because everything is in a fragment. A particle is enough for everything to be there. > If everything is in a fragment, we will not struggle to take anything away. If we were to keep all the things that existed before us and that will exist after us, we wouldn’t be able to do it. But if everything is in a fragment, we can keep everything in one. > It is the solemnity of the Body and Blood of Christ. But is Christ alive or dead? Alive. And is his Body alive or dead? Alive (if…
05Junየጳራቅሊጦስ (A-PHASIKA-Pentecost)
1ኛ ንባብ፥ የሐዋርያት ሥራ፥ 2,1-11 √ ነፋስ የሚመስለው ድምጽ ቤቱን ሞላው። እሳት ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ አረፈ። ደቀመዛሙርቱም ወደ አደባባይ ወጥተው በተለያዩ ቋንቋዎች የእግዚአብሔርን ቃል መናገር ጀመሩ። √ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል ከመፅነስ በቀር ምንም ሌላ ተልእኮ የለውም። መንፈስ ቅዱስ ልክ በድንግል ማርያም ማህፀን ውስጥ ቃሉን በመፅነስ ልጅ እንድትወልድ እንዳስቻላት፣ አሁንም በሐዋርያት ላይ ራሱን በማፍሰስ በልባቸው ውስጥ ክርስቶስን እንዲፀንሱ፣ በሥራቸውም እርሱን እንዲያፈሩና ለአለም ሁሉ እርሱን እንዲያበስሩም ያስችላቸዋል። “ዝግ በነበረ በላይኛው ክፍል በኩል የገባ መንፈስ፣ ኢየሱስ በተፀነሰበት ጊዜም ዝግ በነበረ በድንግል ማህፀን በኩል የገባ መንፈስ ራሱ ነው” (Gregory the Great †604) የክርስትና ታሪክ እና የዘመናት ይዘት በትክክል የዚህ መለኮታዊ ፅንስና ልደት ማራዘሚያ ነው። የማርያም ሕይወት ፍሬ የኢየሱስ ልደት ነው። አጠቃላይ የቤተክርስቲያን ታሪክ ፍሬ እስከ ዓለም ዳርቻ የሚደርስ ክርስቶስ ነው። ነገር ግን የክርስቶስ ፍጻሜ…