የቅዱስ ቁርባን (A-OT-CorpusDomini)

የቅዱስ ቁርባን (A-OT-CorpusDomini)

√ ሁሉም ነገር በአንድ ቁራጭ። የቅዱስ ቁርባን ክብረ በዓል በአንድ ቁራጭ ህብስት ውስጥ ሁሉም እንደሚገኝ የሚገልጽ ክብረ በዓል ነው። ምክንያቱም ሁሉም ነገር በአንድ ፍርፋሪ ውስጥ ይገኛል። ሁሉም ነገር እንዲኖር ትንሽ የህብስት ቁራጭ በቂ ነው።

የክርስቶስ ሥጋና ደም ክብረ በዓል ነው። ግን ክርስቶስ ሕያው ነው ወይስ ሞቷል? ክርስቶስ ሕያው ነው። ሥጋውስ ሕያው ነው ወይስ ሞቷል? የክርስቶስ ሥጋ ሕያው ነው (የሞተ ቢሆን አስከሬን ይባል ነበር)። ሥጋው ሕያው ከሆነ ደግሞ ከሥጋው ጋር ነፍስም አለች። ስለዚህ የኢየሱስ ሥጋ ባለበት የኢየሱስ ነፍስም አለች፣ ምክንያቱም ነፍስ ለሥጋ ሕይወት የሚሰጥ ምንጭ ከሆነ፣ ሥጋ ባለበት ነፍስም ደግሞ አለች።

> የኢየሱስን ሥጋና ደም ስንቀበል የኢየሱስን ነፍስም እንቀበላለን። ስለዚህ የኢየሱስ ሰብአዊነት በሙሉ (ሥጋ ደምና ነፍስ) በቅዱስ ቁርባን ይገኛል። የኢየሱስ ሰብዓዊነት ደግሞ ከመለኮቱ ፍጹም ተለይቶ አያውቅም፥ የናዝሬቱ ኢየሱስና የእግዚአብሔር ልጅ ሁለት የተለያዩ አካላት አይደሉም። ስለዚህ የኢየሱስ ሥጋ ባለበት ነፍሱም አለች (ሰብአዊነቱም አለ ማለት ነው) እና የኢየሱስ ሰብአዊነት ባለበት መለኮቱም አለ (የአብ ልጅ አለ ማለት ነው)።

> ኢየሱስ ግን “እኔን የሚያይ አብን ያያል” ብሎ ስለተናገረ፣ ወልድ ባለበት አብም ይገኛል። አብና ወልድ ባሉበት ደግሞ ከአብና ከወልድ የሚሰርፅ መንፈስ ቅዱስም ይገኛል። ስለዚህ በአንድ የህብስት ቁራጭ ሦስት ሥላሴም አሉ ማለት ነው።

> በአንድ የህብስት ቁራጭ ውስጥ ሥጋና ደም፣ ነፍስና መለኮት፣ እንዲሁም ሥላሴም አሉ። ሌላስ ምን እንጨምር? እግዚአብሔር በሚገኝበት፣ መላው የተፈጠረ ዓለም ይገኛል፣ ምክንያቱም የተፈጠረ አለም በእግዚአብሔር ላይ ምንም ነገር አይጨምርም (መጨመር ቢችል እግዚአብሔር ፍጹም አይባልም ነበር)። ስለዚህ ሥላሴ ባለችበት፣ በቅዱስ ቁርባን ቁራጭ ውስጥ መላው ፍጥረቷም አለች። እግዚአብሔር ደግሞ ዘላለማዊ ስለሆነ፣ በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ያለፉትና ወደፊት የሚሆኑትም ነገሮች ይገኛሉ።

√ በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ሁሉም ነገር ይገኛል። ቅዱስ ቁርባን ሁሉን ነገር የሚሸከም ከሆነ ደግሞ፣ እግዚአብሔር በሚሰማው አይነት ስሜት ይሸከመዋል (የእግዚአብሔርን ፍቅርና ስቃይ፣ የፍጥረትን ፍቅርና ስቃይ ይሸከማል ማለት ነው)። የቀረ ነገር አለ? ምንም የቀረ ነገር የለም። በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ሁሉም ነገር አለ።

> በዛሬ ክብረ በዓል በፍቅሩ ፀሐይንና ከዋክብትን የሚስበውን እግዚአብሔር እናከብራለን። ምክንያቱም መላው ፍጥረት ወደዚህ ወደአንዱ የህብስት ቁራጭ ይሳባል። ስትቆርቢ መላው አጽናፈ ሰማይ በእጅሽ ነወ የሚሆነው። ሥጋሽም የእግዚአብሔር ድንኳን ይሆናል።

√ በምትቆርቢበት ጊዜ በሥጋሽ ውስጥ የእግዚአብሔር ሥቃይም አለ። ምክንያቱም የኢየሱስ ሥጋና ደም ተለያይተዋልና። ደሙ ፈሰሰ። በእጅሽ ያለው መላው የአምላክና የአጽናፈ ሰማይ ስቃይ ነው።

√ ከዚያ ደግሞ ትመገባለህ። እናም እርሱ (ክርስቶስ) ትሆናለህ። በመለኮታዊ መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር ትዋሕዳለህ። ይህን ለመረዳት እምነት ያስፈልጋል። በመስቀል ላይ የኢየሱስ መለኮት ተሰውሮ ነበር፣ ሰብአዊነቱ ግን ይታይ ነበር። በቅዱስ ቁርባን ሁለቱም የተሰወሩ ናቸው። ስለዚህ ቅዱስ ቁርባን የበለጠ እምነት ይጠይቃል።

√ የበለጠ ለመረዳት ወደ ኢየሱስ ልብ መግባት ያስፈልጋል። አንድ ቀን፣ ደቀመዛምርቱ ስለ ዓለም መጨረሻ ሲጠይቁት፣ ኢየሱስ ስለ ራሱ ሲናገር፣ ምስጢራዊ በሆነ ዕረፍተ ነገር ይመልስላቸዋል፥ “ሥጋ ወዳለበት ቦታ ንስሮች ይሰበሰባሉ” (ማቴዎስ 24፥28)። (የግሪክ ቃል “οι αετοι” “ንስር” ተብሎ ይተረጉማል እንጂ “አሞራ” ተብሎ አይተረጉምም)

> ኢየሱስ በአለም መጨረሻ በሚመለስበት ጊዜ የት ይገኛል? በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ለዘላለም በመኖሩ ይገኛል።

> ሥጋውን መለየት የሚችሉት ግን እነማን ናቸው? የትስ ይሆናል? ንስሮች የት እንደሚሰበሰቡ ተመልከት። ንስሮች በሚሰበሰቡበት ስፍራ ሥጋው በዚያ ይኖራል።

> ሥጋና የደም፣ ነፍስና መለኮት፣ ሥላሴና መላው አጽናፈ ዓለም በስጋው ውስጥ መኖራቸውን መለየት የሚችሉ እነዚህ ንስሮች እነማን ናቸው? ንስሮቹ እምነት ያላቸው እና በቅዱስ ቁርባን ውስጥ በእውነት ክርስቶስ መገኘቱን የሚያምኑ ናቸው።

√ ኢየሱስ ሆይ፣ የት ትኖራለህ? በቅዱስ ቁርባን መለኮታዊ ቆራጭ ውስጥ እንደምኖር የሚያምኑ ሰዎች ለቅዳሴ በሚሰበሰቡበት ቦታ ውስጥ እኖራለሁ። በቅዱስ ቁርባን የሚምኑ እንደ ንስሮች ስለታም ዓይን፣ አድካሚ ያልሆነና የተመቸ አበራር፣ ለማይሳሳት ምርመራ የተፈጠረ ማሽተት ያላቸው ናቸው፥ “ንስሮች እዚያ ይሰበሰባሉ”

> እግዚአብሔር የንስርን ዓይን ይስጠን። አዎ፣ እኛ በህብስቱ ክርስቶስን መለየት የምንችል ቅዱሳን ንስሮች ነን።

Leave a reply