የአንደኛ አመት 19ኛ እሁድ (A OT-19)

የአንደኛ አመት 19ኛ እሁድ (A OT-19)

ወንገል፥ ማቴዎስ 14፥22-32

√ እንጀራ ከተባዛ በኋላ፣ ኢየሱስ ለመጸለይ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ። ደቀመዛሙርቱ ብቻቸውን ወደ ባህር ወርደው እየቀዘፉ ነው። ስጋውን ሰጥቶ፣ ደቀመዛሙርቱን ወደ መላው አለም ከላከ በኋላ፣ ኢየሱስ ወደ አባቱ ወጣ፣ ከዓይናችንም ተሰወረ። እኛ ደግሞ ነፋስ በተቃራኒ አቅጣጫ እየነፈሰብን፣ በሌሊት ባህርን እየተሻገርን፣ ሊውጠን በሚፈልግ ውቅያኖስ ላይ ተንጠልጥለን፣ ወደ ማዶ ለመድረስ እንታገላለን። ይህ የሁልጊዜ የቤተክርስቲያን ሁኔታ ነው

> በሌሊት ኢየሱስ በባህር ላይ እየተራመደ (ሞትን ድል እንዳደረገ) መጣ። ቤተክርስቲያን እርሱን ከተመለከተች ትራመዳለች፣ የራስዋን ድክመት ከተመለከተች ግን ትሰምጣለች።

√ “የሌሊቱ አራተኛ ዋዜማ” (25) በድካምና በጭንቀት የተሞላና የሌሊቱን ሙሉ ጨለማ የተሸከመ፣ ከዘጠኝ እስከ አስራሁለት ሰዓት ያለው ጊዜ ነው። ሰዓቱ ሙሉ ሌሊት ቢሆንም፣ ለአዲሱና አሸናፊ ፀሐይ ቅድመ-ሁኔታ ነው፥ “በምሽት ጊዜ እነሆ ሽብር ይሆናል፤ በማለዳ ግን ይጠፋሉ” (ትንቢተ ኢሳይያስ 17፥14)። አራተኛ ዋዜማ ኢየሱስ ከሙታን የሚነሳበት ጊዜ ነው። አሁን ተነስቶ በባህር ላይ እየተራመደ ይመጣል፥ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት በእርሱ ላይ ኃይል አይኖረውም። “መንገድህ በባህር መካከል ነበረ፣ ያለፍከውም በታላላቅ ወንዞች በኩል ነበረ” (መዝሙር 77፥19)።

“የመጀመሪያ ዋዜማ የሕግ፣ ሁለተኛው የነቢያት፣ ሦስተኛው የጌታችን በሥጋው መምጣትና፣ አራተኛው የጌታችን በክብሩ መምጣት ያመለክታል” (Augustine †430)

በባህር ላይ መራመድ አራት ጊዜ የተደገመ የንባቡ ጭብጥ ነው (25.26.28.29)። ደቀ መዝሙርት እንዲያደርጉ የሚፈለግ ይህ ነው።

√ “ና”(29)፥ በቃሉ መሰረት፣ እንደ እርሱና ከእርሱ ጋር በውቅያኖስ ላይ ለመራመድ እንጋበዛለን። በራሳችን ሳይሆን በእርሱ በመተማመን ካልሆነ በስተቀር ማሸነፍ አይቻልም፥ “ከወጥመዶች ሁሉ ስለሚያድነኝ ሁልጊዜ ወደ እርሱ እመለከታለሁ”(መዝሙር 25፥15)።

Leave a reply