- 20Apr
የቤኔዲክት መድሃኒት፥ ወደ እግዚአብሔር መመለስና ቅዱስ ቁርባንን መከላከል
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት ፲፮ በቅርብ ጊዜ ከጻፉት ማስታወሻዎች አጫጭር ትርጓሜን አቀርብላችኋለሁ። እዚህ ላይ የርሳቸው ፅሑፍ ሙሉ በሙሉ ማንበብ ትችላላችሁ (here)። ቤኔዲክት ፲፮ በተለያዩ የአሜሪካና የጀርመን ገዳማት ውስጥ የግብረሰዶማውያን ክለቦች የሚሰሩ እንደነበረና ቤት ውስጥ ተጽዕኖ ያደርጉ እንደነበረ ይገልፃሉ። “ምን መደረግ አለበት? ለዚህ መፍትሔ ሌላ ቤተክርስቲያን መፍጠር አለብን ወይ? በሰው ልጅ ታሪክ እንዲህ አይነት ሙከራ አስቀድሞ ተካሄዶ ነበረ፣ ግን ስኬታማ አልሆነም። ይልቁንስ መንገዱን ሊያሳየን የሚችል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማፍቀርና ለርሱ ብቻ መታዘዝ ነው…” “በዘመናችን ባለው የሥነምግባር ውድቀት ላይ ዋነኛው ተግባራችን ለእርሱ ብቻ በመኖር ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን የሕይወታችን መሰረት ለማድረግ እንደገና መማር ነው። እኛ ግን በተደጋጋሚ ጊዜ ፍሬ እንደሌለው ቃል አድርገነው እግዚአብሔርን ጥለን እንሄዳለን። ስልክርስቶስ ስናጠና ክርስቶስ ራሱ የአስተሳሰባችን፣ የቃላታችንና የድርጊቶቻችን ምንጭ ካልሆነ፣ በስተጀርባውን የምንተው ጥላ ይሆናል…” “ስለዚህ ምን አይነት እርምጃ…
13Aprየተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ አውጥተዋል፥ የሰው ዘር ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ ነው
ይህ አጀንዳ ዓለምን የሚያቅፍ አምባገነናዊ መንግሥት (New World Order) መጀመሪያው ይፋዊ አዋጅ ሊባል ይችላል። ይህ አዲስ አጀንዳ ሙሉ በሙሉ የሰው ዘር እንቅስቃሴዎችን ያካትታል። በመጀመሪያ ሲታይ ይህ አጀንዳ እያንዳንዱን ከባድ ችግር በአለምአቀፍ ደረጃ ላይ የሚታገል ይመስላል። እስከ ዛሬ ድረስ ድህነትን ለማስወገድ በይፋ የሞከረ ሰው እንዳልኖረ ያስመስላል። ይህ ደግሞ ሌላ ጥያቄ ያስነሳል፥ ተሳታፊ ላለመሆን ለሚወስኑት አገሮች ምን ይሆናል? ድህነትን ከሚያስወግደው አለምአቀፋዊ እቅድ ነጻ ይሆናሉ ወይ? በእነዚህ ዓለም አቀፋዊ ግቦች ላይ ለተመለከቱ ብዙዎቹ በጣም ጥሩ ይመስላሉ። ለመሆኑ ረሃብን ማቆም የማይፈልግስ ማን አለ? ዋናው ቁም ነገር ከቋንቋው በስተጀርባ ያለውን ማየትና ምን እየተባለ እንዳለ መረዳት ነው። በእውነት እየተባለ ያለው ደግሞ ዓለምን የሚቆጣጠሩ ሀይሎች የአንድ ዓለም መንግሥት ሕልማቸውን ወደ ቀጣዩ ደረጃ መውሰድ እንደሚፈልጉ ነው። የ2030 አጀንዳ ድብቅ ዓላማ አላማ 1፥ ድህነትን በሁሉም ቦታ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት…
20Marአድሜ ለአፍሪካ ተወካዮች፣ የተባበሩት መንግስታት ኮሚሽን ፅንስ ማስወረድና ሰዶማዊነትን የሚደግፈውን ውሳኔ ሊተው ነው
ሰዶማዊነትን የሚደግፈውን ውሳኔ ይጠበቅ ነበረ። ነገር ግን ባለፈው የካቲት መጨረሻ በተደመደመው የተባበሩት መንግስታት ማህበራዊ እድገት ኮሚሽን ፅንስ ስለ ማስወረድና ሰዶማዊነትን በተመለከተው ጉዳይ ምንም ፍንጭ እንኳን አልሰጠም። እንዲሆም የኮሚሽኑ የመጨረሻው ስምምነት “የወሲብና የስነ ተዋልዶ ጤና” የሚሉትን ቃላት ትቶ የቤተሰብን ብልጽግና የሚደግፉ መመሪያዎችን አካቶአል። በምላሽ የውርጃ ደጋፊ የሆነኑት የሜክሲኮ ተወካይ “ከመካከለኛ ዘመን ለመውጣት ያግዱናል” በማለት የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ተወካዮችን ወቅሰዋል። እንደሚታወቀው በተባበሩት መንግስታት አነጋገር “የወሲብና የስነ ተዋልዶ ጤና” (sexual and reproductive health) ማለት ፅንስ ማስወገድን ማመቻቸት እንደ ማለት ነው። የአፍሪካ አገራት በመወከል የጂቡቲ ተወካይ “ቤተሰብ በማህበራዊ እድገት ውስጥ መሠረታዊ ሚና ይጫወታል፤ ቤተሰቦችን የሚደግፉት ፖሊሲዎች ማህበራዊ እኩልነትን ለማሳደግና ድህነትን ለማስወገድ ይረዳሉ” በማለት የኮሚሽን ስምምነት መልካም ገጽታዎችን ጎላ አድርገው ገልጸዋል። በቅርብ ዓመታት ውስጥም የተባበሩት መንግስታት ማህበራዊ እድገት ኮሚሽን “ብዙ አይነት ቤተሰብ አለ” በሚል አስተያየት…
20Marከየትኛው ፕላኔት?
እንደሚታወቀው፣ ቫቲካን እና የቻይና መንግስት የጋራ ትብብር ታሪካዊ ስምምነት ተፈራርመዋል። ነገር ግን የሆንግ ኮንግ (Hong Kong) ጳጳስ የነበሩ ካርዲናል ዘን (Zen) እንደሚሉት ከሆነ፣ ስምምነቱ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ለጠላቶችዋ አሳልፎ የሚሰጥ ነው። ለእውነተኛ እምነት ታማኝ ሆነው የቀሩት አማኞች በአባታቸው እጅ እንደተሰደዱ ይሰማቸዋል። የተፈረመው ስምምነት “እውነትን ይደብቃል፥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ እና ቤኔዲክቶስ ሁልጊዜ እንዳስቀመጡት፣ እኛ አለን፣ እነርሱም አሉ፣ እኛና እነርሱ በፍጹም መስማማት አንችልም። እኛና እነርሱ የሚል ሁኔታ ያለፈ ታሪክ አይደለም፣ ዛሬም ያለ ታሪክ ነው። ይህን ሁኔታ ሊያጠፋ የሚችል አስማተኛ የለም። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ይህን በሚገባ ያውቃሉ። ካልሆነ እርሳቸው በሰዓታት ጸሎት ጠዋት ጠዋት የምናነበው “ሕዝቡን በምሕረት ስለ ጎበኘና ስላዳነ የእስራኤል አምላክ ጌታ ይመስገን… ከጠላቶቻችንና ከሚጠሉን እጅ አድኖናል” የሚሉትን የዘካርያስ ቃላት ማስወገድ ይኖርባቸዋል። ማታ ማታ የምናነበውም የማርያም መዝሙር እንዲህ ይላል፥ “በብርቱ ክንዱ ኃይሉን አሳይቶአል፤…
0 comments Read more10Mar24Feb“ህብስትና ወይን ጠጅ ከተቀደሱ በኋላ፣ እግዚአብሔር በመንግሥተሰማይ እንዳለ እዚህም ነው። ሰው ይህን ቢረዳ ኖሮ በፍቅር ይሞት ነበር” (Benedict XVI)
23Feb23Febዘወትር በስውር እንደተመኙት መልስ
“ሰዎች በቃላት ሊገለጽ በማይችል ብቸኝነት ውስጥ የሚኖሩ መሆናቸውን ይገነዘቡና የድህነታቸውን ፍርሃት ከተሰማቸው በኋላ፣ ልክ እንደ አዲስ ነገር ሆኖ ለክርስቶስ ታማኝ የሆነውን ያማኞች ታናሽ መንጋ ያገኛሉ፥ እርሱንም ዘወትር በልባቸው እንደተመኙት የውሃ ምንጭ የራሳቸውን ተስፋ አድርገው ያገኙታል” (Benedict XVI)
23Febየመንፈስ ኃይል
“ዛሬ ራስን መቻል ይባላል፣ በጥንት ዘመን የመንፈስ ኃይል ተብሎ ይጠራ ነበር፣ ፕላቶ መኖሪያዋ በሰው ልብ ውስጥ እንደነበረ ብሎ ፅፎአል፣ ልብ የስሜት ተምሳሌት ነው። ስሜት ግን ድክመት አይደለም፣ የነፍስ መጽናናትን የማያገኝ ሐዘንም አይደለም። ስሜት ድፍረት ነው። ስሜት ሁሉን ጥቅሞችና መሰናክሎች ካመዛዘንን በኋላ በእያንዳንዳችን ውሳኔ መነሻ ላይ የምናውቀው ድፍረት ነው። በጥቅም ወይም በድክመት ምክንያት የራሳችን ያልሆነ ውሳኔ ብናደርግ ግን ወዮልን! በራሳችን ሕይወት የውጭ ዜጋ ሆነን ከቀረን ወዮልን! ቤታችን! የመንፈስ ኃይል በራሳችን ቤት ውስጥ የውጭ ዜጋ ከመሆን ይጠብቀናል፣ ከራሳችን ጋር እና የቤታችን ነዋሪዎች መሆናችን እንዲሰማን ያደርጋል። ከራሳችን ጋር ተመሳሳይ የሚያደርገን የአእምሮ ጤንነት እዚህ አለ” (Romano Guardini 1885-1968)

መግቢያ - Entrance
1 ነገሥት 17፡2-7 ያንብቡ፥ የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት ስላልፈለገ፣ እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያሰን ወደ በረሀ ሄዶ በምስጥራዊ ቦታ እንዲሸሸግ ነገረው። በዚህ ምክንያት ሁለት ተቃራኒ ሁኔታዎችን ማነፃፀር እንችላለን፥ በአንድ በኩል የእግዚአብሔርን ድምጽ ያጣው ሕዝብ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በከሪት ሽለቆ ከእግዚአብሔር ቀጥተኛ መመሪያ እና ምግብ የሚቀበል ነቢይ። ስለዚህ የእግዚአብሔር ድምፅ አሁንም ድረስ ወደሚሰማበት ምስጥራዊ ሸለቆ እንግባ።

የታችኛው ክፍል - Lower Room
በዚህ ክፍል ውስጥ ከማህበራዊ ጉዳይና ከዓለም አቀፍ መስተዳደር ጉዳዮች ጀምሬ በመጽሐፍ ቅዱስ እና በጥንታዊ የክርስቲያን ትምህርት በመሞርክስ፣ አንዳንድ ወሳኝ ግንዛቤዎች አቀርብላችኋለሁ። የሐዋርያውን ጳውሎስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ያንብቡ፥ “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ” (ወደ ሮሜ ሰዎች - ምዕራፍ 12፡2)።

የላይኛው ክፍል - Upper Room
አሁን ባለን ታሪክ ውስጥ ጣዕሙን እንዳጣ ጨው ሆነው የተወሰኑ ክርስቲያን አማኞች እና በተለይ መሪዎች የዚህን ዓለም አካሄድ ለመከተል ከፍተኛ ጉጉት ያድርባቸዋል። ለሰርዴስ መልአክ የተሰጠውን ምክር ያስታውሱ፥ “የነቃህ ሁን፣ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና” (የዮሐንስ ራእይ - ምዕራፍ 3፡2)። ክርስቶስ ቀርቦአል፣ ሲመጣም ከጓደኞቹ ቁጥር መገኘት እንፈልጋለን።

የውኃ ጉድጓድ - Water Well
ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈጽሞ በማይደርቁ ጥንታዊ ምንጮች አጠገብ አርፌ ማታደስን አገኛለሁ። “ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?” (መዝሙረ ዳዊት - ምዕራፍ 42)። ቀጣዮቹ ገጾች ክርስቶስን ለመማረክ ማንኛውንም ነገር ለመተው ከመረጡ ከዛሬና ትላንት አማኞች ልብ ይወጣሉ።

እንጀራ ቤት - Kitchen
እና እዚህ ደረስን። የክርስቶስ ወዳጅ ከምድራዊ ደስታ አይገለልም። “እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና ሂድ፥ እንጀራህን በደስታ ብላ፥ የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ” (መጽሐፈ መክብብ - ምዕራፍ 9፡7)። በእግዚአብሔር እይታ መሠረት የሚኖሩት ሰዎች የዝናን የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ ይሰማቸዋል።