የሦስታኛ አመት 33ኛ እሁድ (C OT-33)

የሦስታኛ አመት 33ኛ እሁድ (C OT-33)

ወንገል፥ ሉቃስ 21፥5-19

ቁ5 “አንዳንድ ሰዎች “ይህ ቤተመቅደስ እንዴት ውብ ነው፣ በከበሩ ድንጋዮችና ለእግዚአብሔር በቀረቡ ስጦታዎች አጊጦአል” እያሉ ይነጋገሩ ነበር”፥ …

ሄሮድስ በአስር ዓመታት ውስጥ በ 100,000 ሠራተኞችና ቅድስተ ቅዱሳንን ለመስራት እንደ ጠራቢ በሰለጠኑት 1,000 ካህናት ተጠቅሞ የገነባው እጅግ አስደናቂ ቤተመቅደስ ነው። በ 20 ዓ.አ የተጀመረው ሥራ  ለረጅም ጊዜ ቀጥሎአል፥ ከመፍረሱ ስድስት ዓመት በፊት በ 64 ዓ.ም ውስጥ ያበቃል።

“በከበሩ ድንጋዮች”፥ በነጭ የኖራ ውብ ድንጋይ ከተሠራ ከጥንታዊው ቤተመቅደስ ምንም አያንስም፥  የክርስቶስ አካል በመስቀል ላይ እንደሚጠፋ ቤተመቅደስም ይፈርሳል። የአዲሱ ቤተመቅደስ የማዕዘን ድንጋይ የተሰቀለ ክርስቶስ ነው። ወደ ጌታችን ቀርበው እንደ ህያው ድንጋይ ደቀመዛሙርቱ ለአዲሱ መንፈሳዊ ቤተመቅደስ ግንባታ ተቀጥረዋል (1ኛ ጴጥሮስ 2፥4)።

ቁ8 ደቀመዛምርቱ ኢየሩሳሌም እንደምትጠፋ በሰሙ ጊዜ ይህንን ክስተት የሚያውጅ ምልክት የትኛው እንደሆነ ይጠይቁታል። ኢየሱስ በማስጠንቀቅ ይመልስላቸዋል፥ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ” ምንም ማስጠንቀቂያ አትጠብቁ፣ ሐሰተኛ ነብያት እንዳያታልሉአችሁ አትፍቀዱ፣ ብቻ ለኔ ታማኝ ሁኑ።

ቁ17 “ስለ ስሜ በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ”፥ …

“ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደጠላኝ ዕወቁ” (ዮሐ 15፥18)። የዓለም ስላልሆንን ዓለም ይጠላናል፣ ዓለምን መውደድ እግዚአብሔርን መጥላት እንደሆነም እናውቃለን (ያዕቆብ 4፥4)።

ቁ19 “በመታገሣችሁም ነፍሳችሁን ታገኛላችሁ”፥ …

ትዕግሥት ደቀመዛሙርቱን ከሞትና ትንሳኤ ምስጢር ጋር ያመሳስላል፥ ህይወቱን የሚያጣ ህይወት ያገኛል (9፥24)። ደቀመዝሙር በሰማዕትነት አማካይነት ሞቶ ከተነሳው ኢየሱስ ዘንድ ማንነቱን ያገኛል።

1ኛ ንባብ ሚልክያስ 3፥19-20

ቁ19 “ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች”፥ …

“ስለዚህም በፀሐይ ላይ እምነት አትጣል። እሱ የአለም ዐይን፣ የዕለቱ ደስታ፣ የሰማይና የተፈጥሮ ውበት መሆኑ እውነት ነው። ሲያደንቅህ ለፈጣሪው መስጋናን አቅርብ። ፀሐይ በጣም ደስ የሚያሰኝ ከሆነ፣ በጽድቅ ፀሐይ ውስጥ ሊገኝ የሚችል ቸርነት ምን ያህል ነው? ፀሐይ ፈጣን በመሆንዋ በቀንና በሌሊት በፍጥነት ሁሉንም ነገር ማለፍ ከቻለች፣ ሁልጊዜና በሁሉም ቦታ ይሚኖርና ሁሉን ፍጡራን በክብሩ የሚሞላ አምላክ እንዴት ታላቅ ነው!” (AMBROSE)

“ስለዚህ” በጨለማ ፍጹም እንዳትመላልስ” እና የመጨረሻው ቀን ጨለማ ውስጥ እንዳያገኝህ፣ ብርሃን ለአንተ ወደሚወለድበት፣ “የጽድቅ ፀሐይ” ወደምትወጣበት ቦታ ወደ “ምስራቅ” ሁልጊዜ እንድትመለከት ትጋበዛለህ። እውቀት በሚሰጥ ብርሃን በመገኘትህ፣ ሁልጊዜም የእምነት ቀን ይብራልህና ሁልጊዜም የፍቅርና የሰላም ብርሀን ይጠብቅህ” (ORIGEN)

አጭር ትምህርት

ኢየሱስ በትንቢት የተናገረው ራእይ ከአስር ዓመት በፊት ቶሎ የሚከሰት አይመስልም ነበር። በተቃራኒው ዛሬ በዓይናችን ስር በየቀኑ እየተፈጸመ ያለውን ነገር፣ የክርስቶስን ተቃዋሚ ኃይል ቃል በቃል ያረጋግጣል!

– ከቤተክርስቲያን ውጭ፣ በዓለም ውስጥ፥

= “በglobal” ዓለም ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ብዝበዛና ፖለቲካዊ የበላይነት፣ በጦር ሐይልና በታላቅ ገንዘብ ተቋማት አማካይነት በሕዝቦች መካከል የሚካሄዱ ጦርነቶች፣ የሰው ልጅ አዕምሮና ባህል ማምታታትና መግዛት ይታያል (“ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳል”)።

= የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች እየበዙ ናቸው (“በየቦታው ብርቱ የምድር መናወጥ ይሆናል”) እና ወደፊት የሚመጡ ሌሎች አደጋዎችም ሪፖርት እየተደረጉ ናቸው። ጎርፍና እሳት መሬት ውስጥ ያሉትም የእሳተ ገሞራ እንቅስቃሴዎች እየተስፋፉ ነው።

= ድሮ በተወሰኑ አካባቢዎች ብቻ የነበረ “ረሃብና በሽታ” ባደጉት አገራት ውስጥ እንኳን ሳይቀር እየታየ ነው።

= በማህበርና በቤት ኑሮ ውስጥ “የሚያስፈራሩ ነገሮች” ባልተጠበቀ መጠን በቁጥርና በጭካኔ ጨምረዋል፣ (ቤት ውስጥ የሚፈጸም ወንጀል፣ መንገዶች ላይ፣ በሕዝብ ትራንስፖርት ላይ፣ በሴቶችና በልጆች ላይ የሚፈጸም ጥቃት፣ የእርስ በእርስ ጦርነት፣ ሰይጣናዊ የወንጀል አፈጻጸም)

= “በሰማይ የሚታዩ ታላላቅ ምልክቶች” አሁንም መታየት አለባቸው፣ ነገር ግን እንደ ኢየሱስ ትንቢት ከሆነና በድሮ ዘመናትና በቅርብ ጊዜ እንደተገለጹ ምልክቶች ከሆነ ምናልባት አይዘገዩም።

– ግን በጣም የሚያሳስበን ነገር በቤተክርስቲያን ውስጥ ሲከሰት የምናየው ነገር ነው። እርስዋም ጴጥሮስ በካደበት (“እውነት እልሃለሁ፥ በዚች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ማቴዎስ 26፥34)፣ ኢየሱስ በታሰረበት፣ ሐዋሪያትና ደቀመዛሙርት በፈሩና በተደበቁበት (“በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ” ማቴዎስ 26፥56)፣ ዶሮ በጮኸበትና ጌታን በመካዱ ምክንያት ጴጥሮስ ባፈሰሰበት ዕምባ ጊዜ ውስጥ (“ወዲያውም ዶሮ ጮኸ። ጴጥሮስም ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ብሎ ኢየሱስ የተናገረው ቃል ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጣና ምርር ብሎ አለቀሰ” ማቴዎስ 26፥75) ዳግም የምትኖር ትመስላለች።

ሁላችንም ይህንን በመጠባበቅ ላይ ነን። ጊዜ ግን ያስፈልጋል ምክንያቱም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተጻፉ ትምቢቶች መፈጸም አለባቸው። ስደት ሁለት ዓይነት ሊሆን ይችላል፥

= ዛሬ በመካከለኛ ምስራቅ፣ በአፍሪካ፣ በቻይናና በሌሎችም ስፍራዎች በብዙ አብያተ ክርስቲያናት ሰማዕታት ላይ እየደርስባቸው አካላዊ ሁከት ነው (“ሰዎች እናንተን ይይዙአችኋል፣ ያሳድዱአችኋል፣ ወደ ምኵራብና ወደ ወኅኒ ቤት አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ስለ ስሜም ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎችም ይወስዱአችኋል” ሉቃስ 21፥12)

= የጓደኛሞች፣ በቤት ውስጥ ያሉት፣ በአንድ ገዳም ውስጥ የሚኖሩት ወንድማሞችና እህትማሞች እርስ በእርስ ግንኙነቶች ይበልጥ አስቸጋሪ ሆኖአል  (የዘመናችንን ክስተቶች ማመዛዘን ስለማይችሉ አይረዱምና አያስተውሉም) መግባባት ከባድ በሚያደርግ አእምሯዊና አስተሳሰብ መልክ (“ወላጆቻችሁም ወንድሞቻችሁ ዘመዶቻችሁና ወዳጆቻችሁም ሳይቀሩ አሳልፈው ይሰጡአችኋል”      ሉቃስ 21፥16)። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ዋና ነገር ለተስፋፋው አለማዊ አስተሳሰብ ረሱን የማይሸጥ ሰው ምስክርነት ነው (“ይህም ለምስክርነት መልካም አጋጣሚ ይሆንላችኋል” ሉቃስ 21፥13)፥ ይህም የዘመናችንን ሁኔታ ለሚገነዘቡና የጋራ እምነት ላላቸው ወንድማሞች ድጋፍ የሚሰጥ ምስክርነት ነው። ሌሎቹም በችልታም ይሁን ባለማወቅም አያስተውሉምና ለእነርሱም መጸለይ ያስፈልጋል (“አንድ ሰው ከሙታንም እንኳ ቢነሣ አያምኑም” ሉቃስ 16፥31)።

ዛሬ በአይናችን የምናየው በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚካሄደው ጥፋት ነው። እኛ በጣም እንድንሠቃይ የሚያደርገን ይህ ነው፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት ደረጃ ይደርሳል ብለን አልጠበቅነውም (“ይህ የምታዩት ሁሉ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተነባብሮ የማይቀርበት ጊዜ ይደርሳል” ሉቃስ 21፥6)። ዛሬ የመሠረተ-ትምህርት ድንጋይ፣ የምስጥራት ድንጋዮች፣ ከሁለት ሺህ ዓመታት በላይ የተገነባ ሕንፃ የመፍረስ ትያቄ ደርሶአል (“አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ” ማቴዎስ 16፥18)። ነገር ግን “የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም” (ማቴዎስ 16፥18) ምክንያቱም “የማዕዘን ድንጋይ” ክርስቶስ ራሱ ነው፥ እርሱም በራሱ ጊዜ በማሸነፍ ሁኔታውን ያድሳል።

የቤተክርስቲያን እናት ማርያም ሆይ፣ የአለምና የታሪክ ጌታ የኢየሱስ ክርስቶስስ ድል የሚታወጅበትን ጊዜ እንድታፋጥኚ እንጠይቅሻለን።

Leave a reply