[UR4] የቤኔዲክት ፲፮ አወጣት አሁንም ክፍት ነው (2) The withdrawal of Ratzinger is still open

[UR4] የቤኔዲክት ፲፮  አወጣት አሁንም ክፍት ነው (2) The withdrawal of Ratzinger is still open

በአሁኑ ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ በሁሉም ደረጃ ውስጥ አለመግባባትና መከፋፈል መኖሩ የማይካድ ሐቄ ነው። ታዲያ ይህን የተቋጠረ ነገር እንዴት ልንፈታው እንችላለን?

እንደኔ አስተያየት ሁለት መንገዶች አሉ፣ አንዱ ለወደፊት የሚፈታ ሲሆን ሌላው ግን ለአሁን የሚሆን ነው። ሁለቱም ግን የሚቃረኑ ሳይሆኑ፣ እንዲያውም እርስ በራስ የሚደጋገፉ ናቸው።

የመጀመሪያው መንገድ ቤኔዲክት ፲፮  በ2013 ለመልቀቅ ስለገፋፋቸው ምክንያቶች ጠለቅ ያለና ሚዛናዊ ጥናት ማካሄድ ነው፥ በእርግጥ የርሳቸውን ውሳኔ ሕገወጥ ማድረግ የሚችሉ ጫናዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ከሆነ፣ የፍራንሲስ መላው ጵጵስና ወዲያውኑ ሕገወጥ ይሆናል። ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ጥናት ለማካሄድ፣ ሁለቱም የዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ ፈፃሚዎች መጀመሪያ መሞት አለባቸው (ይህ ደግሞ ለማንም መመኘት የማንፈልግ ነገር ነው)።

ሁለተኛው መንገድ ቤኔዲክት ፲፮  ከስልጣን ለመልቀቅ ያቀዱትን አዲስ አፈፃፀም ጠለቅ ያለና የስውን ክብር የሚጠብቅ ትንታኔ ማድረግ ነው፥ ይህ ደግሞ አሁንም በፍጥነት ሊከናወን ይችላል።

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የቤኔዲክት ፲፮  የመጨረሻ ቃላት እንረዳለን፥

“ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከእንግዲህ የራሱ አይደለም፣ የሁሉም ሰው ነው፣ ሁሉም ሰው የእርሱ ነው። “ሁልጊዜ” እንዲሁም “ለዘላለም” ነው፣ ወደ ግል ኑሮ መመለስ የለም። የሐዋርያ ጴጥሮስ ስልጣን አካላዊ አገልግሎትን ለመተው የወሰንኩት ውሳኔ ይህንን አይሽርም። ወደ ግል ሕይወት አልመለስም […]። መስቀልን አልተውም፣ እንዲሁም ከተሰቀለው ጌታ ክርስቶስ ጋር በአዲስ መንገድ እቆማለሁ። ከእንግዲህ ቤተክርስቲያን የማስተዳደርን ስልጣን አልሸከምም፣ ነገር ግን በቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ የጸሎትን አገልግሎት አልተውም”።

ስለሆነም ቤኔዲክት ፲፮ የሐዋርያ ጴጥሮስ ስልጣን አካላዊ አገልግሎትን ትተዋል እንጂ ሙሉ በሙሉ የጴጥሮስን ስልጣን አልተዉም (የርዕሰ ለቃነ ጳጳሳት ነጭ ልብስ፣ የርዕሰ ለቃነ ጳጳሳት ስም፣ መኖሪያ፣ ሐዋርያዊ በረከቶች፣ ወዘተ.)። የጉዳዩ ዋና ነገር እዚህ ላይ ነው፥ “ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት” መባላቸው ብቻ ሳይሆን፣ የርሳቸው አዲስና ያልተለመደ የስልጣን መልቀቂያ መሠረት ነው።

በቤተክርስቲያን ሕግ፣ የሐዋርያ ጴጥሮስ ስልጣን ለሁለት እንደማይከፋፈል (አካላዊና መንፈሳዊ) ሁላችንም እናውቃለን። ነገር ግን ቤኔዲክት ፲፮ ስልጣን ላይ ነበሩና በስልጣን ያለው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቤተክርስቲያን ሕግ በማረምና በመሰረዝ፣ አዲስ ህግና ደንብ ሊያወጣ ይችላል። አዲሱ ህግ እውነተኛ ምክንያት ካለውና እግዚአብሔር ከሰጠው ህግ ጋር የማይጋጭ ከሆነ ተቀባይነት አለው።

ያለ ጥርጣሬ፣ በሐዋርያ ጴጥሮስ ስልጣን ውስጥ ሁለት አገልግሎቶችን መለየት (አካላዊና መንፈሳዊ፣ የሥራና የመሆን) በሕጋዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊሰራጭ የሚችል ሕግ ነው።

በላቲን እንደሚባል፣ ቤኔዲክት ፲፮ “potuit, decuit, ergo fecit”፥ (ማድረግ ይችሉ ነበር፣ መልካም እንደነበረ ፈርደዋልና ስለሆነም ፈጽመዋል)።

ይህ የቤኔዲክት ፲፮ ነፃና ሉአላዊ ውሳኔ በሐዋርያ ጴጥሮስ ወምበር ለፍራንሲስ የሕግን ግድቦች አቋቅሞአል፥ ማለትም የቤኔዲክት ፲፮ ተተኪ ለሥራ ብቻ የተገደበውን ስልጣን ወርሶአል እንጂ ሙሉና ወሰን የሌለውን ስልጣን አልወረሰም። ማለትም የቤኔዲክት ፲፮ ተተኪ “በቤኔዲክት ፲፮ ፍቃድ የሚሠራ” ነው።

ምናልባትም በይፋ የዚህን ውሳኔ ትርጉምና ስፋት ግልጽ መደረግ ነበረበት (ግን በግል ተደርጎ ሳይሆን አይቀርም)።

ለማጠቃለል፣ የቤኔዲክት ፲፮ ቃላት የፍራንሲስ ትርጉም የለሽ ከሆኑ ትምህርቶች ጋር የሚጋጩ ከሆነ፣ ጥፋቱ የቤኔዲክት ፲፮ አይደለም፥ እርሳቸው የካቶሊክ እውነትን በመከላከል በቤተክርስቲያን መድረክ ላይ ብቅ ማለት አለባቸው። ቤኔዲክት ፲፮ በእርግጥ እንደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት “መሥራት” ትተዋል እንጂ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት “መሆን” አልተዉም።

በመጨረሻ፣ የራሴ ግምት ምንም ቢሆንም፣ በቤኔዲክት ፲፮ “ግማሽ መልቀቂያ” መሠረት ግልጽ የሆነ ከሰማይ የተሰጠ መልእክት ሊኖር ይችላል። ያለበለዚያ ከአድካሚና አሰልቺ የሰባት ዓመታት ውዝግብ በኋላ፣ እስካሁን ድረስ ስልጣናቸውን ሙሉ በሙሉና ግልጽ በሆነ መንገድ ያስረክቡ ነበር። ይልቁንም የመጨረሻ ፍጻሜዎችን በመጠባበቅ አሁንም እዚያው በአቋማቸው ይፀናሉ።

Leave a reply