- 23Feb
“ከመካከላችን አንድ አሥር ሰዎች ቅዱስ ሕይወት ብንመራ፣ ከተማውን ሁሉ የሚያበራ መብራት እናበራ ነበር” (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
18Febየሃይማኖት ብዛት በእግዚአብሔር ፈቃድ (ሊቀ ጳጳሱ ፍራንሲስ)
“የሃይማኖቶች የከለር የፆታ የዘር እና የቋንቋ ብዛት በእግዚኣብሄር ጥበብ የተፈቀደ ሁኔታ ነው”። ይህ መግለጫ ባለፈው የካቲት 4 በአቡ ዳቢ (ኤሚሬትስ) ፍራንሲስ እና የአል-አህዛር ታላቁ ኢማም በፈራረሙት ስምምነት ላይ የሚገኝ ነው። በዘፍጥረት ምዕራፍ 11 የተጻፈው ግን እግዚአብሔር የቋንቋ መለያየትን እንደ ኃጢአት ቅጣት አድርጎ እንደፈቀደ ነው። ፍራንሲስ ሰዎችን እነደ መሥዋዕት የሚያርዱትን ሀይማኖቶች የእግዚአብሔር ፈቃድ አድርገው ይቆጥሯቸዋል ማለት ነው። ስላሴንና የክርስቶስን መለኮትነት የሚቃረኑትን እስልምና ወይም ይሁዲነት የእግዚአብሔር ፈቃድ አድርገው ይቆጥሯቸዋል። እግዚአብሔር እርስ በራሳቸው የሚቃረኑትን ሃይማኖቶች ከፈቀደ፣ የፍራንሲስ አምላክ ሁለት ተቃራኒ አስተያየት ይደግፋል ማለት ነው። ልክ እንደ ሰይጣን እውነትንና የእውነት ተቃራኒ ይፈልጋል፥ በእርግጥ ሰይጣን የውሸት መርህ ነው። ከኤሚሬትስ ሲመለሱ በበረራ ላይ በሚደረገው የጋዜጠኞች ጉባኤ ፍራንሲስ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፥ “ከካቶሊክ አመለካከት አንፃር የፈረምነው ስምምነት ከሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ አንድ ሚሊሜትር እንኳን አልተንቀሳቀሰም። ይህ ሰነድ የተፈረመ በሁለተኛ…
18Febሁለት ቤተክርስቲያናት ሊኖሩ ይችላሉ
እኛ የዓመፅ ምሥጢር (2ኛ ወደ ተሰሎንቄ 2፡7) አሁንም በስራ ላይ እንደሆነ እናውቃለን፣ ነገር ግን የኃይሉን ሙሉ መጠን አናውቀውም። በእይታ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን በጠላትዋ ድል ልትደረግ እንደምትችል አምኖ መቀበል ምንም ችግር የለውም፣ በዚህም ምክንያት ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን መለወጥ እንደምትችል እናውቃለን። ሁለት ቤተክርስቲያናት ሊኖሩ ይችላሉ፥ አንደኛይቱ በይፋዊ እይታ ለይ ያለች፣ በአለም ሚድያ ፕሮፓጋንዳ በሐሰት ክብር የተጋነነች ቤተክርስቲያን ናት (ሌላው ቀርቶ አሻሚ የሆኑ አመለካከቶች ያሉት ጳጳስ ሊኖራት ይችላል)፤ ሌላዋ ደግሞ ለኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ የሆነ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ያላት፣ ከአንዳንድ ታማኝ ካህናትና አማኞች ጋር በምድር ዙሪያ እንደ ትንሽ መንጋ የተበታተነች፣ የዝምታ ቤተክርስቲያን ናት። ይህች ሁለተኛይቱ ቤተክርስቲያን የተስፋው ቃል የምትወርስ ነች፣ የመጀመርያ ግን ከሀዲ ናት። ሁለቱም ቤተክርስቲያናት በአንድ ጳጳስ ሊመሩ ስለሚችሉ አንድ አካል ይመስሉ ይሆናል። አሻሚ የሆኑ አመለካከቶች ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት…
18Decለምን የከሪት እንጀራ?
“ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምስራቅ ሂድ” (1 ነገሥት 17፡2-7)። ምስራቅ ክርስቶስ ማለት ነው ወይም ደግሞ በመጀመሪያ የነበረ ወይም መነሻው ነው። ኤልያስ ወደ ክርስቶስ ዘወር ይላል፣ በተመሳሳይ ጊዜ ግን ወደ መነሻውም ይመለሳል። የትኛው መነሻ? በእውነቱ የከሪት ወንዝ በአብርሃምና በያዕቆብ ታሪክ ውስጥ የተከናወኑትን የመጀመርያ ክስተቶች ከሚያመለክቱ ወንዞች ከያርሙክና ከያቦቅ ወንዝ አጠገብ ይገኛል። የወንዝ ውሃም፣ ቁራዎቹ የሚያመጡ ሥጋና ዳቦ ደግሞ የሙሴን ታሪክ የሚያመለክቱ ምሳሌዎች ናቸው። እንዲያውም በምድረ በዳ ውስጥ እስራኤላዊያን ከዓለት የሚፈልቅ ውሃ ይጠጡና ከሰማይ በወረደ እንጀራና ሥጋ ይመገቡ ነበረ። ስለዚህ ኤልያስ የተባለው ማለት “ከዚህ ተነሥተህ ወደ መጀመሪያህና ወደ መነሻህ ሂድ” ማለት ነው። በኤልያስ ሕይወት ውስጥ እንዲህ ባለ አሳዛኝ ወቅት፣ ምግብና ዉሃ የእግዚያብሔር ፍቅር ምልክቶች ናቸው። “ከሪት ተብሎ በሚጠራው ሸለቆ ተሸሸግ”። እግዚያብሔር ኤልያስን ይሸሽጋል፣ ኤልያስ የእግዚያብሔር ሰው ነው፣ በርሱ ብቻ የእግዚያብሔር ቃል ይስተጋባል፣ ነገር…

መግቢያ - Entrance
1 ነገሥት 17፡2-7 ያንብቡ፥ የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት ስላልፈለገ፣ እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያሰን ወደ በረሀ ሄዶ በምስጥራዊ ቦታ እንዲሸሸግ ነገረው። በዚህ ምክንያት ሁለት ተቃራኒ ሁኔታዎችን ማነፃፀር እንችላለን፥ በአንድ በኩል የእግዚአብሔርን ድምጽ ያጣው ሕዝብ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በከሪት ሽለቆ ከእግዚአብሔር ቀጥተኛ መመሪያ እና ምግብ የሚቀበል ነቢይ። ስለዚህ የእግዚአብሔር ድምፅ አሁንም ድረስ ወደሚሰማበት ምስጥራዊ ሸለቆ እንግባ።

የታችኛው ክፍል - Lower Room
በዚህ ክፍል ውስጥ ከማህበራዊ ጉዳይና ከዓለም አቀፍ መስተዳደር ጉዳዮች ጀምሬ በመጽሐፍ ቅዱስ እና በጥንታዊ የክርስቲያን ትምህርት በመሞርክስ፣ አንዳንድ ወሳኝ ግንዛቤዎች አቀርብላችኋለሁ። የሐዋርያውን ጳውሎስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ያንብቡ፥ “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ” (ወደ ሮሜ ሰዎች - ምዕራፍ 12፡2)።

የላይኛው ክፍል - Upper Room
አሁን ባለን ታሪክ ውስጥ ጣዕሙን እንዳጣ ጨው ሆነው የተወሰኑ ክርስቲያን አማኞች እና በተለይ መሪዎች የዚህን ዓለም አካሄድ ለመከተል ከፍተኛ ጉጉት ያድርባቸዋል። ለሰርዴስ መልአክ የተሰጠውን ምክር ያስታውሱ፥ “የነቃህ ሁን፣ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና” (የዮሐንስ ራእይ - ምዕራፍ 3፡2)። ክርስቶስ ቀርቦአል፣ ሲመጣም ከጓደኞቹ ቁጥር መገኘት እንፈልጋለን።

የውኃ ጉድጓድ - Water Well
ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈጽሞ በማይደርቁ ጥንታዊ ምንጮች አጠገብ አርፌ ማታደስን አገኛለሁ። “ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?” (መዝሙረ ዳዊት - ምዕራፍ 42)። ቀጣዮቹ ገጾች ክርስቶስን ለመማረክ ማንኛውንም ነገር ለመተው ከመረጡ ከዛሬና ትላንት አማኞች ልብ ይወጣሉ።

እንጀራ ቤት - Kitchen
እና እዚህ ደረስን። የክርስቶስ ወዳጅ ከምድራዊ ደስታ አይገለልም። “እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና ሂድ፥ እንጀራህን በደስታ ብላ፥ የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ” (መጽሐፈ መክብብ - ምዕራፍ 9፡7)። በእግዚአብሔር እይታ መሠረት የሚኖሩት ሰዎች የዝናን የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ ይሰማቸዋል።