-
15May
[UR7] ሁለት ቤተክርስቲያንና ሁለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት
ብጽአት Anne Catherine Emmerich, 1820፥ “የሁለት አብያተክርስቲያን እና የሁለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በጣም አስደናቂ ራእይ አይቻለሁ… መላው ቤተክርስቲያን በጥቁር ታሽጋ ነበርና በውስጧ የሚከናወነው ሁሉ በድቅድቅ ጨለማ የተሞላ ነበረ… የሐሰት ቤተመቅደስና የሐሰት አምልኮን አየሁ… የሐሰት ቤተክርስቲያን ሲያድግ አይቻለሁ። ሁሉን ዓይነት መናፍቃን ወደ ከተማ ሲጎርፉ አየሁ። የካህናት መንፈሳዊነት እየቀዘቀዘ ሲመጣና የጨለማ ክበብ በጣም እየሰፋ ሲሄድ አየሁ… በየቦታው ካቶሊካዊያን ሲጨቆኑ፣ ሲበሳጩ፣ ሲገደቡና ነፃነታቸው ሲነፈግ አይቻለሁ። አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተው ነበርና መከራ በሁሉም ቦታ ተስፋፍቶ ነበር… “እንደገና በራዕይ ሌላ ነገር አየሁ… ቤተክርስቲያን በታላቅ ጭንቀት በወደቀችበት ጊዜ ከመከራ ነፃ ወጣች… ቅድስት ድንግል ማርያም ነጠሏን በበቤተክርስቲያን ላይ ስትዘርጋ አየሁ። ሁሉም ነገር ሲታደስ እና ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ ቤተክርስቲያን አየሁ…”
-
10Apr
[UR5] ኮቪድ-19 እና የእግዚአብሔር ቅጣት (1)
ኮቪድ-19 ስለእግዚአብሔር ቅጣት እንደገና እንድናስብ እያደረገ ነው፥ ነገር ግን ከቅዱሳት መጻሕፍት ጀምሮ ጉዳዩ ውስብስብ ነው። እግዚአብሔር ይቀጣልን? ለመረዳት እንሞክር። የመጀመሪያው መልስ በ2ኛ ጴጥሮስ 2፥4-17 ላይ እናገኛለን፥ “መላእክትን እንኳ ኃጢአት በሠሩ ጊዜ እግዚአብሔር ሳይራራላቸው በጨለመ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ሆነው የፍርድን ቀን እንዲጠባበቁ ወደ ገሃነም ጣላቸው፥ እንዲሁም የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ሰዎች በነበሩበት አለም ላይ የጥፋትን ውኃ ሲያመጣ ራርቶ የቀደመውም ዓለም አልማረውም፤ ደግሞ እግዚአብሔርን ለማያመልኩ ሁሉ የመቀጣጫ ምሳሌ እንዲሆኑ የሰዶምንና ገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ እንዲጠፉ ፈረደባቸው… ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር በየቀኑ ያየውና ይሰማው በነበረው ሕገ ወጥ ድርጊታቸው ጻድቅ ነፍሱ ትጨነቅ ነበር… ጌታ እግዚአብሔር እርሱን በማምለክ የሚኖሩትን ሰዎች ከፈተና እንደሚያድናቸው፥ ኃጢአተኞችንም እንዴት እንደሚቀጣና ለፍርድ ቀንም እንዴት ጠብቆ እንደሚያቆያቸው ያውቃል ማለት ነው… እነዚህ ግን ለመጠመድና…
-
06Feb
[UR4] የቤኔዲክት ፲፮ አወጣት አሁንም ክፍት ነው (2) The withdrawal of Ratzinger is still open
በአሁኑ ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ በሁሉም ደረጃ ውስጥ አለመግባባትና መከፋፈል መኖሩ የማይካድ ሐቄ ነው። ታዲያ ይህን የተቋጠረ ነገር እንዴት ልንፈታው እንችላለን? እንደኔ አስተያየት ሁለት መንገዶች አሉ፣ አንዱ ለወደፊት የሚፈታ ሲሆን ሌላው ግን ለአሁን የሚሆን ነው። ሁለቱም ግን የሚቃረኑ ሳይሆኑ፣ እንዲያውም እርስ በራስ የሚደጋገፉ ናቸው። የመጀመሪያው መንገድ ቤኔዲክት ፲፮ በ2013 ለመልቀቅ ስለገፋፋቸው ምክንያቶች ጠለቅ ያለና ሚዛናዊ ጥናት ማካሄድ ነው፥ በእርግጥ የርሳቸውን ውሳኔ ሕገወጥ ማድረግ የሚችሉ ጫናዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ከሆነ፣ የፍራንሲስ መላው ጵጵስና ወዲያውኑ ሕገወጥ ይሆናል። ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ጥናት ለማካሄድ፣ ሁለቱም የዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ ፈፃሚዎች መጀመሪያ መሞት አለባቸው (ይህ ደግሞ ለማንም መመኘት የማንፈልግ ነገር ነው)። ሁለተኛው መንገድ ቤኔዲክት ፲፮ ከስልጣን ለመልቀቅ ያቀዱትን አዲስ አፈፃፀም ጠለቅ ያለና የስውን ክብር የሚጠብቅ ትንታኔ ማድረግ ነው፥ ይህ ደግሞ አሁንም በፍጥነት ሊከናወን ይችላል። በቅዱስ ጴጥሮስ…
-
06Feb
[UR3] የቤኔዲክት ፲፮ አወጣጥ አሁንም ክፍት ነው (1) The withdrawal of Ratzinger is still open
የሐዋርያ ጴጥሮስ መሪነት ክርስቶስ በተናገረው ቃላት ላይ ተመሰረተ፥ “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም” (ማቴዎስ 16፥18)። ነገር ግን የዛሬ የካቶሊክ መሪዎች ካቶሊካዊ እምነትን በተደጋጋሚ እየደበደቡ ነው። እግዚአብሔር ክልስ እንደነበረ ተብሎአል፣ ማርያም ተራ ልጅ እንደነበረች ተብሎአል (እናስ ያለ ሐጢያት የተፀነሰች አልነበረችምን?) ወይስ በእግዚአብሔር ላይ እንደተናደደች ተብሎአል (የፍጡራን ለእምነትና ለታዛዥነት ምሳሌ አይደለችምን?)። ከዚህ በፊት በሰው መሥዋዕት ብቻ የምትረጋጋ ፓቻማማ የምትባል ህይወት የሌላትና የደረቀች የደቡብ አሜሪካ ጣኦት ከማርያም ጋር በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ማስቀመጥ ተችሎአል። ለዚህ ሁሉ ok ተባለ። የክርስቶስ ወንጌል የጋብቻን ፍቺ ያልፈቀደ ምህረትን በመርሳት እንደሆነ፣ ሆኖም በክርስቶስ ጊዜ የድምጽ መቅረጫዎች ስላልነበሩ የወንጌልን ቃላት በትክክል ማወቅ እንደማንችለው ማለት ትችሎአል። ድርብ ok ተባለ። ሶዶም ከተማ የተቃጠለችው በግብረ ሰዶማዊነት ምክንያት ሳይሆን እንግዳን ባለመቀበል ምክንያት በማለት፣ ብሉይ ኪዳን…
-
26Jan
[UR2] ከመድረክ በስተጀርባ፥ እንዴት እንደ ሆነ እነሆ። የፍራንሲስ ቁጣ በካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ላይ። Background: this is how things went. The despot’s fury against the Catholic pope
“ከልባችን ጥልቀት” የሚል መጽሐፍ፣ በትክክል በቤኔዲክት ፲፮ እና በካርዲናል ሣራህ የተጻፈ ነው፣ ምክንያቱም መጽሐፉን ለማጀጋጀት ሁለቱ የተፃፃፉት ደብዳቤዎች ያለምንም ጥርጣሬ ማስረጃ ናቸው። ከመጀመሪያ ጀምሮ ሁሉም ነገር በጋራ ስምምነት የታቀደ ነበረ። የካህናትን ምንኩስና (ትዳርን መያዝ የሚከለክለው ተውፊት) የሚገልጽ ጽሁፍ አስቀድሞ ከታወቀ በኋላ፣ በፍራንሲስ ንዴት ምክንያት በቫቲካን ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ብጥብጥ ተጀመረ። ምክንያቱም የቤኔዲክት ፲፮ ከፍተኛ ቃል፣ ፍራንሲስ በቀጣይ ድህረ-ሲኖዶስ ማሳሰቢያ ውስጥ የካህናትን ምንኩስና እንዳያፈርሱ ይከለክላል። ስለዚህ ፍራንሲስ የቤኔዲክት ፲፮ ፀሐፊን ጠርተው፣ የቤኔዲክት ፲፮ ስም ከዚያ መጽሐፍ ሽፋን እንዲሰረዝ በንዴት አዘዙት። ፍራንሲስ ሙሉ በሙሉ ቤኔዲክት እንዲክዱ ጠይቀው ነበረ። በዚህ ምክንያት በማለዳ የተነበበ ዜና “ቤኔዲክት ከካርዲናል ሣራህ ጋር ምንም መጽሐፍ አልፃፉም ወይም ሽፋኑን አልፈቀዱም (ማለትም ምንም አልፈረሙም)” በማለት አስታወቀ። ይህ ግን እውነት ስላልነበረ፣ ቤኔዲክት ፲፮ “ካርዲናል ሣራህ በመጽሐፉ ሽፋን ላይ ያለኔ ፈቃድ ስሜን…
-
22Nov
እናንተም ደግሞ መሄድ ትፈልጋላችሁ? (ዮሐ 6፥68)
1. አንዳንድ ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ሁለት የተለያዩ አማልክት አሉ ብለው በማወቅ ወይም ባለማወቅ ያምናሉ። ሁለተኛው አምላክ የመጀመሪያው አምላክ “ዝግመተ ለውጥ” ነው ብለው ያምናሉ። አንዱ ህጉን የሚያስገድድ ብርቱው ፈራጅ የሆነው የብሉይ ኪዳን አምላክ ሲሆን፣ አንዱ ደግሞ የአዲስ ኪዳን አምላክ ነው። ሁለቱም ከምህረትና ይቅር ባይነት አንፃር እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ናቸው። እስከዚህ ያብራራሁት “ግኖሲስ” ተብሎ የሚጠራ በክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው መናፍቅ ነው (በእንግልዝኛ Gnosis ወይም Gnosticism)። የመጀመርያ ክርስቲያን ግኖሲስ ኢየሱስን እንደ “አዲስ ሰይጣን” አድርጎ ያስበው ነበር። ምንም እንኳ የማይረዳ ቢመስልም፣ በግኖሲስ ትምህርት መሰረት፣ በክፉ ፈጣሪ (የብሉይ ኪዳን አምላክ) ለተፈጠረ ለአዳም ዕውቀትና ነፃነት በማሳየት (“ግኖሲስ” በግሪክ ቋንቋ “እውቀት” መለት ነው)፣ ሰይጣን የብርሃን ምንጭ ነው ይለዋል። እንደ ግኖሲስ አስተሳሰብ፣ ዓለም በክፉ አምላክ የተፈጠረች የሰው ዘር የታሰረባት እስር ቤት ናት ብሎ ያምናል። ስለዚህ የፈጣሪ አምላክ ሕግ የሰው…
-
10Oct
የአማዞን የጳጳሳት ጉባኤ (ሲኖዶስ)
ባለፈወ ጥቅምት 4 በቫቲካን ጋርደን በአማዞን ሲኖዶስ መክፈቻ ስነ-ሥርዓት ላይ የሆነውን ነገር አስተውላችኋል? ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አረማዊ ንጥረ ነገሮችን ያካተተ ሥነ ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል። የተለያዩ የአማዞን ሕዝብ መሪዎች ለእናት ምድር ጸሎት አቀረቡ። አንድ ዛፍ ተተክሎአል። አንድ ሰው በጉልበቱ ተንበርክኮ የቆሻሻ አቧራ ስሞአል። ከዝግጅቱ በኋላ ተሳታፊዎች ነፍሰጡር ሴቶች እና እናት ምድር የሚመስሉትን ሐውልቶች በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው ሲሰግዱ ታይተዋል። የእግዚአብሔር ቃልና የቤተክርስቲያን ትምህርትና ምስጥራት እስካሉ ድረስ፣ ወንጌልን መስበክ ይቻላል። ነገር ግን ወንጌላዊ ተልእኮ በአረማውያን ሥነ-አምልኮ ውስጥ መሳተፍን ያካትታል ብሎ የሚያስተምር መመሪያ አላውቅም። ከአረማውያን ጋር መነጋገር አለብን ከሚሉ ሰዎች ጋር መሄድ አያስፈልግም። ሚሽነሪዎች በአማዞን አካባቢ ገብተው እግዚአብሔር ዓለምን ስለወደደ አንድ ልጁን አሳልፎ እንደሰጠ ከልብና በፍቅር እንዲናገሩ ይገባል። የቤተክርስቲያን ተውፊት ክርስቶስን እንድንሰብክ ያስተምረናል። ይሁን እንጂ ከአረማውያን ጋር እንድንወያይ፣ በአረማውያን አምልኮ ውስጥ እንድንሳተፍም…
-
13May
በኢራቅና በሶርያ የተሰቀሉ ክርስቲያኖች… ሴቶቻቸው ከተደፈሩና ልጆቻቸው ከተገደሉ በኋላ፣ ተሰቃይተው ሞቱ። የተደፈሩት፣ የተጨፈጨፋትና ተሰልበው ወይም አይናቸው ተነቅሎ የተረፉት ሳይቆጠሩ፣ በ2010 ብቻ የተገደሉ የክርስቲያኖች ቁጥር ከ 3000 እስከ 4300 ይደርሳል። በ2010 በባህር ውስጥ የሞቱ ሰዎች 2000 ናቸው። ስለዚህ በዐብይ ጾም ሰብከትና በፍኖተመስቀል ጊዜ፣ በመጀመሪያ የሞቱትን ክርስቲያኖች ማስታወስ ይገባናል፣ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ መናገር ይቻላል። ስለ ክርስቲያን ሰማዕታት ለምን አይነሳም?
-
29Apr
እውነትን ለመናገር ድፍርት ያላቸው ሰዎች አሉ
በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚፈፀሙት ገብረሰዶማዊ ድርጊቶች ቤኔዲክት ፲፮ ባለፈው ሳምንት ከጻፉ በኋላ፣ የፊላደልፊያ ጳጳስ አቡነ ቻፑት (Chaput) የሚከተለውን አስተያየት አቅርበዋል። (…) “በአጭር ጽሑፋቸው ውስጥ የዮሴፍ ራፂንገር (Joseph Ratzinger) እውቀትና ማስተዋል በምድረ በዳ ውስጥ እንደሚዘምብ ዝናብ ነው። ለምሳሌ፥ “አካላዊ ሕይወት ከማዳን በላይ የሆኑት መቼም እማንተዋቸው እሴቶች አሉ። ሰማዕትነት አለ። እግዚአብሔር አካላዊውን ሕይወት ከማትረፍ በላይ ነው። እግዚአብሔርን በመካድ የተገዛ ሕይወት፣ በመጨረሻ ውሸት ላይ የተመሠረተ ሕይወት፣ ሕይወት አይደለም… ከእግዚአብሔር ውጭ የሆነ ዓለም ትርጉም የለሽ ዓለም ብቻ ሊሆን ይችላል… ከዘመናችን ሁከት መመነጨት ያለበት መሠረታዊ ተግባር እንደገና ለእግዚአብሔር ብቻ መኖር እንድንጀምር ነው” “ዛሬ ቤተክርስቲያን እንደ አንድ ፖለቲካዊ ተቋም ተደርጋ ትቆጠራለች። ብዙ ጳጳሳት እንኳን ስለ ቤተክርስቲያን ያላቸው አመለካከት ፖለቲካዊ አመለካከት ነው” በመጨረሻም፥ “በራሳችን የተፈጠረ ቤተክርስቲያን እቅድ በእርግጥ ሕያው ከሆነው አምላክ እንድንርቅ ይሚፈልግ የዲያብሎስ ዕቅድ ያለው ነው። ይህ…
-
20Apr
ከዲያቢሎስ ጋር የፈፀምነው ስምምነት ዋጋ እያስከፈለን ነው
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት Pius ፲፩ “አንድ መንግስት በማሕፀን ውስጥ ያለውን ህፃን ለመከላክል ካልቻለ፣ እግዚአብሔር ከምድር ወደ ሰማይ የሚጮኸውን የንጹሐን ደም እንደሚበቀል አስታውሱ”። አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ፍርሃት ይገልጻሉ፥ ፅንስ ማስወገድ የተለመደ ነገር እንዲሆን ስለተደረገ፣ ማኅበረሰባችን ከባድ ቅጣት ይደርስበታል። ማኅበረሰባችን ቅጣት ይደርስበት ይሆን? እኔ የምመልሰው ይህ ነው፥ ዙሪያውን ተመልከቱ! ቀደም ብለው አለማችን የሚገባውን ቅጣት ተቀብሎአል፥ ዘርኝነት፣ የቤቶች መውደም፣ የቤተሰቦች ድህነት፣ ወንጀል፣ ባልና ሚስት መለያየት፣ ስራ አጥነት፣ የዕፅና የመጠት ሱስ። ወጣቶችም ስቃያቸው ለማሳየት ፀጉራቸው ቀይና ቢጫ ይቀባሉ። በነዚህ ችግሮችና ፀንስን በማስወረድ መካከል ምንም አይነት ግንኙነት ላይኖር ይችላል። የተቆጣም አምላክ እነዚህን ቅጣቶች በኛ ላይ እንዳደረሰ መጠቆም አልፈልግም። በእርግጥ የነዚህ ቅጣቶች ምክንያት ማኅበረሰባችን ራሱ ነው፥ ፅንስ ማስወረድን በመቀበሉ ከዲያቢሎስ ጋር ስምምነት ተፈራርሞአልና እነዚህ ችግሮች ሁሉም የስምምነቱ አካል ናቸው።