[K3] ለዘመናት የተጠበቀ ክስተት፥ የፀሐይ የቀለበት ግርዶሽ፣ የጊዛ ፒራሚድና ላሊበላ

[K3] ለዘመናት የተጠበቀ ክስተት፥ የፀሐይ የቀለበት ግርዶሽ፣ የጊዛ ፒራሚድና ላሊበላ

“እግዚአብሔር ሰማያትን በቃሉ፣ በሰማይ የሚገኙትን ፍጥረቶች በትእዛዙ ፈጠረ” (መዝሙረ ዳዊት 33፥6)

√ በሚቀጥለው ሰኔ 14 የሚታይ የፀሐይ ግርዶሽ በዓመት ረጅሙ ቀን ውስጥ (በአስትሮኖሚ መሰረት ይህ ቀን የ summer solstice ሲባል፣ በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ላይ የፀሐይ ጨረሮች ለሰሜን ዋልታ ቅርብ በሚሆኑበት ጊዜ በአመት አንድ ጊዜ የሚከሰት ነው) እና በጋላክቲክ የወገብ መስመር ላይ የሚፈጸም ነው (galactic equator ደግሞ የ Milky Way የወገብ መስመር ነው)። ይህ ክስተት በመቶ ወይም በሺ ለሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ የማይደገም ልዩ ክስተት ነው።

የዚህ ታላቅ የሰማይ ክስተት ጥናት አስገራሚ ሆኖ አልቀረም፥ በምድራችን ጥንታዊ ሐውልቶች ውስጥ በምስጢር ተጽፎ የሚገኝ ክስተት ነው፣ በተለይም ከ Stonehenge (UK)፣ ከ Giza (Egypt)፣ ከ Lalibela (Ethiopia) እና ከ Sana’a (Yemen) ጋር ይገናኛል።

√ የ Stonehenge የድንጋይ ሐውልት በ Scotland ውስጥ ታላቁ የግብፅ ፒራሚድ በተሠሩበት ዘመን ከክርስቶስ በፊት በ3200 አካባቢ የተገነባ ሐውልት ነው። ይዘቱ ከተለያዩ የድንጋይ ቀለበቶች የተሠራ የክብ ቅርጽ ያለው ነው።

> ይህ ካልን ወድያ፣ ሰኔ 14 በዚህ ታሪካዊ እና ምስጢራዊ ቦታ ላይ አንድ ለየት ያለ ክስተት ይከሰታል፥ 1) በግንባታው ጫፍ ላይ የተቀመጠ “Heel Stone” በሚባል በዋንኛው ድንጋይ ላይ ፀሐይ ትወጣለች፣ 2) ጋላክቲክ ወገብ (galactic equator)፣ ፀሐይ፣ ጨረቃና ምድር በአንድ መስመር ላይ ይሰለፋሉ።

√ በፀሐይ ግርዶሽ ቀን፣ ሌላ ልዩ ክስተት በግብጽ ውስጥ በጊዛ በታላቁ ፒራሚድ ላይ ይከሰታል።

> በዚህ ቦታም ብርሀን በሚጨለምበት ሰዓት፣ ፀሐይና ጨረቃ በሰማይ ላይ ካላቸው አቀማመጥና በፒራሚዱ ውስጥ የንጉስ ክፍልና የንግስት ክፍል ካላቸው አቀማመጥ ጋር አስደናቂ ተመሳሳይነት ያለው ክስተት ይፈጸማል። ፀሐይና ጨረቃ በሰማይ ያላቸው አቀማመጥ በታላቁ ፒራሚድ ውስጥ ያለውን የሁለቱ ክፍሎች (የንጉስና የንግስት ክፍል) አቀማመጥ በትክክል ይደግማል ማለት ነው።

> በተጨማሪም፣ ፀሐይና ጨረቃ በ Galactic Equator መስመር ላይ በትክክል ተደራርበው ይሰለፋሉ። ሲደራረቡ ደግሞ ጨረቃ የፀሐይን ክብ መሀል እያቋረጠና ፀሐይ የጨረቃን ክብ መሀል እያቋረጠ፣ በቀጥታ በፒራሚዱ ጫፍ መስመር ላይ የአሣ ቅርጽ (ወይም የህይወት አበባ የሚባል የለውዝ ስዕል) ይፈጠራል።

> በዚህ ቅጽበት፣ በፒራሚድ ውስጥ ያሉትን የንጉስና የንግስት ክፍል መሀሎች የሚያገናኝ መስመርና የ Galactic Equator መስመር በትክክል አንድ አይነት አቀማመጥ ይኖራቸዋል።

√ ይህ አስደናቂ ክስተት በክርስትና ታሪክ በአለም ውስጥ ታላቅ ሚና የተጫወተችውን የኢትዮጵያ አገር ያካትታል።

> ሰኔ 14 የላሊበላ ቅድስት ከተማ በጸሐይ ግርዶሽ ትሸፈናለች። በንጉስ ላሊበላ ትእዛዝ በዚሁ ከተማ 11 አብያተ ክርስቲያናት አልተገነቡም እንጂ በዓለት ውስጥ ተወቅረው ተቀርጿል። በዚህ አማካይነት በምድር ላይ ካሉት እጅግ አስደናቂ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ተፈጠረ።

> ግርዶሹን ለመግለጽ በተከፈተ በ NASA ድረ ገጽ ላይ እንደሚታይ፣ የጨረቃ ጥላ ዋና መስመር ላሊበላን ያቋርጣል ብቻ ሳይሆን፣ በትክክል በአስራ አንዱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል በማለፍ፣ የዮርዳኖስን ወንዝ መስመር እየተከተለ፣ የተቀደሰውን ስፍራ ለሁለት ያቋርጣል።

√ በእነዚህ ግዙፍና ጥንታዊ መዋቅሮች ውስጥ፣ ብዙን ጊዜ 3፣ 7 እና 11 ቁጥሮች ይገኛሉ። ለምሳሌ የ Stonehenge ሐውልት ዋና ቀለበት 56 ድንጋይ አለው (5+6=11)፤ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት 11 ናቸወ… እነዚህ ቁጥሮች በግርዶሽ ሰማያዊ መገጠሚያዎች ላይም ይታያሉ።

√ የበለጠ ማወቅ ከፈለጋችሁ፣ የሚከተለው ቪዲዮ ፀሐይ፣ ጨረቃና ምድር galactic ወገብ መስመር ላይ በመሰለፋቸው የሚቀርጹትን የጂኦሜትሪ ቅርጾች ያሳያል። የህይወት አበባ ቅርጽ (ለውዝ) በሰማይ ላይ በመቅረጽ፣ የዚህ ግርዶሽ ክስተት እንዴት ልዩ እንደሆነ ያሳያል… Solar eclipse June 21 Stonehenge, Pyramids

√ ብዙውን ጊዜ ታሪካዊ የክርስቶስና የማርያም ምስሎች በህይወት አበባ ውስጥ ይቀረጻሉ (ለምሳሌ እመበታችን ማርያም ከልጇ ጋር ወይም ባረገዘች ሴት መልክ በለውዝ ቅርጸ ውስጥ ትቀረጻለች፥ ማህፀኗ በየህውት ፍሬ በክርስቶስ የተሞላ ነው)። የለውዝም ቅርጽ የሴትና የህይወት ምልክት ነው። የሕይወት አበባ የዓሣም ቅርጽ አለው፥ አሣ ከመጀመርያ የክርስቶስ ምልክት ነው። የአሣ ቅርጽ የሚፈጠረው ሁለት ክቦች በመገናኘታቸው ነው፥ የአምላክ ወይም የመለኮት ክብና የሰው ወይም የሰብአዊነት ክብ (ክርስቶስ አምላክና ሰው ነው)።

 

√ ይህ ሁሉ በ Stonehenge እና በጊዛ ታላቁ ፒራሚድ ውስጥ የሚገኘውን ጂኦሜትሪ የሚያረጋግጥ ይመስላል፣ እንዲሁም በዮሐንስ ራዕይ የተገለጸውን የእየሩሳሌም ጂኦሜትሪ እና በፕላቶ ጽሑፎች ውስጥ ያለውን የማግኒሲያ የደስታ ከተማ ጂኦሜትሪ የሚያረጋግጥ ይመስላል።

የበለጠ መመርመር ጠቃሚ ሳይሆን አይቀርም…

“አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፣ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፣ አይደክምም፣ አይታክትም፣ ማስተዋሉም አይመረመርም” (መጽሐፈ ኢሳያስ 40፥28)

Leave a reply