-
22Aug
የአንደኛ አመት 19ኛ እሁድ (A OT-19)
ወንገል፥ ማቴዎስ 14፥22-32 √ እንጀራ ከተባዛ በኋላ፣ ኢየሱስ ለመጸለይ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ። ደቀመዛሙርቱ ብቻቸውን ወደ ባህር ወርደው እየቀዘፉ ነው። ስጋውን ሰጥቶ፣ ደቀመዛሙርቱን ወደ መላው አለም ከላከ በኋላ፣ ኢየሱስ ወደ አባቱ ወጣ፣ ከዓይናችንም ተሰወረ። እኛ ደግሞ ነፋስ በተቃራኒ አቅጣጫ እየነፈሰብን፣ በሌሊት ባህርን እየተሻገርን፣ ሊውጠን በሚፈልግ ውቅያኖስ ላይ ተንጠልጥለን፣ ወደ ማዶ ለመድረስ እንታገላለን። ይህ የሁልጊዜ የቤተክርስቲያን ሁኔታ ነው። > በሌሊት ኢየሱስ በባህር ላይ እየተራመደ (ሞትን ድል እንዳደረገ) መጣ። ቤተክርስቲያን እርሱን ከተመለከተች ትራመዳለች፣ የራስዋን ድክመት ከተመለከተች ግን ትሰምጣለች። √ “የሌሊቱ አራተኛ ዋዜማ” (25) በድካምና በጭንቀት የተሞላና የሌሊቱን ሙሉ ጨለማ የተሸከመ፣ ከዘጠኝ እስከ አስራሁለት ሰዓት ያለው ጊዜ ነው። ሰዓቱ ሙሉ ሌሊት ቢሆንም፣ ለአዲሱና አሸናፊ ፀሐይ ቅድመ-ሁኔታ ነው፥ “በምሽት ጊዜ እነሆ ሽብር ይሆናል፤ በማለዳ ግን ይጠፋሉ” (ትንቢተ ኢሳይያስ 17፥14)። አራተኛ ዋዜማ ኢየሱስ ከሙታን የሚነሳበት ጊዜ ነው። አሁን…
-
20Aug
ፍልሰታ ማርያም (Ethiopian Assumption)
በማርያም ውስጥ ሁሉም ነገር “አስቀድሞ” ይፈጸማል፥ > በክርስቶስ ትሩፋት ምክንያት “አስቀድማ” ዳነች (ያለ ኃጢያት ተፀነሰች) > ወንድ ሳያውቃት እናት ባደረጋት በመንፈስ ቅዱስ ሥራ “አስቀድማ” “ፍሬያማ” ሆነች (“የእግዚአብሔር እናት”) > ማንም ሰው ሊያየውና ሊሰግድለት ከመቻሉ በፊት (ከዮሴፍ በፊት፥ ከእረኞች በፊት፥ ከሰባሰገዶች በፊት) በቤተልሔም የተወለደውን የእግዚአብሔር ልጅ “አስቀድማ” ሰገደች > በቃና ዘገሊላ የመጀመሪያ ተአምሩን እንዲፈጽም ኢየሱስን ለመጠየቅ በመንፈስ ቅዱስ “አስቀድማ” ተነሳሳች > ከአካላዊ ሞት በፊት በመነሳት “አስቀድማ” ወደ ሰማይ ፈለሰች > የክፋት ምንጭ በሆነው በዓመፀኛው መልአክ፣ በጥንታዊ እባብ ላይ፣ በሰይጣን ላይ “አስቀድማ” አሸናፊ ሆነች √ In Mary everything happens “in advance”: > “in advance” redeemed (“Immaculate”) for the merits of Christ; > “in advance” fruitful (“Mother of God”) by the work of the Holy Spirit who made her a mother without…
-
08Aug
የአንደኛ አመት 17ኛ እሁድ (A OT-17)
ወንገል፥ ማቴዎስ 13፥44-52 √ መንግሥተ ሰማይ፣ የተሸሸገ ሀብትና እጅግ ክቡር የሆነ እንቁ አንድ አይነት ነገር ናቸው? የተሸሸገ ሀብትና እጅግ ክቡር የሆነ እንቁ ሁለቱም መንግሥተ ሰማይ ከሆኑ፣ በተሸሸገው ሀብትና እጅግ ክቡር በሆነው እንቁ መካከል ምን ልዩነት አለ? የተሸሸገ ሀብት እጅግ ዋጋ ያለው እንቁ ራሱ ሊሆን አይችልምን? ሁለቱም አንድ አይነት ነገር አይደሉምን? > አላስፈላጊ ምሳሌዎችን አባዝቷል! ግን ኢየሱስ አላስፈላጊ ምሳሌዎችን ያባዛል ብለህ ታምናለህን? በዚህ ጉዳይ በጥንቃቄ ማንበብ ያለብን እኛ ነን እንጂ! “መንግሥተ ሰማይ እርሻ ውስጥ የተሸሸገውን ሀብት ትመስላለች…” (44)፤ “መንግሥተ ሰማይ ክቡር የሆነውን እንቁ ለመግዛት የሚፈልግ ነጋዴን ትመስላለች” (45)። አንድ አይነት ነገር እንዳልሆነ አስተውለሃል? መንግሥተ ሰማይ ክቡር የሆነው እንቁ አይደለችም፣ መንግሥተ ሰማይ ክቡር የሆነውን እንቁ ለመግዛት የሚፈልግ ነጋዴ ናት። > የተሸሸገው ሀብትና ነጋዴው ምን አይነት ልዩነት አላቸው? የተገኘ ሀብት ድርጊትን ፈጻሚ ወይስ ድርጊትን ተቀባይ…
-
17Jul
የአንደኛ አመት 14ኛ እሁድ (A OT-14)
ወንገል፥ ማቴዎስ 11፥25-30 1 “አባት ሆይ! … አመሰግንሃለሁ” (25)፥ … በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወልድ ወልድ የሚሆንበት “አባባ” የሚል ቃል በልባችን ውስጥ ይመነጫል (“አባባ” ሕፃን ልጅ አፍ መፍታት በሚጀምርበት ጊዜ የሚናገረው ቃል ነው)። በአብና በወልድ መካከል ባለው መግለጽ በማይቻል ውይይት ውስጥ እንገባለን። በቅድስት ሥላሴ ውስጥ እንገባለን። > ፍጥረት ሁሉ አላማውን ይፈጽማል፥ የእግዚአብሔር ልጅ እና የሰው ልጅ በሆነው በኢየሱስ ዋሽንት ድምጽ ተደስተን፣ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያዋሕደውን የሰርግ ግብዣ እንሳተፋለን። በስጋው አማካይነት እያንዳንዱ ስጋ ከክብር ጋር ይዋሐዳል። > አባባ ተብሎ የሚጠራ “የሰማይና የምድር ጌታ ነው” (25)። ለእኛ ቅርብና አፍቃሪ የሆነ አባታችን ልዑልና ሁሉን የሚችል ነው። እንደ ጣዖት እንዳይታይ፣ እግዚአብሔር የሚገለጸው በተቃራኒ ቃላት አማካይነት ነው፥ እርሱ ቅርብና ልዑል፣ አፍቃሪና ኃያል፣ ትሁትና ታላቅ፣ እናትና አባት ነው። > የአለም ጥበበኞችና ብልጦች ስልጣን ያለውን ጥበበኛ አምላክ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ። ትሁታንና ታናናሾች ግን…
-
19Jun
የቅዱስ ቁርባን (A-OT-CorpusDomini)
√ ሁሉም ነገር በአንድ ቁራጭ። የቅዱስ ቁርባን ክብረ በዓል በአንድ ቁራጭ ህብስት ውስጥ ሁሉም እንደሚገኝ የሚገልጽ ክብረ በዓል ነው። ምክንያቱም ሁሉም ነገር በአንድ ፍርፋሪ ውስጥ ይገኛል። ሁሉም ነገር እንዲኖር ትንሽ የህብስት ቁራጭ በቂ ነው። > የክርስቶስ ሥጋና ደም ክብረ በዓል ነው። ግን ክርስቶስ ሕያው ነው ወይስ ሞቷል? ክርስቶስ ሕያው ነው። ሥጋውስ ሕያው ነው ወይስ ሞቷል? የክርስቶስ ሥጋ ሕያው ነው (የሞተ ቢሆን አስከሬን ይባል ነበር)። ሥጋው ሕያው ከሆነ ደግሞ ከሥጋው ጋር ነፍስም አለች። ስለዚህ የኢየሱስ ሥጋ ባለበት የኢየሱስ ነፍስም አለች፣ ምክንያቱም ነፍስ ለሥጋ ሕይወት የሚሰጥ ምንጭ ከሆነ፣ ሥጋ ባለበት ነፍስም ደግሞ አለች። > የኢየሱስን ሥጋና ደም ስንቀበል የኢየሱስን ነፍስም እንቀበላለን። ስለዚህ የኢየሱስ ሰብአዊነት በሙሉ (ሥጋ ደምና ነፍስ) በቅዱስ ቁርባን ይገኛል። የኢየሱስ ሰብዓዊነት ደግሞ ከመለኮቱ ፍጹም ተለይቶ አያውቅም፥ የናዝሬቱ ኢየሱስና የእግዚአብሔር ልጅ ሁለት የተለያዩ…
-
12Jun
ቅድስት ስላሴ (A-OT-Trinity)
1ኛ ንባብ፥ ዘጸአት 34፥4-6.8-9 √ “እግዚአብሔር በደመና ወርዶ ከሙሴ ጋር በዚያ ቆመ” (ኦሪት ዘጸአት 34፥5)። እግዚአብሔር በደመና ምስል ይገለጻል። ደመና ግን ጭጋግና ጨለማ ነው፥ ምንም ነገር ማየት አይቻልም። በጭጋግ ውስጥ ግን ምንም ባይታይም፣ ሰው በውስጡ እየኖረ አለማየትን ይለምዳል። ዋናው ነገር ማየት አይደለም፣ አለማየትን መልመድ ነው እንጂ። √ እግዚአብሔር በደመና ምስል ውስጥ ይገለጻል፣ ደመና የመለኮታዊ ጭጋግ ምስል ነው፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር የማይመረመር አምላክ እና የማይታወቅ ምስጢር ነው። በሚገለጽበት ጊዜ በደመና ተደብቆ ምስጢር መሆኑን አይተውም። ይልቁንም ነፍሳችንን በምስጢሩ ያሳትፋል። > እኛ በደመና ውስጥ አናይም እንጂ በደመና ውስጥ እንደገባን እናውቃለን። እግዚአብሔር አይታይም እንጂ ወደ እርሱ ስንቀርብ በመለኮታዊ ደመና እንደገባን እንገነዘባለን። ነገር ግን እግዚአብሔር በሚገለጽበት ጊዜ ምስጢሩን አያስወግድም እንጂ በምስጢሩ ያሳትፈናል። ደመና እግዚአብሔር ምስጢሩን ሳይተው በምስጢሩ እንደሚያሳትፈን የሚገልጽ ምስል ነው። እግዚአብሔር ከእኛ በላይ ነው፥ በእርሱ…
-
10Jun
Solemnity of the Body and Blood of Christ
√ The whole in one fragment. The solemnity of the Body and Blood of Christ is the solemnity of the whole in a fragment. Because everything is in a fragment. A particle is enough for everything to be there. > If everything is in a fragment, we will not struggle to take anything away. If we were to keep all the things that existed before us and that will exist after us, we wouldn’t be able to do it. But if everything is in a fragment, we can keep everything in one. > It is the solemnity of the Body and Blood of Christ. But is Christ alive or dead? Alive. And is his Body alive or dead? Alive (if…
-
05Jun
የጳራቅሊጦስ (A-PHASIKA-Pentecost)
1ኛ ንባብ፥ የሐዋርያት ሥራ፥ 2,1-11 √ ነፋስ የሚመስለው ድምጽ ቤቱን ሞላው። እሳት ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ አረፈ። ደቀመዛሙርቱም ወደ አደባባይ ወጥተው በተለያዩ ቋንቋዎች የእግዚአብሔርን ቃል መናገር ጀመሩ። √ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል ከመፅነስ በቀር ምንም ሌላ ተልእኮ የለውም። መንፈስ ቅዱስ ልክ በድንግል ማርያም ማህፀን ውስጥ ቃሉን በመፅነስ ልጅ እንድትወልድ እንዳስቻላት፣ አሁንም በሐዋርያት ላይ ራሱን በማፍሰስ በልባቸው ውስጥ ክርስቶስን እንዲፀንሱ፣ በሥራቸውም እርሱን እንዲያፈሩና ለአለም ሁሉ እርሱን እንዲያበስሩም ያስችላቸዋል። “ዝግ በነበረ በላይኛው ክፍል በኩል የገባ መንፈስ፣ ኢየሱስ በተፀነሰበት ጊዜም ዝግ በነበረ በድንግል ማህፀን በኩል የገባ መንፈስ ራሱ ነው” (Gregory the Great †604) የክርስትና ታሪክ እና የዘመናት ይዘት በትክክል የዚህ መለኮታዊ ፅንስና ልደት ማራዘሚያ ነው። የማርያም ሕይወት ፍሬ የኢየሱስ ልደት ነው። አጠቃላይ የቤተክርስቲያን ታሪክ ፍሬ እስከ ዓለም ዳርቻ የሚደርስ ክርስቶስ ነው። ነገር ግን የክርስቶስ ፍጻሜ…
-
30May
የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት (A-PHASIKA-Ascension)
1ኛ ንባብ፥ የሐዋርያት ሥራ 1,1-11 √ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ አይን ተለይቶ ቀረ። እስከዚያ ቀን ድረስ እየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ይኖርና ይበላ ነበር፤ በገሊላ መንገዶች ላይም ከእነርሱ ጋር ይራመድ ነበር፣ ድምጹን ለመስማት እና ተዓምርን ለማግኘት ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ይሰባሰቡ ነበር። አሁን ግን ከእነርሱ ተለይቶ ቀርቷል። ነገር ግን እየሱስ ደቀመዛሙርቱን አልተወም፣ ይልቁን በውስጣቸው መኖር ጀምሯል። ካረገ በኋላ እየሱስ ከአይናቸው ቢለይም በነፍሳቸው ውስጥ መኖር ጀምሯል። በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ክርስቶስ በደቀመዛምርቱ ይኖራልና ደቀመዛሙርቱም በእርሱ ይኖራሉ። “በእኔ ኑሩ፣ እኔም በእናንተ እኖራለሁ” የሚል የኢየሱስ ቃል እና ትእዛዝ እንደሁ ተፈጽሟል (ዮሐንስ 15፥4)። √ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ሲያናግሩ ለመጀመርያ ጊዜ “ጌታ ሆይ!” ብለው ይጠሩታል (6)። ‘ጌታ’ በግሪክ ቋንቋ ‘ኪርዮስ’ (κύριος) ይባላል። ‘ኪርዮስ’ ማለት ደግሞ በሲና ተራራ ላይ እግዚአብሐር ለሙሴ የገለጸለት ስም ነው። ይህ ስም በብሉይ ኪዳን ማንበብ የተከለከለ ስለነበረ፣…
-
16May
የፋሲካ 5ኛ እሁድ (A-PHASIKA-5)
ወንገል፥ ዮሐንስ 14,1-12 √ መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ (6)፣ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም፥ ኢየሱስ ወደ አብ የሚመራ መንገድ ነው። ወደ ሰማይ መድረስ የምንችል፥ > ትእዛዞቹን በመፈጸም > በእምነት አማካይነት፣ ምክንያቱም ጌታችን የመጣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኝ ነው” (ዮሐንስ 3,15) > የእርሱን ምሳሌ በመከተል፣ ምክንያቱም ክርስቶስን ካልመሰለ ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም > ከሁሉ በላይ፣ ክርስቶስ ስጋን ለብሶ በመስቀል ላይ ስለሞተ > ክርስቶስ ከእርሱ ጋር አንድ ተፈጥሮ ያለውን አባቱ ስለገለጸ። √ ኢየሱስ መንገድ ነው። እርሱ ሰማይና ምድርን የሚያገናኝ ብቸኛው መንገድ ነው። በመካከላችን በኖረበት ጊዜ በዚህ ምድር ላይ የእርምጃዎቹን ግልጽ ዱካዎች ትቶአል። የእርሱ እርምጃዎች የዘመናት ብልሽትና የጠላት ሸፍጥ ማጥፋት ያልቻሉ የማይሰረዙ እርምጃዎች ናቸው። “መንገድ የሆነው የሰው ፋና ወደሌለው ቆሻሻ አይመራንም። እውነት የሆነው በሐሰት አያፌዝብንም። ሕይወት የሆነው…