ቅድስት ስላሴ (A-OT-Trinity)

ቅድስት ስላሴ (A-OT-Trinity)

1ኛ ንባብ፥ ዘጸአት 34፥4-6.8-9

√ “እግዚአብሔር በደመና ወርዶ ከሙሴ ጋር በዚያ ቆመ” (ኦሪት ዘጸአት 34፥5)። እግዚአብሔር በደመና ምስል ይገለጻል። ደመና ግን ጭጋግና ጨለማ ነው፥ ምንም ነገር ማየት አይቻልም። በጭጋግ ውስጥ ግን ምንም ባይታይም፣ ሰው በውስጡ እየኖረ አለማየትን ይለምዳል። ዋናው ነገር ማየት አይደለም፣ አለማየትን መልመድ ነው እንጂ።

√ እግዚአብሔር በደመና ምስል ውስጥ ይገለጻል፣ ደመና የመለኮታዊ ጭጋግ ምስል ነው፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር የማይመረመር አምላክ እና የማይታወቅ ምስጢር ነው። በሚገለጽበት ጊዜ በደመና ተደብቆ ምስጢር መሆኑን አይተውም። ይልቁንም ነፍሳችንን በምስጢሩ ያሳትፋል።

> እኛ በደመና ውስጥ አናይም እንጂ በደመና ውስጥ እንደገባን እናውቃለን። እግዚአብሔር አይታይም እንጂ ወደ እርሱ ስንቀርብ በመለኮታዊ ደመና እንደገባን እንገነዘባለን። ነገር ግን እግዚአብሔር በሚገለጽበት ጊዜ ምስጢሩን አያስወግድም እንጂ በምስጢሩ ያሳትፈናል። ደመና እግዚአብሔር ምስጢሩን ሳይተው በምስጢሩ እንደሚያሳትፈን የሚገልጽ ምስል ነው። እግዚአብሔር ከእኛ በላይ ነው፥ በእርሱ እንታቀፋለን እንጂ እኛ እርሱን አናቅፍም።

√ “አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመግለጽ ምንም እንኳ ምስሎችን ቢፈልግ፣ ብልህተኛ ቢሆንም፣ አዳዲስ ምስሎችን የመፍጠር አቅም ቢኖረውም፣ ኃይል ይጎድለዋል። የኛ ፈጠራ በእግዚአብሔር ምስጢር መግባት ባይችልም ግን ምንም ችግር የለም፣ ምክንያቱም ነፍሳችን ያለችው የመመርመር ፍላጎትና ምኞት ፀሐይንና ከዋክብትን በሚስብ በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ተሳታፊ በመሆኗ ትረካለች” (Dante Alighieri †1321)

> ስለ ሥላሴ ስናስብ እንዳወቅን ማሰብ የለብንም። ሥላሴን አውቄያለሁ ብዬ ከገመትኩ ያወቅሁት ሥላሴ አይደለም።

> አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ፥ ሥላሴ ሦስት አካላት ናቸው። እንቁጠራቸው! “አንድ ሁለት ሦስት”… ሥላሴ ማለት ነው! ይህ አካሄድ ግን ስሕተት ነው፣ ምክንያቱም እግዚአብሔርን አባዝተናል! ማለት ያለብን “አንድ አንድ አንድ” ነው። እግዚአብሔርን ሦስት ጊዜ እንደግማለን፣ ያለው ግን አንድ አምላክ ብቻ ነው።

> አብ ስንል ሙሉ አምላክ ነው፣ ወልድ ስንል ሙሉ አምላክ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ስንልም ሙሉ አምላክ ነው፥ ነገር ግን ሦስት አማልክት አይደሉም። ታድያ ለምን ሦስት ጊዜ ይደገማል? ምክንያቱም አብ ወልድ አይደለም፣ ወልድም መንፈስ ቅዱስ አይደለም እና መንፈስ ቅዱስም አብ አይደለም። ስለዚህ በፍጹም ልዩ ናቸው፣ በፍጹም ደግሞ አንድ ናቸው።

> መመርመር አይቻልም፣ ነገር ግን መለመን እና መሳተፍ ይቻላል። በእርግጥ፣ ሰው የሚለምን ከሆነ የሚለምነውን አስቀድሞ ያውቃል። የምናውቀው ግን ምስጢሩን ስለያዝን ሳይሆን ምስጢሩ ስለያዘን ነው።

√ ፍጹም ተሳትፎ በመንግስተ ሰማይ ቢፈጸምም፣ ይህ ተሳትፎ ቀድሞ በዚህ ምድራዊ ህይወት ላይ ይጀምራል። የክርስትና ሕይወት እንዲህ ነው፥ በእግዚአብሔር ሕይወት በሆነ በቅድስት ሥላሴ ሕይወት መሳተፍ ነው። እግዚአብሔር ሁለንተናዊ መስህብ ነው (ፀሐይንና ከዋክብትን የሚስብ ነው)። መኖር ማለት ራሳችንን ወደ እግዚአብሔር እንድንሳብ መፍቀድ ማለት ነው። መንገዱ ኢየሱስ ነው፥ “መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ” (ዮሐንስ 14፥6)።

√ በመጨረሻ፣ ስለ ቅድስት ሥላሴ ለማወቅ የሚከተለው ምሳሌ መመልከት ይቻላል።

> አሁን እያሰብክ ነው።

> እንድምታስብ ታውቃለህ፣ ማለትም እንድምታስብ እያሰብክ ነው (የምታስብና እንድምታስብ የምታስብ አንተ ራስህ ነህ)። ስንት ናችሁ? አንድ። የምታስብ ነህ እና የሐሳብህ ይዘት ነህ። ሁለት ግን አይደላችሁም።

> እንድምታስብ ስታስብ፣ የምታስብና የሐሳብህ ይዘት በመሆንህ ትደነቃለህ። ይህላችሁ፥ የሚያስብ፣ የታሰበና የሁለቱ መደነቅ አገኝተናል። ሦስት የተለዩ ነገሮች አሉ፣ እነርሱ ግን አንድ ነገር ብቻ ናቸው! ቅድስት ሥላሴ ከዚህ ምሳሌ ጋር ይመሳስላል።

Leave a reply