- 08Oct
ቤታችን በእሳት ላይ አይደለም
በCO2 እና በአየር ብክለት መካከል ውስጥ ያለው ግንኙነት ምንድነው? CO2 ከአየር ብክለት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ደግሞ በአየር ንብረት ውስጥ የCO2 ብዛትና የሙቀት መጠን ግንኙነት እንዳላቸው የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማረጋገቻ የለም። እንዲያውም ባለፉት 5000 ዓመታት ውስጥ በአየር ንብረት ውስጥ አነስተኛ የCO2 መጠን ሲኖር ትልቅ የሙቀት ለውጥ ተመዝግበዋል። እውነት ለመናገር በምድር ላይ ያለው ሙቀት እየጨመረ መምጣቱ እውነት ነውን? የሰው ስራ በነዚህ ለውጦችላይ ምን ያህል ተጽዕኖ ያሳድራል? በ1400 ዓ.ም. አካባቢ ሳይንቲስቶች “የበረዶ አነስተኛ ዘመን” ብለው የጠሩት የብርድ ዘመን ነበር። ከ1400 እስከ 1700 ዓ.ም. ድረስ የሙቀት መጠን እየወረደ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን በ1700 ተመዝግቦአል። ከ1700 ዓ.ም. ጀምሮ በምድር ላይ ያለው የሙቀት መጠን ደጋሚ ወደ ላይ ከፍ ማለት ጀምሮአል። ይህ የሚያመለክተው የተፈጥሮ የአየር ንብረት ስርዓት በአሁኑ ጊዜ “በሙቀት” ደረጃ ላይ መሆኑን ነው። ሆኖም፣ አሁንም ቢሆን…
28Sepየክርስቶስ ተቃዋሚ ትምህርት
የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አዲስ ፈጠራ ሳይታይ አልፎአል። ርዕሱ “ዓለም አቀፉን የትምህርት ስምምነት እንደገና መገንባት” የሚል፣ “ከሁሉም አለምና ከሁሉም ሃይማኖት በትምህርት መስክ ውስጥ የሚሳተፉትን የህዝብ ቁጥሮች” ይጋብዛል። በጣም የሚያስደንቀው ነገር ቢኖር፣ በዚህ ትምህርታዊ ስምምነት አጠቃላይ የክርስቲያን መለያ ምልክት አለመኖር ነው። ፍራንሲስ ስምምነቱን በሚያቀርቡበት የቪዲዮ መልእክት ውስጥ፣ የእግዚአብሔርም ሆነ የኢየሱስና የቤተክርስቲያን ዱካ የለውም። ዋነኛው የስምምነቱ ቅመር “አዲስ ሰብአዊነት” “የጋራ ቤት” “ሁለንተናዊ አንድነት” “ብልጽግና” “ትብብር” እና “ተቀባይነት” የሚሉ ናቸው። እና ሀይማኖቶችስ? እነሱም ባልተለየ “ምልልስ” ውስጥ ተቀላቅለው የቀሩ ናቸው። “የመድልዎ ቦታን ለማፅዳት”፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት “የሰው ወንድማማችነት” የሚለውን በየካቲት 4 2019 (EC) ከአል-አዝሀር ታላቁ ኢማም ጋር የተፈራረሙትን ሰነድ ያስታውሳሉ። ሰነዱ “የሃይማኖት ብዛትና ልዩነት” በ“መለኮታዊ የእግዚአብሔር ጥበብና ፈቃድ” ይመሰረታል በማለት ይገልጻል። በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አንድ የሮማ ሊቀጳጳስ እንዲሀ ሆኖ አለማዊ የትምህርት ስምምነት የራሳቸውን አድርገው…
24Sepባለፈው ሰኔ ወር ውስጥ ለአንድ ትልቅ የምዕራብ አገር ፓርላማ የአየር ንብረት ለውጥ (global warming) ምክንያት ሰው መሆኑ የመንደር አፈታሪክ ነው ብሎ የሚከራከር አቤቱታ ተልኳል። አቤቱታው ከፍተኛ እውቀት ባላቸው በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 200 የሳይንስ ሊቃውንት ተፈርሞአል። ሰነዱ የሚከተለውን ይገልጻል፥ ከ1950 እስከ 2000 ባነበሩት ዓመታት የታየው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ አስደንጋጭ ጉዳይ አይደለም፥ ቀደም ብለው በነበሩት ጊዜያት ይበልጥ ሞቀታማ ወቅቶች ተከስተዋል። ደግሞም ከ2000 ጀምሮ እስከ ዛሬ በምድር ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ቆሞአል። የአየር CO2 ማደግ የጀመረው ከፍተኛ ሰው ሰራሽ ልቀቶች ከመኖራቸው በፊት ነው (ማለትም ከ 1700ዎቹ ዓመታት በኋላ ከተጠቀሰው የአየር ልውጥ ጋር ተያይዞ ነው)። በተቃራኒው በኢንዱስትሪ ዘመን በአየር ንብረት ውስጥ የተከሰተው የCO2 ጭማሪ በአለም አቀፍ አማካይ የሙቀት መጠን ላይ ፋይዳ የለውም (የCO2 ክምችትና የሙቀት መጠን ተመጣጥነው አያድጉም)። የCO2 መጨመር በዓለም አቀፍ ዕፅዋት…
21Sepጌታችን ሆይ፣ ስለ እኛ ሳይሆን፣ ስለስምህ ክብር ይሁን። (መዝሙረ ዳዊት)
ጌታችን ሆይ፣ ስለ እኛ ሳይሆን፣ ስለስምህ ክብር ይሁን። (መዝሙረ ዳዊት) ስለሚያቃጥለን ፀሐይ፣ ስለሚያርሰን ዝናብ፣ እንከን የለሽ ስለሆነው የጀግኖች ትግል፣ እናመሰግንሀለን። ስለሚያሠቃየን ረሀብ፣ ስለሚያደርቀን ጥማት፣ እጅና እግር ሲዳከም፣ እናመሰግንሀለን። ስለሚያሳውረን ነፋስ፣ ስለሚያነደን አሸዋ፣ በጭቃ ውስጥ ስለፈሰሰ ደማችን፣ እናመሰግንሀለን። በውጊያ እያለን እንቅልፍ ባጣን ሌሊት፣ ልብን በእውነተኛ ደስታ ስለሚሞላ ጽሞናና ጸሎት፣ እናመሰግንሀለን። ስለጠላታችን እንባ፣ በጦር ሜዳ ስንጋለብ፣ ድግሳችን በሆነው በውጊያ እልልታ፣ እናመሰግንሀለን። በሰዎች ልብና በግምቦች ጫፍ ጎልቶ ስለሚታይ እምነት፣ ስለሚጠብቀን አዳኝ ሞታችን፣ እናመሰግንሀለን። ከፊትህ ለመምጣት ስላለን አስደሳች ተስፋ፣ ደረታችን ቆስሎ ስንጸዳ፣ እናመሰግንሀለን። በልባችን ውስጥ ስለሚያነቃቃን የጦር መሳሪያ ፍቅር፣ ስለታላቁ ክብርህ ክቡር ጌታችን ሆይ፣ እናመሰግንሀለን። ጌታችን ሆይ፣ ስለ እኛ ሳይሆን፣ ስለስምህ ክብር ይሁን። (መዝሙረ ዳዊት) (የቤተመቅደስ ፈረሰኞች መዝሙር Templars’ Hymn)
24Augድንግል ማርያም ከዚህ ሕይወት እንዴት እንዳለፈችና በመላእክት እጅ ወደ ሰማይ እንደፈለሰች እናስባለን።
ቅድስት ድንግል ማርያም የሞተችው በንጹህ ፍቅር ተጠምቃ ነው እንጂ በህመም ምክንያት አይደለም። ልጆችዋ ደግሞ የእናታቸውን ምሳሌ መከተል ስላለባቸው ከዚህ አለም ስትለይ በአስደሳቸ ሞት መለየት ከፈለክ እግዚአብሔርን ውደድ። ነፍሷ ሁልጊዜ በዓለም ውስጥ ካሉ ነገሮች ሁሉ ተለይታ የምትኖርና ሁልጊዜም ከእግዚአብሔር ጋር የምትዋሐድ ስለነበረ፣ የቅድስት ማርያም ሞት አስደሳች ነበር። ፀሐይን የለበሰች፣ ጨረቃን ከእግሯ በታች ያደረገች፣ የዚህን ምድር ሀብት ትረግጣለች። አንተም በሞት ጊዜ መደሰት ትፈልጋለህ? ከሁሉም ነገር፣ ከዘመድም፣ ከክብርም፣ ከሀብትም፣ ከስጋህም ተለይተህ ኑር። ምክንያቱም ከእነዚህ ነገሮች ጋር በመያያዝህ ሞትህ መራራ ይሆናል። ሁልጊዜ ቅድስት፣ ሁልጊዜም ንፁህ፣ ሁልጊዜም ከኃጢአት ጥላ ነፃ ስለነበረች፣ የቅድስት ማርያም ሞት አስደሳች ነበር። አንተም ከኃጢያት የጸዳ የሆነውን ቅዱስ ሕይወት በመምራት፣ ሞትህ አስደሳችና ጣፋጭ እንዲሆን ታደርጋለህ። በሰማይ ክብር በእግዚአብሔር እንደምትደሰት እርግጠኛ ስለነበረች፣ የቅድስት ማርያም ሞት አስደሳች ነበር። ከዚህ አለም ስትለይ በአስደሳቸ ሞት መለየት…
31Julሕይወትህን ሊለውጥ የሚችል ጥበብ
ብዙውን ጊዜ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት፣ ብዙዎቻችን ለመተግበር የሚከብደን አንድ ምግባር አለን፥ ንፅህና፣ ቸርነት፣ እምነት፣ ትዕግስት፣ ደግነት፣ ተስፋ፣ ምህረት ወይም ትህትና ሊሆን ይችላል። ደስ የሚለው ግን በተቃራኒው ብዙዎቻችን ከሌሎች ምግባሮች ይበልጥ በቀላሉ የምንለማመድበት አንድ ምግባር አለን። በተፈጥሮ፣ በአስተዳደግ፣ በባህርይና በጸጋ ጥምረት ምክንያት፣ ሳይከብደን የምንፈጽመው ምግባር አለን። የተጠቀሰውን መልካም ምግባር የተሻለ ለማድረግ ምን ያስፈልጋል? ያለህን ጥሩ ምግባር ማሻሻል አላስፈላጊ ነገር ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ጥንካሬህን ወደ ኦሊምፒክ ደረጃ ከፍ ማድረግ ከቻልክ፣ ወደ ውጭ ይንፀባርቃልና በሌሎች ምግባሮች ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል። ለምሳሌ፣ በደግነት ጎበዝ ከሆንክ ንጽሕና ቀላል ይሆንልሃል። በንጽሕና ጎበዝ ከሆንክ ደግነት ቀላል ይሆንልሃል። እኛ ሁላችንም ማበረታታት የሚገባን አንድ ልዩ ምግባር አለን የሚል እምነት አለኝ። ጥንካሬህን ለማወቅ ሞክር። ይህ መንፈሳዊ ጤንነትን የሚሰጥ ልምምድ ነው። የዚያ ምግባር ልምምድህ በጣም ጥሩ እንደሚያደርግህ ማሰብ ራሱ መልካም…
03Junችግሮችን ማስወገድ ወይስ ህፃናትን ማጥፋት? የ2030 አጄንዳ እና የህይወት መብት
ህይወትን በተመለከተ፣ በተባበሩት መንግስታት ላይ ጥርጣሬ ውስጥ የምንወድቀው እኛ ብቻ አይደለንም። በ 1994 GC ካይሮ ውስጥ በተካሄደው የሕዝብና ልማት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ጀምሮ (International Conference on Population and Development)፣ የabortion ተሟጋቾች በተባበሩት መንግስታት ሰነዶች ቋንቋ በመጠቀም አጀንዳቸውን ማራመድ ከጀመሩ ቆይተዋል። ብዙን ጊዜ በተባበሩት መንግስታት ሰነዶች ውስጥ በሚገኘው “የወሲብና የስነ ተዋልዶ መብቶችና ጤና አገልግሎት” (“sexual and reproductive rights” and “sexual and reproductive health care services”) በሚል ሀረግ ትርጉም ላይ እስካሁን ያልተቋረጠ ትግል ተካሄዶአል። የabortion ተሟጋቾች የወሲብና የስነ ተዋልዶ መብቶች የውርጃን መብት እንደሚያካትቱ ያምናሉ። የተባበሩት መንግስታት በ2015 GC በጻፉት የዘላቂ እድገት አላማዎች አጄንዳ ዙርያ (Agenda 2030) ይህ ፊልሚያ አሁንም እንደገና ተፋፍሟል.። እንዲያውም በአጄንዳ ቁትር 3.7 እና 5.6 ውስጥ ከላይ የጠቀስኩትን ቋንቋ እናገኛለን። ምንም እንኳን abortion የሚል ቃል በሰነዱ ውስጥ ባይኖርም፣ አጄንዳን 2030…
13Mayበኢራቅና በሶርያ የተሰቀሉ ክርስቲያኖች… ሴቶቻቸው ከተደፈሩና ልጆቻቸው ከተገደሉ በኋላ፣ ተሰቃይተው ሞቱ። የተደፈሩት፣ የተጨፈጨፋትና ተሰልበው ወይም አይናቸው ተነቅሎ የተረፉት ሳይቆጠሩ፣ በ2010 ብቻ የተገደሉ የክርስቲያኖች ቁጥር ከ 3000 እስከ 4300 ይደርሳል። በ2010 በባህር ውስጥ የሞቱ ሰዎች 2000 ናቸው። ስለዚህ በዐብይ ጾም ሰብከትና በፍኖተመስቀል ጊዜ፣ በመጀመሪያ የሞቱትን ክርስቲያኖች ማስታወስ ይገባናል፣ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ መናገር ይቻላል። ስለ ክርስቲያን ሰማዕታት ለምን አይነሳም?
29Aprእውነትን ለመናገር ድፍርት ያላቸው ሰዎች አሉ
በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚፈፀሙት ገብረሰዶማዊ ድርጊቶች ቤኔዲክት ፲፮ ባለፈው ሳምንት ከጻፉ በኋላ፣ የፊላደልፊያ ጳጳስ አቡነ ቻፑት (Chaput) የሚከተለውን አስተያየት አቅርበዋል። (…) “በአጭር ጽሑፋቸው ውስጥ የዮሴፍ ራፂንገር (Joseph Ratzinger) እውቀትና ማስተዋል በምድረ በዳ ውስጥ እንደሚዘምብ ዝናብ ነው። ለምሳሌ፥ “አካላዊ ሕይወት ከማዳን በላይ የሆኑት መቼም እማንተዋቸው እሴቶች አሉ። ሰማዕትነት አለ። እግዚአብሔር አካላዊውን ሕይወት ከማትረፍ በላይ ነው። እግዚአብሔርን በመካድ የተገዛ ሕይወት፣ በመጨረሻ ውሸት ላይ የተመሠረተ ሕይወት፣ ሕይወት አይደለም… ከእግዚአብሔር ውጭ የሆነ ዓለም ትርጉም የለሽ ዓለም ብቻ ሊሆን ይችላል… ከዘመናችን ሁከት መመነጨት ያለበት መሠረታዊ ተግባር እንደገና ለእግዚአብሔር ብቻ መኖር እንድንጀምር ነው” “ዛሬ ቤተክርስቲያን እንደ አንድ ፖለቲካዊ ተቋም ተደርጋ ትቆጠራለች። ብዙ ጳጳሳት እንኳን ስለ ቤተክርስቲያን ያላቸው አመለካከት ፖለቲካዊ አመለካከት ነው” በመጨረሻም፥ “በራሳችን የተፈጠረ ቤተክርስቲያን እቅድ በእርግጥ ሕያው ከሆነው አምላክ እንድንርቅ ይሚፈልግ የዲያብሎስ ዕቅድ ያለው ነው። ይህ…
20Aprከዲያቢሎስ ጋር የፈፀምነው ስምምነት ዋጋ እያስከፈለን ነው
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት Pius ፲፩ “አንድ መንግስት በማሕፀን ውስጥ ያለውን ህፃን ለመከላክል ካልቻለ፣ እግዚአብሔር ከምድር ወደ ሰማይ የሚጮኸውን የንጹሐን ደም እንደሚበቀል አስታውሱ”። አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ፍርሃት ይገልጻሉ፥ ፅንስ ማስወገድ የተለመደ ነገር እንዲሆን ስለተደረገ፣ ማኅበረሰባችን ከባድ ቅጣት ይደርስበታል። ማኅበረሰባችን ቅጣት ይደርስበት ይሆን? እኔ የምመልሰው ይህ ነው፥ ዙሪያውን ተመልከቱ! ቀደም ብለው አለማችን የሚገባውን ቅጣት ተቀብሎአል፥ ዘርኝነት፣ የቤቶች መውደም፣ የቤተሰቦች ድህነት፣ ወንጀል፣ ባልና ሚስት መለያየት፣ ስራ አጥነት፣ የዕፅና የመጠት ሱስ። ወጣቶችም ስቃያቸው ለማሳየት ፀጉራቸው ቀይና ቢጫ ይቀባሉ። በነዚህ ችግሮችና ፀንስን በማስወረድ መካከል ምንም አይነት ግንኙነት ላይኖር ይችላል። የተቆጣም አምላክ እነዚህን ቅጣቶች በኛ ላይ እንዳደረሰ መጠቆም አልፈልግም። በእርግጥ የነዚህ ቅጣቶች ምክንያት ማኅበረሰባችን ራሱ ነው፥ ፅንስ ማስወረድን በመቀበሉ ከዲያቢሎስ ጋር ስምምነት ተፈራርሞአልና እነዚህ ችግሮች ሁሉም የስምምነቱ አካል ናቸው።

መግቢያ - Entrance
1 ነገሥት 17፡2-7 ያንብቡ፥ የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት ስላልፈለገ፣ እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያሰን ወደ በረሀ ሄዶ በምስጥራዊ ቦታ እንዲሸሸግ ነገረው። በዚህ ምክንያት ሁለት ተቃራኒ ሁኔታዎችን ማነፃፀር እንችላለን፥ በአንድ በኩል የእግዚአብሔርን ድምጽ ያጣው ሕዝብ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በከሪት ሽለቆ ከእግዚአብሔር ቀጥተኛ መመሪያ እና ምግብ የሚቀበል ነቢይ። ስለዚህ የእግዚአብሔር ድምፅ አሁንም ድረስ ወደሚሰማበት ምስጥራዊ ሸለቆ እንግባ።

የታችኛው ክፍል - Lower Room
በዚህ ክፍል ውስጥ ከማህበራዊ ጉዳይና ከዓለም አቀፍ መስተዳደር ጉዳዮች ጀምሬ በመጽሐፍ ቅዱስ እና በጥንታዊ የክርስቲያን ትምህርት በመሞርክስ፣ አንዳንድ ወሳኝ ግንዛቤዎች አቀርብላችኋለሁ። የሐዋርያውን ጳውሎስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ያንብቡ፥ “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ” (ወደ ሮሜ ሰዎች - ምዕራፍ 12፡2)።

የላይኛው ክፍል - Upper Room
አሁን ባለን ታሪክ ውስጥ ጣዕሙን እንዳጣ ጨው ሆነው የተወሰኑ ክርስቲያን አማኞች እና በተለይ መሪዎች የዚህን ዓለም አካሄድ ለመከተል ከፍተኛ ጉጉት ያድርባቸዋል። ለሰርዴስ መልአክ የተሰጠውን ምክር ያስታውሱ፥ “የነቃህ ሁን፣ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና” (የዮሐንስ ራእይ - ምዕራፍ 3፡2)። ክርስቶስ ቀርቦአል፣ ሲመጣም ከጓደኞቹ ቁጥር መገኘት እንፈልጋለን።

የውኃ ጉድጓድ - Water Well
ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈጽሞ በማይደርቁ ጥንታዊ ምንጮች አጠገብ አርፌ ማታደስን አገኛለሁ። “ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?” (መዝሙረ ዳዊት - ምዕራፍ 42)። ቀጣዮቹ ገጾች ክርስቶስን ለመማረክ ማንኛውንም ነገር ለመተው ከመረጡ ከዛሬና ትላንት አማኞች ልብ ይወጣሉ።

እንጀራ ቤት - Kitchen
እና እዚህ ደረስን። የክርስቶስ ወዳጅ ከምድራዊ ደስታ አይገለልም። “እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና ሂድ፥ እንጀራህን በደስታ ብላ፥ የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ” (መጽሐፈ መክብብ - ምዕራፍ 9፡7)። በእግዚአብሔር እይታ መሠረት የሚኖሩት ሰዎች የዝናን የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ ይሰማቸዋል።