[K2] Boeing 737 Max “በሰርከስ ክበብ ታቅዶ፣ ተራ በተራ በጦጣዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ የተዘጋጀ ነው” Boeing 737 Max “designed by clowns and supervised by monkeys”

[K2] Boeing 737 Max “በሰርከስ ክበብ ታቅዶ፣ ተራ በተራ በጦጣዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ የተዘጋጀ ነው” Boeing 737 Max “designed by clowns and supervised by monkeys”

Boeing 737 Max ላይ ስለደረሱ አደጋዎች ምርመራ፣ የኩባንያው አስተዳደር ቸልተኝነትንና ስግብግብነትን የሚገልጹ አስደንጋጭ ዝርዝሮች ብቅ እያሉ ነው። RT እንደዘገበው፣ የኩባንያው አንድ ባለሙያ አውሮፕላኑ “በሰርከስ ክበብ (circus clown) ታቅዶ፣ ተራ በተራ በጦጣዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ የተዘጋጀ ነው” በማለት ገልፆ ነበር። ሌላ ባለሙያም “ባለፈው ዓመት ስለደበቅኩት ነገር እስካሁን ድረስ በእግዚአብሔር ዘንድ ይቅርታን አላገኘሁም” ብሏል። ሌሎች ችግሮች ደግሞ ከ“በረራ አስመሳይ” (flight simulator) ብቃት ጋር የተገናኙ ናቸው፤ አንድ ሠራተኛ ሌላውን፥ “በ flight simulator ብቻ በሰለጠነውን የአውሮፕላን አብራሪ ታምናለህን? ሚስትህንና ልጆችህን ለርሱ ታሰረክባለህን?” በማለት ጽፎአል። መልሱ “አይ” የሚል ነው።

የሚያሳስበው ነገር ቢኖርም፣ እነዚህን ወሬዎች በጥልቀት ከመመርመር ይልቅ እየተወገዱ መሆናቸውን ነው። የአሜሪካ ፌዴራል በረራ ድርጅት (FAA America Federal Aviation Agency) እስካሁን ድረስ flight simulator ፍጹም በቂ እንደሆነ ከመግለጽ አያርፍም።

የ 737 Max ትንተና የበራሪዎችን ህይወት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉትን ብዙ ስህተቶች እየገለጸ ነው (የኢትዮጵያ  አየር መንገድ ብልሽት እንዲከሰት ምክንያት የሆነውን የ MCAS ሶፍትዌር ውቅር ችግር ሳይጨመር)። እነዚህ ስህተቶች ከሶስት ምክንያቶች የመነጩ ናቸው፥

– ለተፎካካሪ A320 (የአውሮፓ አውሮፕላን) ፈጣን ምላሽ መስጠት

– በአዲስ ፕሮጀክት ላይ ገንዘብ ሳይመደብ፣ የ60 ዓመት ዕድሜ የአውሮፕላን ሞዴል የማሻሻል ፍላጎት አለመኖሩ

– እንደ ህንድ በዝቅተኛ የሠራተኞች ደሞዝ ባሉበት አገሮች ውስጥ የአውሮፕላን ሥራ በመሥራት፣ የምህንድስና ወጪዎችን ለመቀነስ የሚደረግ ውድድር።

ውጤቱስ? የሰዎችን ሕይወትና የኩባንያውን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል የኪሳራ ፕሮጀክት ሆኖአል!

Leave a reply