[UR7] ሁለት ቤተክርስቲያንና ሁለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት

[UR7] ሁለት ቤተክርስቲያንና ሁለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት

ብጽአት Anne Catherine Emmerich, 1820፥

“የሁለት አብያተክርስቲያን እና የሁለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በጣም አስደናቂ ራእይ አይቻለሁ… መላው ቤተክርስቲያን በጥቁር ታሽጋ ነበርና በውስጧ የሚከናወነው ሁሉ በድቅድቅ ጨለማ የተሞላ ነበረ… የሐሰት ቤተመቅደስና የሐሰት አምልኮን አየሁ… የሐሰት ቤተክርስቲያን ሲያድግ አይቻለሁ። ሁሉን ዓይነት መናፍቃን ወደ ከተማ ሲጎርፉ አየሁ። የካህናት መንፈሳዊነት እየቀዘቀዘ ሲመጣና የጨለማ ክበብ በጣም እየሰፋ ሲሄድ አየሁ… በየቦታው ካቶሊካዊያን ሲጨቆኑ፣ ሲበሳጩ፣ ሲገደቡና ነፃነታቸው ሲነፈግ አይቻለሁ። አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተው ነበርና መከራ በሁሉም ቦታ ተስፋፍቶ ነበር…

“እንደገና በራዕይ ሌላ ነገር አየሁ… ቤተክርስቲያን በታላቅ ጭንቀት በወደቀችበት ጊዜ ከመከራ ነፃ ወጣች… ቅድስት ድንግል ማርያም ነጠሏን በበቤተክርስቲያን ላይ ስትዘርጋ አየሁ። ሁሉም ነገር ሲታደስ እና ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ ቤተክርስቲያን አየሁ…”

Leave a reply