የፋሲካ 5ኛ እሁድ (A-PHASIKA-5)

የፋሲካ 5ኛ እሁድ (A-PHASIKA-5)

ወንገል፥  ዮሐንስ 14,1-12

√ መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ (6)፣ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም፥ ኢየሱስ ወደ አብ የሚመራ መንገድ ነው። ወደ ሰማይ መድረስ የምንችል፥

> ትእዛዞቹን በመፈጸም

> በእምነት አማካይነት፣ ምክንያቱም ጌታችን የመጣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኝ ነው” (ዮሐንስ 3,15)

> የእርሱን ምሳሌ በመከተል፣ ምክንያቱም ክርስቶስን ካልመሰለ ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም

> ከሁሉ በላይ፣ ክርስቶስ ስጋን ለብሶ በመስቀል ላይ ስለሞተ

> ክርስቶስ ከእርሱ ጋር አንድ ተፈጥሮ ያለውን አባቱ ስለገለጸ።

√ ኢየሱስ መንገድ ነው። እርሱ ሰማይና ምድርን የሚያገናኝ ብቸኛው መንገድ ነው። በመካከላችን በኖረበት ጊዜ በዚህ ምድር ላይ የእርምጃዎቹን ግልጽ ዱካዎች ትቶአል። የእርሱ እርምጃዎች የዘመናት ብልሽትና የጠላት ሸፍጥ ማጥፋት ያልቻሉ የማይሰረዙ እርምጃዎች ናቸው።

“መንገድ የሆነው የሰው ፋና ወደሌለው ቆሻሻ አይመራንም። እውነት የሆነው በሐሰት አያፌዝብንም። ሕይወት የሆነው በስውር አሳልፎ አይሰጠንም” (Hilary of Poitiers †367)

“መንገዱ በእውቀትና በጽድቅና በኩል ደረጃ በደረጃ የሚያሳድገን ጉዞ እንደሆነ እንረዳለን። ከፊታችን ለሚጠብቀን የተባረከ የእግዚአብሔርን እውቀት ለማገኘት፣ እስከ መጨረሻ ኪሎሜቴር ድረስ እንታገላለን።  እየሱስ እውነተኛ መንገድ ነው፣ ግራ የሚያጋባ መታጠፊያ የሌለበት ወደ አብ የሚመራ ቀጥ ያለ መንገድ ነው። ምክንያቱም በእርሱ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም” (Basil the Great †379)

√ “ልጆች እናቶቻቸውን ሲሰሙ እና አብረዋት ሲንቀሳቀሱ ቋንቋቸውን መናገር ይማራሉ። እኛም እየሱስን በመቅረብና ቃላቱን፣ ድርጊቶቹንና ልቡን በመመልከት፣ በጸጋው አማካይነት፣ እንደ እርሱ መናገር ፣ መሥራትና መመኘት እንማራለን። እርግጠኛ መንገድ ይህ ነው” (Francis de Sales †1622)

“የትኛውን ጉዞ ትመርጣለህ? እኔ መንገድ ነኝ። የት መሄድ ትፈልጋለህ? እኔ እውነት ነኝ። የት መሆን ትፈልጋለህ? እኔ ሕይወት ነኝ” (Augustine †430)

Leave a reply