ፋሲካ፥ የነገሮችን ይዘት ለመገምገም እንማር (EASTER: seeing the essence of things)

ፋሲካ፥ የነገሮችን ይዘት ለመገምገም እንማር (EASTER: seeing the essence of things)

የእግዚአብሔር ህግ ፍጹምነት በአሮጌው እና በአዲሱ መካከል ባለው አስደናቂ አንድነት ይገለጻል። በዘላለማዊ አምላክ ጥበበኛ እጅ (ማለትም በመንፈስ ቅዱስ) የሚደረግ ሁሉ በዋጋ የማይተመን ስፌት ይመስላል።

✓ ፋሲካ የሚለ ቃል ከዕብራይስጥ ‘ፐሳህ’ ከሚል ቃል የመጣ ነው። ትርጉሙም ‘ሽግግር’ ማለት ነው። ስለሆነም፥ ሁለቱም ክስተቶች በሽግግር ተለይተው ይታወቃሉ
1. የአይሁድ ፋሲካ፣ ከአራት መቶ ዓመታት ስደት በኋላ ከግብጽ ባርነት ወደ ስጋዊ ነፃነት በሙሴ አማካይነት ተፈጽሞአል።
2. የክርስትና ፋሲካ፣ ከአዳም ኃጢአት በኋላ ከሰይጣን ባርነት ወደ መንፈሳዊ ነፃነት በክርስቶስ መሥዋዕት አማካይነት ተፈጽሞአል።
ክርስቶስ የሰማይን በር ስለከፈተልን፥ እንደየትጋታችን ቢሆንም ወደ መጀመርያው ገነት መመለስ እንችላለን።

✓ አሁን የሁለቱን ተመሳሳይነት እንመልከት
የአይሁድ ሕግ በአይሁድ ፋሲካ ወይም በቂጣ በዓል ቀን ለመስዋእት ከቀረበ በግ ጋር፣ እርሾ ያልገባበት ቂጣ እና መራራ እፅዋት እንዲበላ ያዝዛል፥
1. በግ የንጽህናና የየዋህነት ምልክት ነው፣ በዚህ ምክንያት በግ ለእግዚአብሔር ለምስጋና ሥነ-ሥርዓት የሚሰዋ እንስሳ ነው
2. እርሾ ያልገባበት ቂጣ የችኩልነት ምልክት ነው፥ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመሄዳቸው በፊት በመጨረሻው መቅሰፍት ሌሊት፣ አይሁዳዊያን እጭር ጊዜ ስለነበራቸው ለጉዞ ለመነሳት ይቸኮሉ ነበር
3. መራራ እፅዋት የወቅቱ የጭንቀት ትዝታ ምልክት ናቸው (የግብፃውያን የበኩር ልጆች ሞት ጭንቀት)።

✓ አሁን የንፅፅር ትንታኔ
1. በአዲስ ኪዳን፣ በጉ ከእንስሳ (✓ በአለም ውስጥ ወዳለው ቁሳቁስ) ወደ ሰው ይለወጣል፣ እንዲሁም ወደ አምላክ (✓ ከአለም ውጭ ወዳለው መንፈስ) ይለወጣል።
በትንቢተ ኢሳያስ “ግፍና ችግር ደረሰበት፣ ይሁን እንጂ ምንም አልተናገረም፣ ለመታረድ እንደሚወሰድ ጠቦትና በሽላቶቹ ፊት ጸጥ እንደሚል በግ ዝም አለ እንጂ አልተናገረም” (53፥7) የሚል ተጽፎ ይገኛል። በዮሐንስ ወንጌል “እንሆ የአለምን ኃጢአት የሚያጠፋ የእግዚአብሔር በግ ይህ ነው” (1፥29) የሚል ተጽፎ ይገኛል። በዮሐንስ ራእይ ደግሞ “በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሞ” (14፥1) አሸናፊ ሆኖ ይገለጻል።
2. የዳቦ ምልክት ደግሞ ወደ ሌላ ትምህርት ይመራናል።
በዮሐንስ ወንጌል 6፥32-35 “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ከሰማይ የወረደውን እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤ እውነተኛውን እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው”… “የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ፈጥሞ አይራብም፤ በእኔ የሚያምን ፈጽሞ አይጠማም” ተጽፎ ይገኛል።
በሙሴ የተሰጠ ዳቦ (ዘጸአት 16፥13-16) ህይወትና የመንፈስ ጤና የማይሰጥ የበረሐ መና ነው። ስጋን ብቻ የሚያረካ የቂጣ ዳቦ የሙሴ ሕግ ምሳሌ ሆኖ እርሾ ወይም ፍቅር የሌለው ዳቦ ነው።
3. በመጨረሻ፣ መራራ እፅዋትን ከስቅለት ጨለማና ስቃይ ጋር፣ ከአባት በኩር ልጅ ሞት ጋር፣ ከሐሞትና ከሆምጣጤ ጋር እንዴት ማነፃፀር አንችልም? (ማቴዎስ 27፥34-48)

በዚያ ሐሙስ ምሽት ላይ፣ ከመታሰሩ በፊት ኢየሱስ ዳቦን ይዞ፥ “ተቀበሉና ሁላችሁም ከእርሱ ብሉ፣ ይህ ስለ እናነት የሚሰጥ ስጋዬ ነውና”፣ ጽዋውን ይዞ፥ “ተቀበሉና ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ፣ ይህ የደሜ ጽዋ ነውና፣ ስለናንተና ስለ ብዙዎቹ ለኃጢአት ሥርየት የሚፈስሰው የአዲሱና የዘላለማዊ ኪዳን ደም ነው” ብሎ ተናገረ።
ከላይ የተጠቀሱትን ቃላት ትርጉም እንመርምር
ዳቦ የህይወት መሠረታዊ ምግብ ነው፥ ያለ ዳቦ ማንም ሰው ይሞታል! ወይን ጠጅና ደም ደግሞ ማነፃፀር እንችላለን፥ ወይን ጠጅ የወይን ተክል ጭማቂ ነው፥ ደም ለሥጋ አካል ጭማቂ ነው። ያለ ደም ማንም ሰው አይኖርም!
ስለዚህ ያለ ዳቦ-ክርስቶስ-ፍቅር በመንፈስ እንሞታለን! ያለ ወይን-ደም-ፍቅር እስከ ሞት ድረስ በጨለማ ውስጥ እንጓዛለን!

“ደሙ ባላችሁበት ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ እኔም ደሙን በማይበት ጊዜ አልፌአችሁ እሄዳለሁ፤ በእናንተ ላይ ምንም አይነት መቅሠፍት አይደርስባችሁም” (አሪት ዘጸአት 12፥13)።
በሌሊት፣ በምንኖርበት ዓለም ላይ፣ ከሚከሰት የሰይጣን ንዴት ለመታደግ ተስፋ ማድረግ የምንችለው፣ በክርስቶስ ድንቅ ምሳሌ በመመገብ ብቻ ነው። የዮሐንስ ራእይ ግልጽ ነው፥ ማኅተም የታተሙባቸው 144 ሰዎች ናቸው፣ 1 + 4 + 4 = 9 ወይም 3 x 3 = በሦስት እጥፍ የተባዛ ኃይል ነው።
በተጨማሪም፣ ከ 12 x 12 ጋር እኩል ስለሆነ፣ 144 መላውን የሰው ዘር የሚወክሉና በሁሉ ምድር ላይ የተባዙ የአሥራ ሁለት የእስራኤል ነገዶች ምልክት ነው።

በግምባር ላይ የሚታተም ማኅተም በትክክል የበግ ደም፣ የመስቀል ምልክት፣ ውሃና እሳት፣ በመቀላቀል አዲስ ነገር የሚሆኑት ቁሳቁስና መንፈስ ነው። ውሃ ከእሳት ጋር ሲቀላቀል አይተንምን? የኛ ስጋ ከመንፈስ ጋር ሲቀላቀል አይድንምን?
የዚህ አለም ባልሆነ በመንፈስ በሚገዛበት ጊዜ፣ አለማዊ ሰው ወደ አዲስ ነገር አይለወጥምን?
እንግዲያው አይናችንን እንክፈትና የነገሮችን ይዘት በተሻለ ለመገምገም እንማር።

Leave a reply