- 03Apr
የአብይ ጾም 5ኛ እሁድ (A LENT-5)
ወንገል፥ ዮሐንስ 11፥1-45 ቁ3 “ጌታ ሆይ፥ እነሆ ወዳጅህ ታሞአል”፥ … “ብዙዎች የእግዚአብሔር ወዳጆች በመጥፎ ነገር ሲሰቃዩ ማየት ያናድዳቸዋል። ለምሳሌ፣ የታመሙ ወይም ድሃ የሆኑ ወይም ሌሎች አሳዛኝ ሁኔታዎችን የተቋቋሙ አሉ። በዚህ ምክንያት የሚሰናከሉት የእግዚአብሔር ልዩ ወዳጅ እንደነዚህ ያሉትን ነገሮች ለመቋቋም የእርሱ ድርሻ እንደሆነ አያውቁም። የአልዓዛርን ታሪክ ማየት እንችላለን፥ እርሱ የክርስቶስ ወዳጅ ነበረ ግን ታሞአል” (JOHN CHRYSOSTOM 344-407) “እዚህ ላይ ለወዳጅ የሚያስፈልገው አንድ ትእዛዝ ብቻ ነው፥ ነገር ግን ሴቶቹ ኢየሱስን ’ና’ ብለው አላዘዙም። ደግሞም ‘እዚያ እዘዝ እና እዚህ ይፈጸማል’ ለማለት አልደፈሩም። እነዚህ ሴቶች የተናገሩት ‘ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሞአል’ የሚል ቃል ብቻ ነው፤ ማለትም፥ አንተ ማወቅህ በቂ ነው፣ ምክንያቱም ሰውን ወደህ ለብቻ አትተውም” (AUGUSTINE 354-430) ቁ6 “እንደ ታመመም በሰማ ጊዜ ያን ጊዜ በነበረበት ስፍራ ሁለት ቀን ዋለ”፥ … “ለሞት ሙሉ በሙሉ ቦታ እንዴት እንደሰጠ ትመለከታለህ።…
28Marየአብይ ጾም 4ኛ እሁድ (A LENT-4)
ወንገል፥ ዮሐንስ 9፥1-41 ቁ7 “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው”፥ … “እግዚአብሔርም ደግሞ ተናገረኝ እንዲህም አለኝ፥ ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚሄደውን የሰሊሆምን ምንጭ ውኃ ጠልቶአልና…” ብርቱና ብዙ ውኃ ባለው በኤፍራጥስ ወንዝ ተደስተዋል (ትንቢተ ኢሳይያስ 8፥5-7)። “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል” (መዝሙረ ዳዊት 23)። እምነት በጸጥታ በሚሄድ ውኃ ውስጥ፣ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይገኛል። እንቁም፣ ፀሎትን እንጨምር፣ ወደ ራሳችን እንግባ። እግዚአብሔር የሚገኘው በጸጥታ በሚፈስ ውሃ ውስጥ ነው እንጂ በኤፍራጥስ ወንዝ ብርቱ ግፊት ውስጥ አይገኝም። 1ኛ ንባብ፥ 1ኛ ሳሙኤል 16፥1-13 ሳሙኤል ዳዊትን ይቀባል፣ ከዚህ ቀን ጀምሮ ዳዊት ንጉሥ ነው። ነገር ግን ዳዊት እንደ ንጉሥ የሚገለጸው ከሳኦል ሞት በኋላ ብዙ ችግርና መከራ ካሸነፈ በኋላ ብቻ ነው። ሆኖም ግን ከዚያ በፊት እግዚአብሔር አስቀድሞ በስውር መርጦት ነበረ። ማንም እንደማያስተውለው እግዚአብሔር በስውር ይሠራል።…
20Marየአብይ ጾም 3ኛ እሁድ (A LENT-3)
ወንገል፥ ዮሐንስ 4፥5-42 ቁ6 “በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ የተነሳ ስለደከመው በጕድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ”፥ … እዚህ ላይ ሁለት ነገሮች ይጠቁማሉ፥ ድካምና ስድስተኛ ሰዓት። ስድስተኛ ሰዓት ክርስቶስ የተሰቀለበት ሰዓት ነው፣ ድካም ደግሞ የመስቀሉ ድካም ነው። በሰማርያ ጕድጓድና በመስቀል ላይ የተከሰተውን ማነጻጸር እንችላለን፥ በሰማርያ ጕድጓድ ኢየሱስ ውሃን ይጠይቃል፣ በመስቀል ላይ “ጠማኝ” ይላል። በሰማርያ ጕድጓድ ኢየሱስ የውሃን ጥማት ለዘላለም የሚያረካ የሕይወትን ውሃ ይሰጣል፣ በመስቀል ላይ ጎኑ ራሱ የሕይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል። “ለሁሉ ሰው የሕይወት እስትንፋስ ምንጭ የሆነው ክርስቶስ በጉዞ ምክንያት ደክሞ ስለነበረ በሰማርያ የውሃ ምንጭ አጠገብ ተቀመጠ። ጊዜውም የሚያቃጥል ሙቀት ውቅት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ። መሲሑ በጨለማ ያሉትን ሊያበራላቸው የመጣው እኩለ ቀን ነበር። ውሃን የፈጠረ ለመጠጣት ሳይሆን ለማንጻት ወደምንጩ መጣ። የዘላለማዊነት…
13Marየአብይ ጾም 2ኛ እሁድ (A LENT-2)
ወንገል፥ ማቴዎስ 17፥1-9 ቁ1 “ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው”፥ … “ከስድስት ቀንም በኋላ”፥ … ከባርነት ነፃ ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት ለመድረስ እስከ ዛሬ ድረስ አብሮ በምጥ ጭንቀት ተይዞ በመቃተት ላይ ያለው የፍጥረት ፍጻሜ ሰባተኛው ቀን (ሮሜ 8፥21-22) የሁሉ ፍጥረት አላማ ነው። “ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ”፥ … “ጴጥሮስ ያዕቆብና ዮሐንስ ከርሱ ጋር ባላቸው ቅርበትና ፍቅር ምክንያት ኢየሱስን ወደ ተራራ ይሸኛሉ” (JOHN CHRYSOSTOM 344-407) ታቦርና ደብረዘይት ማነፃፀር እንችላለን። በታቦር ላይ አብ ልጁን ሲጠራ፣ በደብረዘይት ላይ ኢየሱስ አባቱን ይጠራል። ታቦር ላይ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ያሳያል፣ በደብረዘይት ደግሞ ኢየሱስ ሰው መሆኑን ያሳያል። ቁ2 “በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ”፥ … ይህ መለወጥ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ሁሉ ያቀደ…
05Marየአብይ ጾም 1ኛ እሁድ (A LENT-1)
ወንገል፥ ማቴዎስ 4፥1-11 የኢየሱስ ፈተናዎች ከሦስት ጣዖታት ጋር የተዛመዱ ናቸው፥ እነሱም ድንጋዮችን ወደ እንጀራ የሚቀይር የኢኮኖሚ ጣዖት አምልኮ፤ እግዚአብሔርን መግዛት የሚፈልግ የሃይማኖት ጣዖት አምልኮና ሁሉን ሰው መግዛት የሚፈልግ የፖለቲካ ጣዖት አምልኮ ናቸው። ቁ1 “ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው”፥ … “ይፈተን ዘንድ”፥ … “ልጄ ሆይ፣ እግዚአብሔርን ለማገልገል ራስህን ካቀረብህ ለፈተና ተዘጋጅ” (ሲራክ 2፥1)። ጥሩ ውሳኔ ከተወሰነ በኋላ የመፅናት ትግል አለ። በግሪክ ቋንቋ “ፈተና” “peiro” ይባላል፣ “peiro” ማለት ማቋረጥ ማለት ነው፥ experience በማድረግ (experience = “peiro”), expert (“peiro”) እንሆናለን። በድሮ ታሪክ ፈተናዎች እንዲሁ ትምህርት ይባሉ ነበር፥ እሱም ልጆች መሆናችንን እንጂ ዳቃሎላዎች አለመሆናችንን የሚያረጋግጠው የልጅ ሕይወት ሥልጠና ነው (ዕብራውያን 12፥8) ፣ በእምነት ደረጃ የመጣራት ሥልጠና ነው (ያቆብ 1፥2-4፣ 1ጴጥሮስ 1፥6)። “ከዲያብሎስ”፥ … በግሪክ ቋንቋ “ዲያብሎስ” ማለት የሚከፋፍል ማለት…
24Jan[K2] Boeing 737 Max “በሰርከስ ክበብ ታቅዶ፣ ተራ በተራ በጦጣዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ የተዘጋጀ ነው” Boeing 737 Max “designed by clowns and supervised by monkeys”
Boeing 737 Max ላይ ስለደረሱ አደጋዎች ምርመራ፣ የኩባንያው አስተዳደር ቸልተኝነትንና ስግብግብነትን የሚገልጹ አስደንጋጭ ዝርዝሮች ብቅ እያሉ ነው። RT እንደዘገበው፣ የኩባንያው አንድ ባለሙያ አውሮፕላኑ “በሰርከስ ክበብ (circus clown) ታቅዶ፣ ተራ በተራ በጦጣዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ የተዘጋጀ ነው” በማለት ገልፆ ነበር። ሌላ ባለሙያም “ባለፈው ዓመት ስለደበቅኩት ነገር እስካሁን ድረስ በእግዚአብሔር ዘንድ ይቅርታን አላገኘሁም” ብሏል። ሌሎች ችግሮች ደግሞ ከ“በረራ አስመሳይ” (flight simulator) ብቃት ጋር የተገናኙ ናቸው፤ አንድ ሠራተኛ ሌላውን፥ “በ flight simulator ብቻ በሰለጠነውን የአውሮፕላን አብራሪ ታምናለህን? ሚስትህንና ልጆችህን ለርሱ ታሰረክባለህን?” በማለት ጽፎአል። መልሱ “አይ” የሚል ነው። የሚያሳስበው ነገር ቢኖርም፣ እነዚህን ወሬዎች በጥልቀት ከመመርመር ይልቅ እየተወገዱ መሆናቸውን ነው። የአሜሪካ ፌዴራል በረራ ድርጅት (FAA America Federal Aviation Agency) እስካሁን ድረስ flight simulator ፍጹም በቂ እንደሆነ ከመግለጽ አያርፍም። የ 737 Max ትንተና የበራሪዎችን ህይወት አደጋ…
22Jan[WW1] ምንም የማያጣ (ቅዱስ ባስልዮስና ግሮጎርዮስ) Who has nothing to lose (Saint Basil and Gregory Nazianzus)
ቅዱስ ባስልዮስና ቅዱሰ ግሮጎርዮስ “ክርስቶስ አምላክ አይደለም” በሚል በአርዮስ መናፍቅነት ጊዜ በሰሜናዊ ቱርክ ቀጰዶቅያ በሚባል ክልል ውስጥ ጳጳሳት ነበሩ። ስለ አርዮስ የሚገልፅ የኒቂያ ጉባኤ ግልጽ ማረጋገጫ ቢኖርም፣ መናፍቃን ተስፋ አልቆረጡም ነበረ። ባስልዮስና ግሮጎርዮስ መናፍቅነትን ለማጥፋት ባከናወኑት ትግል ውስጥ ለእውነት በመቆም የማይሸነፉ ሀይሎች ነበሩ። ራሱ የአርዮስ ተከታይ የነበረ ንጉሥ ዩልያኖስ ለመናፍቃን ቅዱስ ቁርባን እንዲፈቀድላቸው ጳጳሳትን ለማስገደድ በሞከረ ጊዜ፣ ባስልዮስና ግሮጎርዮስ ለመታዘዝ አልቻሉም። አንድ ቀን በባስልዮስና በክልሉ አስተዳዳሪ መካከል የተከሰተ ክርክር፣ በአሁኑ ጊዜ ያልተለመደ የአንድ ጳጳስ ጥንካሬና ምሳሌነት ያሳያል። የክልሉ አስተዳዳሪ፣ የባስልዮስ ተቃውሞ ሲያጋጥመው፥ “መላው ዓለም የሚሰግድለትን የንጉሠ ነገሥቱን ፈቃድ ለመቃወም እብዳችኋልን? የንጉሠ ነገሥቱን ቁጣ፣ ስደት ወይም ሞት አትፈሩምን?” ሲል፣ ባስልዮስ ረጋ ብሎ “ምንም ንብረት የሌለው ንብረትን ማጣት አያስፈራራውም፤ ምድር ሁሉ ቤቴ ስለሆነች ልታሳድዱኝ አትችሉም፤ ሞት እንኳን ቢሆን ለእኔ መስጠት ከምትችሉት ታላቅ…
0 comments Read more21Jan[LR1] በውጪ አቆጣጠር 2019 የሞት ዋና መንስኤ? ልጅ ማስወረድ The world’s leading cause of death in 2019? Abortion.
ምንም እንኳን ማወቅ በጣም ተገቢ ቢሆንም፣ በመደበኛ ሚዲያዎች ችላ የሚባሉ ዜናዎች አሉ። በምድር ላይ እጅግ ዘመናዊ የሆነ Worldometer የሚባል የሒሳብ ማሽን ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ 58.6 ሚሊዮን ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጦአል። ታድያ አዲስ ነገር የት አለ? በእውነቱ ሁለት ዜናዎች አሉ፣ የተደራረቡም ናቸው። የመጀመሪያው፥ በ2019 ከሞቱት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ የሞቱት በተፈጥሮ ምክንያት ሳይሆን በሰው ፍቃድ ምክንያት ነው። አለምን ያደናቀፉት ጦርነቶች ከታሰቡ፣ ግድ ነው ትሉ ይሆናል!!! ግን አይደለም፣ ስህተት ነው! እንዲያውም፣ አሳዛኝና የማይነበበው ሁለተኛው ዜና እንሆ፥ በዓለም ላይ በሰው ፍቃድ ከሞቱት ሰዎች፣ አብዛኞቹ የሞቱት በሰው በተነሳ ግጭትና ጦርነት ሳይሆን በፍቃደኝነት ፅንስን በማስወረድ ነው። ባለፈው ዓመት 42.4 ሚሊዮን የሰው ልጆች በውርጃ ምክንያት ተገድለዋል። ግልጽ ለማድረግ፣ 42 ሚሊዮን ሰለባዎች ማለት፣ በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ጊዜ አውሮፓ በጥፋት፣ ቦምብና በማጎሪያ ካምፖች በተናወጠች ጊዜ ከነበሩት ሲቪልና ወታደራዊ ሰለባዎች…
18Janየጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት (Baptism of the Lord)
ይህን የዮርዳኖስ ትዕይንት ከጎልጎታ ጋር ማነፃፀር እንችላለን። እዚህ ላይ ኢየሱስ በውሃ ውስጥ ሲጠመቅ፣ እዚያ በሞት ይጠመቃል፤ እዚህ ላይ የሰማይ መጋረጃ ሲቀደድ፣ እዚያ የቤተመቅደስ መጋረጃ ይቀደዳል፤ እዚህ ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን ሲቀበል፣ እዚያ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣል፤ እዚህ በአባቱ ሲጠራ፥ እዚያ አባቱን ይጠራል፤ እዚህ በአባቱ ልጅ ተብሎ ይጠራል፣ እዚያ ልጅ ተብሎ ይሚጠራ በሮማዊ ወታደር ነው (27፥51-54)። መላው የኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት፣ በሥጋው በመገለጹ በዚህ ሁለት ትዕይንቶች መካከል ይገኛል፣ እንዲሁም የእነዚህ ሁለት ትዕይንቶች ማብራሪያ ነው። የጥምቀት ዘር አድጎ የመስቀል ዛፍ ይሆናል። ቁ13 “በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ”፥ … እርሱ ለምን መጣ? ቅዱሱ ምን ኃጢአት አለው? ምንም! በዚህ ምክንያት የሁሉን ሰው ኃጢአት ይሸከማል። የሌሎችን ክፋት የሚሸከመው ክፋትን ሳያደርግ የሚያፈቅር ነው። የጥምቀቱ አላማ ከልደቱ ጋር አንድ ዓይነት ነበር፣ ማለትም ከኃጢተኛ ሰው ዘር…
10Jan[UR1] ኢየሱስ ባለተወለደ ቢሆንስ? What if Jesus was never born?
የስልጣኔአችን ሥሮች በእሱ ላይ የተመሰረቱ ናቸው እና በአጭሩ ያለ እሱ አይሆኑም ነበር። አንዳንድ ምሳሌዎች እነሆ፥ ሆስፒታል የሆስፒታሎችና የህሙማን እንክብካቤ እድገት ድሆችንና የህሙማንን ከክርስቶስ ስቃይ ማነጻጸር ከእምነት የመነጨ ነው፣ በምድራዊ ሕይወቱ ኢየሱስ የሥጋና የነፍስ ፈዋሽ ሆኖ ራሱ ሕመምተኛ ነበረ፤ የመካከለኛው ዘመን የሥነ-መለኮት ምሁራን እንዳሉት ኢየሱስ ራሱ ሐኪምና ህመምተኛ ነበረ። በመካከለኛው ዘመን የተሠሩ ብዙ ሆስፒታሎች (አብዛኛውን በገዳማት አጠገብ) “Domus Dei” (የእግዚአብሔር ቤት) ተብለው ይጠሩ ነበር። በላቲን አሜሪካ፣ እስያና አፍሪካ የመጀመሪያ ሆስፒታሎች በካቶሊክና በፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያን ተመሰርተዋል፥ ዛሬም ቢሆን የአብያተ ክርስቲያናት ጤና አገልግሎት በብዙ አገሮች ውስጥ ትልቅ ሚና አላቸው። የሕፃናት ክብር ክርስትና በተስፋፋ ቁጥር፣ ፅንስ ማስወረድ እና ሕፃናትን ማስወገድ በሕብረተሰብ ተቀባይነት ባለማገኘታቸው ተገድበዋል። በሮማ ግዛት ውስጥ የማይፈለጉ ሕፃናትን በገበያ መሸጥ በስፋት ተለምዶ ቢሆን ኖሮ፣ ክርስቲያኖች ይህንን ድርጊት እንደ ግድያ ያወግዙት ነበር። ዮስቲኖስ ሰማዕት (100-165…
መግቢያ - Entrance
1 ነገሥት 17፡2-7 ያንብቡ፥ የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት ስላልፈለገ፣ እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያሰን ወደ በረሀ ሄዶ በምስጥራዊ ቦታ እንዲሸሸግ ነገረው። በዚህ ምክንያት ሁለት ተቃራኒ ሁኔታዎችን ማነፃፀር እንችላለን፥ በአንድ በኩል የእግዚአብሔርን ድምጽ ያጣው ሕዝብ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በከሪት ሽለቆ ከእግዚአብሔር ቀጥተኛ መመሪያ እና ምግብ የሚቀበል ነቢይ። ስለዚህ የእግዚአብሔር ድምፅ አሁንም ድረስ ወደሚሰማበት ምስጥራዊ ሸለቆ እንግባ።
የታችኛው ክፍል - Lower Room
በዚህ ክፍል ውስጥ ከማህበራዊ ጉዳይና ከዓለም አቀፍ መስተዳደር ጉዳዮች ጀምሬ በመጽሐፍ ቅዱስ እና በጥንታዊ የክርስቲያን ትምህርት በመሞርክስ፣ አንዳንድ ወሳኝ ግንዛቤዎች አቀርብላችኋለሁ። የሐዋርያውን ጳውሎስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ያንብቡ፥ “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ” (ወደ ሮሜ ሰዎች - ምዕራፍ 12፡2)።
የላይኛው ክፍል - Upper Room
አሁን ባለን ታሪክ ውስጥ ጣዕሙን እንዳጣ ጨው ሆነው የተወሰኑ ክርስቲያን አማኞች እና በተለይ መሪዎች የዚህን ዓለም አካሄድ ለመከተል ከፍተኛ ጉጉት ያድርባቸዋል። ለሰርዴስ መልአክ የተሰጠውን ምክር ያስታውሱ፥ “የነቃህ ሁን፣ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና” (የዮሐንስ ራእይ - ምዕራፍ 3፡2)። ክርስቶስ ቀርቦአል፣ ሲመጣም ከጓደኞቹ ቁጥር መገኘት እንፈልጋለን።
የውኃ ጉድጓድ - Water Well
ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈጽሞ በማይደርቁ ጥንታዊ ምንጮች አጠገብ አርፌ ማታደስን አገኛለሁ። “ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?” (መዝሙረ ዳዊት - ምዕራፍ 42)። ቀጣዮቹ ገጾች ክርስቶስን ለመማረክ ማንኛውንም ነገር ለመተው ከመረጡ ከዛሬና ትላንት አማኞች ልብ ይወጣሉ።
እንጀራ ቤት - Kitchen
እና እዚህ ደረስን። የክርስቶስ ወዳጅ ከምድራዊ ደስታ አይገለልም። “እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና ሂድ፥ እንጀራህን በደስታ ብላ፥ የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ” (መጽሐፈ መክብብ - ምዕራፍ 9፡7)። በእግዚአብሔር እይታ መሠረት የሚኖሩት ሰዎች የዝናን የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ ይሰማቸዋል።