![[LR1] በውጪ አቆጣጠር 2019 የሞት ዋና መንስኤ? ልጅ ማስወረድ The world’s leading cause of death in 2019? Abortion.](https://breadofkerith.com/wp-content/uploads/2020/01/82653971_552345872025748_9154706148425728000_n.jpg)
ምንም እንኳን ማወቅ በጣም ተገቢ ቢሆንም፣ በመደበኛ ሚዲያዎች ችላ የሚባሉ ዜናዎች አሉ። በምድር ላይ እጅግ ዘመናዊ የሆነ Worldometer የሚባል የሒሳብ ማሽን ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ 58.6 ሚሊዮን ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጦአል። ታድያ አዲስ ነገር የት አለ? በእውነቱ ሁለት ዜናዎች አሉ፣ የተደራረቡም ናቸው። የመጀመሪያው፥ በ2019 ከሞቱት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ የሞቱት በተፈጥሮ ምክንያት ሳይሆን በሰው ፍቃድ ምክንያት ነው። አለምን ያደናቀፉት ጦርነቶች ከታሰቡ፣ ግድ ነው ትሉ ይሆናል!!!
ግን አይደለም፣ ስህተት ነው!
እንዲያውም፣ አሳዛኝና የማይነበበው ሁለተኛው ዜና እንሆ፥ በዓለም ላይ በሰው ፍቃድ ከሞቱት ሰዎች፣ አብዛኞቹ የሞቱት በሰው በተነሳ ግጭትና ጦርነት ሳይሆን በፍቃደኝነት ፅንስን በማስወረድ ነው። ባለፈው ዓመት 42.4 ሚሊዮን የሰው ልጆች በውርጃ ምክንያት ተገድለዋል። ግልጽ ለማድረግ፣ 42 ሚሊዮን ሰለባዎች ማለት፣ በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ጊዜ አውሮፓ በጥፋት፣ ቦምብና በማጎሪያ ካምፖች በተናወጠች ጊዜ ከነበሩት ሲቪልና ወታደራዊ ሰለባዎች በላይ ነው። ይህን የገለፀው Worldometers የክርስትና ተቋም አይደሉም፣ ለማንም ተደራሽ የሆነ የኢንተርነት ጣቢያ ነው፤ ስለ አስተማማኝነቱ ከአሜሪካ ቤተ መጽሐፍት ማህበር ተሽልሞአል፣ ከBBC ጋር አብሮ ይሠራል።
ለብዙ ዓመታት ውርጃ ለህይወት መጥፋት ምክንያት አንደኛ መሆኑን ተረጋግጦአል። ደግሞም ሌሎች የሞት ምክንያቶች በደረጃ በጣም ሩቅ ናቸው፥ በ2019፣ 8.2 ሚሊዮን ሰዎች በካንሰር፣ 1.7 ሚሊዮን በኤች አይ ቪ፣ 13 ሚሊዮን በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት ሞተዋል። በህክምና እድገት፣ ሰውን በመርዳትና የሚያስፈልግ ገንዘብ በመመደብ፣ ካንሰርና ሌሎችን በሽታዎች ማሸነፍ እንደሚያስፈልግ ግልጽ ነው። ሆኖም፣ በጣም የሚገርም ነገር፣ ምንም እንኳን ከዚህ በላይ ቁጥሮች ቢጻፉም፣ ስለ ውርጃ ምንም እየተባለ አይደለም።
ከዚህ ዝምታ በስተጀርባ ቢያንስ ሁለት ዓይነት ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። የመጀመሪያው ምክንያት ከውርጃ ድርጊት ተፈጥሮ የተነሳ ነው፥ ምንም እንኳን ሁሉም የባህልና የሚዲያዎች ግፊት ሕጋዊ እንዲሆን ለማድረግ ጫና ቢያደርጉም፣ እስከ ዛሬ ድረስ በብዙ ሰዎች ዘንድ ውርጃ ሥነ ምግባር የጎደለው፣ ፍትሐዊ ያልሆነ፣ አሰቃቂ ድርጊት እንደሆነ ተደርጎ ይስተዋላል። በአንድ ቃል እንደ አፀያፊ ድርጊት ይታያል። በዚህ ምክንያት ርዕሱን ችላ ማለትን ተለምዶአል።
ውርጃ የማይጠቀስበት ሁለተኛው ምክንያት፣ ዛሬ አብዛኛውን ገዢ ባህል በዚህ ጉዳይ ላይ ካለው አቀራረብ የመነጨ ነው። በተለይም ዘዴው እንደሚከተለው ነው፥ የሰውን ትኩረት ወደ ፍልስፍና በመሳብ (ራስን መምራት፣ የመካከለኛውን ዘመን መጥፎ ባህል እንዳይመለስ ማድረግ፣ የወንድ ግዛት ማስወገድ፣ ወዘተ)፣ የማስወረድ “መብት” ማስፋፋትና ውርጃ ራሱ ምን እንደሆነ አለማስተማር።
ስለዚህ ገና ከጅማሬው ዓመት 2020 አመት፣ ከ 1,330,000 በላይ ሰለባዎችን ስላደረገ ክስተት ማንም ሰው እያወራ አይደለም (የ Worldometers data እዚህ መመልከት ይቻላል፥)። ይህ ችልተኝነት በዚህ 2020 አመት ውስጥ ገና ያልተወለደውን ልጅ ለመከላከል የግንዛቤ ውጊያ እንድንቀጥል አንድ ተጨማሪ ምክንያት ነው።
Leave a reply