[UR3] የቤኔዲክት ፲፮ አወጣጥ አሁንም ክፍት ነው (1) The withdrawal of Ratzinger is still open

[UR3] የቤኔዲክት ፲፮  አወጣጥ አሁንም ክፍት ነው (1) The withdrawal of Ratzinger is still open

የሐዋርያ ጴጥሮስ መሪነት ክርስቶስ በተናገረው ቃላት ላይ ተመሰረተ፥ “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም” (ማቴዎስ 16፥18)።

ነገር ግን የዛሬ የካቶሊክ መሪዎች ካቶሊካዊ እምነትን በተደጋጋሚ እየደበደቡ ነው።

እግዚአብሔር ክልስ እንደነበረ ተብሎአል፣ ማርያም ተራ ልጅ እንደነበረች ተብሎአል (እናስ ያለ ሐጢያት የተፀነሰች አልነበረችምን?) ወይስ በእግዚአብሔር ላይ እንደተናደደች ተብሎአል (የፍጡራን ለእምነትና ለታዛዥነት ምሳሌ አይደለችምን?)። ከዚህ በፊት በሰው መሥዋዕት ብቻ የምትረጋጋ ፓቻማማ የምትባል ህይወት የሌላትና የደረቀች የደቡብ አሜሪካ ጣኦት ከማርያም ጋር በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ማስቀመጥ ተችሎአል። ለዚህ ሁሉ ok ተባለ። የክርስቶስ ወንጌል የጋብቻን ፍቺ ያልፈቀደ ምህረትን በመርሳት እንደሆነ፣ ሆኖም በክርስቶስ ጊዜ የድምጽ መቅረጫዎች ስላልነበሩ የወንጌልን ቃላት በትክክል ማወቅ እንደማንችለው ማለት ትችሎአል። ድርብ ok ተባለ። ሶዶም ከተማ የተቃጠለችው በግብረ ሰዶማዊነት ምክንያት ሳይሆን እንግዳን ባለመቀበል ምክንያት በማለት፣ ብሉይ ኪዳን ሳይጨመር በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ለሁለት ሺህ ዓመታት የሶዶም ጥፋት በተሳሳተ መንገድ እየተተረጎመ ነበር ለማለት ተችሎአል። የድርብ ok ድርብ ተብሎአል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ስደተኛ፣ እባብና ሰይጣን ተብሎአል። አራተኛ ok ተባለ። ቅዱስ ቀኖናዎችን የሚወቅሱት መሪዎችን ከነቀፍህ ግን ok የሚባል መልስ ከአምስተኛው ፎቅ እንደሚወርድ የሻገተ ሸክላ ይጨፈለቃል። እዚህ ላይ ok የሚባል የለም፣ ከካቶሊክ እምነት ውጭ ትባላለህና “መሀሪ” የምትባል ቤተክርስቲያን ከአባልነት ታሰወግድሃለች።

በዚህ በጨቀየ ካቶሊክ እምነት ውስጥ ከሞት የተረፈ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በላይነት ቀኖና ብቻ ነው። ከ ትችት በላይ ሆኖ፣ ቀጥታ በመንፈስ ቅዱስ ተመርጦአል በማለት፣ ሁልጊዜ ፍጹም እና ድንቅ እንደሆነ ይታሰባል፥ ይህ ግን የካቶሊክ እምነት ሳይሆን፣ ፈጠራ ነው።

በተቃራኒው፣ ቀኖናዎችን የሚጥስ ከሆነ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መመከር እንዳለበት ቅዱስ ቶማስ ያስተምራል፣ ለምሳሌ ሐዋርያ ጴጥሮስ በተሳሳተበት ጊዜ ጳውሎስ ገሰጸው። አክራሪ ካቶሊክ ደራሲ የነበረ Dante Alighieri በድርሰቱ ሁለት ጳጳሳት በሲኦል አስገብቶአል፥ አንዱ በትዕቢት ምክንያት ሌላው ደግሞ በፍርሃት ምክንያት ነበረ።

የሮማ ጳጳስ የሚመረጠው በካርዲናሎች ጉባኤ ነው። ነፃነት የእግዚአብሔር ስጦታ ነውና በማንኛውም ጊዜ እያንዳንዱ ሰው ክፉን መምረጥ መብቱ ነው። ይህ ደግሞ የሮማን ጳጳስ ለሚመርጡ ካርዲናሎችም ይሠራል።

የታሪክን መጽሐፍ ካነበበ፣ ማንኛውም ሰው ቤተክርስቲያን በመጥፎና ብቃት በጎደላቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምክንያት (ፀረ ሊቃነ ጳጳሳት ሳይጨመሩ) እንደተሰቃየች ያውቃል።

ካቶሊክ አማኝ አንድ ነገር ትክክል መሆኑን ወይም አለመሆኑን ሁል ጊዜ ለማመዛዘንና ለመወሰን መተው የለበትም። በወንጌል ውስጥ በጎቹን የማይጠብቁ መጥፎ እረኞች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገልፆአል። በወንጌል ውስጥ በጎቹ እረኛውን በድምፁ እንደሚያውቁት (ማለትም እሱ በሚናገረው ማለት ነው) ተገልፆአል። ወንጌልን የሚቃረን ነገር ከሆነ፣ በጎች እረኛቸውን መከተል እንደሌለባቸውም ያውቃሉ።

ክርስትና በጭፍን ታዛዥነት ላይ የተመሠረተ ሳይሆን፣ በነፃ ፍቃድ ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት ነው። ወንጌልን በመጣስ ለሚቃወም መሪ ጭፍን ታዛዥነት መስጠት አይገባም።

በጎች እረኛቸውን የሚለዩት በቃላቱ ነው እንጂ በሽታው አይደለም። ከበጎች ጋር ተደባልቆ የበጎች ሽታ ያለው ተኵላ ነው፣ ምክንያቱም እንደ በግ ለብሶ እንደ በግ መሽተት አለበት።

የካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የክርስቶስ ምክትል ነው። ክርስቶስ መንታ ወንድሞች አልነበሩትም። የሮማ ጳጳስ አንድ መሆን አለበት። ሁለት ሊሆኑ አይችሉም። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመሆን፣ እንከን የሌለውን ምርጫ ማካሄድ ያስፈልጋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መፍታትና ማሰር ስለሚችል፣ ምርጫው ፍጹም መሆን አለበት። ምርጫው ሕጋዊ እንዳይባል የምርጫ ሥርዓት አፈፃፀም ላይ ጥርጣሬ ካለ በቂ ነው። የሮማ ጳጳስ ለመሆን የመጀመሪያው መስፈርት የሮማ ወንበር ክፍት መሆን አለበት። የቀድሞው ጳጳስ ከዚህ አለም ማለፍ አለበት።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መልቀቅ ይችላልነ? አይችልም፣ የኩባንያ ሥራ አስኪያጅ አይደለም። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሙሉ ስልጣኑን መተው ይችላልን? ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የክርስቶስ አምሳያ ነውና ክርስቶስ ወደ ጎልጎታ ሳይደርስ መስቀሉን እንዳልተወ፣ የሮማ ጳጳስም ስለደከመው ስልጣኑን መተው አይችልም፣ ምክንያቱም የተሰጠውን ተልእኮ በመቀበል ቤተክርስቲያንን ፈጽሞ ላለመተው ፅኑ ቃል ገብቷል። ስልጣንን ለመተው ማሰብ የሚችለው፣ የፍርድና የውሳኔ ነፃነቱ ከተጎዳ ብቻ ነው (የአእምሮ ጉዳት፣ የአንጎል ካንሴር፣ እስር ቤት፣ ወዘተ)።

“በዕድሜና በድካም ምክንያት” መልቀቃቸው (ከስድስት ዓመት በኋላ የቤኔዲክት ፲፮ አእምሮ አሁንም በሚያስደንቅ ሁኔታ እየሠራ ነው)፣ እንደ ማንኛውም ሥራ አስኪያጅ መልቀቃቸው በቤተክርስቲያንና በጳጳስነት ቅድስና ላይ አሳዛኝ አደጋ ደርሶአል።

ሕጋዊ እንዲሆን የስልጣን መልቀቂያ ያለምንም ግዴታ መከናወን አለበትና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ለቆ እንደገና ተራ ጳጳስ መሆን አለበት። ነገር ግን በአገልግሎታቸው መክፈቻ ቅዳሴ ላይ በሰበኩት ሰብከት፣ ቤኔዲክት ፲፮ “ተኵላዎችን ፈርቼ እንዳልሸሽ ስለ እኔ ጸልዩ” ብለው ነበረ።

ባለፈው መጋቢት ወር የሞቱት የቤልጂየም ካርዲናል Godfried Danneels፣ ቀጣዩን ምርጫ በማዘጋጀት ቤኔዲክት ፲፮ እንዲለቁ ለማስገደድ በተካሄደው ሴራ፣ የአስራ አንድ ካርዲናሎች ቡድን አባል መሆናቸውን አምነዋል።[1] ከምርጫ ውጪ ለድርድር መገናኘትና መስማማት ስለማይፈቀድ፣ ቀጣዩ ምርጫ ሕጋዊ አልሆነም፤ በድርድር የተሳተፉትም በቀጥታ የተወገዙ ናቸው።

እኛ አንዳንድ ጥርጣሬ አለን። ምክንያቱም የመልቀቃቸው ምክንያት በተመለከተ ሲጠየቁ፣ ቤኔዲክት ፲፮ “መጓዝ በጣም ያደክመኛል” ብለው ነበረ። ግን የሮማ ጳጳስ ለመሆን መጓዝ አስፈላጊ አይደለም፣ በታሪክ ያሉት ምርጥ ጳጳሳት ከሮማ ተንቀሳቅሰው አያውቁም።

ሕጋዊ እንዲሆን ደግሞ መልቀቂያው ሙሉ መሆን አለበት፥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወደ ተራ ጳጳስ መመለስ አለበት። በተቃራኒው ቤኔዲክት ፲፮ አሁንም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው (emeritus) እና ለምን ጥቁር ወይም ቀይ ልብስ እንደማይለብሱ ሲጠየቁ “በመኝታ ክፍል ውስጥ ነጭ ልብስ ብቻ ነበረ” ብለው መለሱ። በተለይም ርዕሰ ጉዳዩ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከሆነች፣ ለእኛ ካቶሊካዊያን እንዲህ አይነት ቀልዶች እንግዳ ነገር ይመስላሉ። እንዲህ አይነት ጨዋታ አንረዳም።

በ2013 February 12 (የውጪ አቆጣጠር)፣ በየጣሊያን ጋዜጣ[2] በታተመው መግለጫ ውስጥ፣ ፈላስፋ Luciano Canfora  ቤኔዲክት ፲፮ በጻፉት መልቀቂያ ውስጥ ሁለት የላቲን ቋንቋ ስህተቶችን ዘግቧል።[3] በሰነዱ መጨረሻ ላይ ደግሞ፣ የታወጀ የስልጣን መልቀቂያ በ February 28 በ29(???) ስዓት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚሆን ተፃፈ።

ያለ ምንም ጥርጣሬ፣ እንደ ቤኔዲክት ፲፮ አይነት አስተዋይ ሰው ፊርማ ያለው ሰነድ በዘፈቀደ ወይም በጸሐፊ ተዘጋጅቶ እንደገና ሳይነበብና ሳይፈተሽ መጻፉ አይታሰብም።

አልፎ አልፎ ቤኔዲክት ፲፮ ምንም ችግር የላቸውም ብሎ የሚገልጽ ሰው አለ። እኛ ግን ከጥቁር መልእክት (black mail) በታች የሆነ ሰው እስከ ሞት ድረስ ከጥቁር መልእክት ሥር መሆኑን አስተውለናል። በመልቀቂያ ያሉ የሰዓትና የላቲን ቋንቋ ስህተቶችን ስናይ፣ c.f. የሚል ምህፃረ ቃል ትዝ ይለናል፥ በላቲን ቋንቋ c.f. (coactus fecit)  ማለት “ተገድጄ አድርጊያለሁ” ማለት ነው። በኮሙኒስት ግዛት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያኖች በዚህ ድብቅ ምህፃረ ቃል ይጠቀሙ ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የክርስቶስ አምሳያ ነው፥ የክርስቶስ በረከት ለመስጠት አንድ እድል እንኳን አያጣም። ሰላምታን የሚያቀርብ በመባረክ ነው፣ ምክንያቱም በምድር ላይ ከክርስቶስ እኩል ዋጋ ያለው በረከት ሊሰጥ የሚችል እርሱ ብቻ ነው። “መልካም ምሽት” የሚል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ በምድረ በዳ እርሱ ብቻ ውኃን ሊሰጥህ ሲችል፣ ጥማትህን ከማርካት ይልቅ ሰላምታ እንደሚሰጥህ ሰው ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የክርስቶስ አምሳያ ነው፣ ስልዚህ የራሱ ግላዊ ህይወት መርሳት አለበት። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስለ ራሱ አያወራም፥ ለምሳሌ በልጅነቱ የከብቶች አራጅ መሆን ያስብ እንደነበረ ወይም በአእምሮ ህክምና ስድስት ወር እንዳሳለፈ አይናገርም።

እያንዳንዱ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቃል እንደ ክርስቶስ ቃል ይቆጠራል፣ ስለዚህ እያንዳንዱ ቃል በከፍተኛ ጥንቃቄ የተጠና ሜሆን አለበት፣ ዝም ብሎ እንደፈጠራ መፃፍ የለበትም፤ አማኞችን ወደ ስህተት መምራት ስለሚችል እያንዳንዱ ቃል ፍጹምና ግልጽ መሆን አለበት። ያለ ዝግጅት መናገር ቀኖናዎችን ሆን ብሎ የመጣስ ዘዴ ይመስላል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እያንዳንዱ ድርጊት የክርስቶስ መገለጫ ስለሆነ፣ ፍጹም ድርጊት መሆን አለበት፥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ትዕግስትን አጥቶ ሴት አማኝ በጥፊ በመምታት ራሱን ማጋለጥ የለበትም።

ቤተክርስቲያን በታላቅ ጨለማ ውስጥ ያለች ይመስላል፣ ነገር ግን የሲኦል ኃይሎች እንደማያሸንፏት ቃል tገብቶልናል።

[1] የቡድኑ ስም “የሴንት ጋለን ማፊያ” ነው

[2] Corriere della Sera

[3] Pro Ecclesiae vitae in place of pro Ecclesiae vita (i.e. for the life of the Church) and, in the fundamental sentence, the accusative commissum instead of the dative commisso (connected to ministry (i.e. to the minister entrusted to me).

Leave a reply