የሰብከተገና 3ኛ እሁድ (A ADV-3)

የሰብከተገና 3ኛ እሁድ (A ADV-3)

ወንገል፥ ማቴዎስ 11፥2-11

ድምፅ ከቃሉ፣ ምኞት ከሚጠበቅ፣ ውሃ ከመንፈስ ቅዱስ፣ ጥያቄው ከመልሱ መለየት እንደማይቻል፣ የዮሐንስ ሕይወትም ከኢየሱስ ሕይወት መለየት አይቻልም።

ቁ3 “ይመጣል የተባለው መሲሕ አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ?”፥ …

“ዮሐንስ ይህንን የጠየቀው ባለማወቅ ሳይሆን፣ የማያውቁትን ለመምራትና እነሱን “እንሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያጠፋ የእግዚአብሔር በግ ይህ ነው” (ዮሐ 1፥29) ለማለት ነው” (JEROME)

ዮሐንስ ደቀመዛሙርቱን ወደ ኢየሱስ ለመላክ ያሰበው፣ የመሲሑ ሕያው ቃል ራሱ እንዲያሳምናቸው ነው።

ቁ4-6 “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት፤ ዕውሮች ያያሉ፣ አንካሶችም ቀጥ ብለው ይሄዳሉ፣ ለምጻሞችም ይነጻሉ፣ ደንቆሮችም ይሰማሉ፣ ሙታንም ይነሣሉ፣ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከሉት ሁሉ ብፁዓን ናቸው”፥ …

እንደ ዮሐንስ እኛም “ይመጣል የተባለው መሲሕ አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” በማለት እንጠይቃለን። መልሱ ደግሞ በተግባር ይታያል፥ “ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት”። የሚታየውና የማያምኑትም ሁሉ ሳይቀሩ መገንዘብ የሚችሉት ነገር የሚቀጥለወ ነው፥

በኢየሱስ እምነት ከሌለ…

– “ዕውሮች ዕውሮች ሆነው ይቀራሉ”፥ ስለ ሰው ታሪክ ክርስቲያናዊ ግንዛቤ የሌላቸው ሰዎች ዓለምን ለማዳን በመጨናነቅ ፖሊቲካዊ፣ ህጋዊ፣ ሥነምግባራዊ፣ ሕብረተሰባዊና የፋይናንስ መፍትሔዎችን ብቻ እየፈለጉ፣ ሳይሳካላቸው ሁኔታውን የበለጠ ያባብሳሉ፥ ዛሬ የዓለም ገዥዎች ዓለምን ማስተዳደር አልቻሉም።

– “አንካሳዎች አንካሳዎች ሆነው ይቀራሉ”፥ የታሪክ “እድገት” በየትኛው ቦታ እያነከሰ ይሄዳልና ሰው እንደ ሰው ሆኖ በክብር አይራመድም። በማህበረሰብ ውስጥ የከፉ ነገሮች ይከሰታሉ።

– “ለምጻሞች ለምጻሞች ሆነው ይቀራሉ”፥ ብዙዎች በአካላቸውና በነፍሳቸው አጥፊ በሆነ ምግባር  ተበላሽተዋል።

– መገንዘብና “ሁኔታውን መስማት” ስለማይችሉ፣ “ደንቆሮች ደንቆሮች ሆነው ይቀራሉ”፥ እስካሁን ተግባራዊ ያደረጉት የዓለም አካሄድና እቅድ እየፈረሰ ነው። የአለም አስከፊ ሁኔታ ሲጮህባቸው እነርሱ አይሰሙም።

– ክርስቲያናዊና ሰብዓዊ ባልሆነ ማህበረሰብ በአካል እንኳ ሳይቀር በሥጋም ስለተገደሉ፣ “ሙታን ሙታን ሆነው ይቀራሉ”፥ የሰውን ልጅ ሕይወት ሰብዓዊ ለማድረግ ከተፈለገ፣ ከክርስቶስና ከክርስትናም ውጪ ሌላ አማራጭ መንገድ የለም።

ቁ7 “ለመሆኑ ምን ልታዩ ወደ በረሓ ወጣችሁ? በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነውን?”፥ …

“በሸምበቆ ላይ አነስተኛ ነፋስ ሲነፍስ ሸምበቆ ያጎነብሳል። ሸምበቆ መንፈሳዊ ያልሆነ ነፍስ ያመለክታል። ምስጋና ወይም ስድብ ሲነፍስበት ወዲያውኑ ወደ ሁሉም አቅጣጫ ይቀየራል። ዮሐንስ በነፋስ የሚናወጥ ሸምበቆ አልነበረም። ከሰው አስመሳይነት ጋር አይስማማም፣ የሰው ስድብ ምንም አይመስለውም“ (GREGORY THE GREAT)

ዮሐንስ ሰንደቅ ዓላማ አይደለም። የእግዚአብሔር መንፈስ ካልሆነ ምንም ነፋስ አይነካውም። በእርግጥም እንደማንኛውም ነቢይ በጌታ ፊት “ይቆማል” (1ነገሥት 17፥1 ዮሐ 1፥35)። ከእግዚአብሔር ፊት ያልቆመ ማንኛውም ሰው በጣዖታትና በአለማዊ ጥቅም ሳይደሰት ይመራል።

ቁ8 “ደግሞስ ምን ለማየት ወጣችሁ? ጥሩ የሐር ልብስ የለበሰውን ለማየት ነውን? ጥሩ የሐር ልብስ የሚለብሱማ በነገሥታት ቤት ይገኛሉ”፥ …

“ይህ ሰው ለምን የድግስ ብዛት ይመኛል? አንበጣና የበረሐ ማር ይበላል። ለስላሳ ልብስ መልበስ ለምን ይፈልጋል? ልብሱ ከግመል ፀጉር የተሠራ ነው። ነገር ግን የሚያቆላምጡ፣ ገንዘብን የሚሹ፣ ሀብትን የሚፈልጉ፣ እንዲሁም በቅንጦት የሚኖሩና ለስላሳ ልብስን የሚለብሱ ሰዎች በነገሥታት ቤት ውስጥ ይኖራሉ” (JEROME)

ቁ9 “ታዲያ ስለምነ ወጣችሁ? ነብይ ለማየት ነውን?  አዎ! እንዲያውም ከነብይ የሚበልጠውን ለማየት እላችኋለሁ”፥ …

ዮሐንስ የነቢያት አባት የሆነው የኤልያስን ተመሳሳይ ልብስ ይለብስ ነበር (2ነገሥት 1፥8)። ቤተመንግሥቱ ምድረ በዳ ሲሆን፣ ለአለባበሱና ለምግቡ ተስማሚ ነበረ። ዮሐንስ የትንቢትና የፍፃሜ ደጃፍ ሲሆን፣  ከሁሉም ነቢያት በላይ ነው፥

ቁ11 “በምድር ላይ ከተወለዱት ሰዎች ሁሉ ከአጥማቂው ዮሐንስ የሚበልጥ ከቶ የለም። ነገር ግን በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉ ያነሰው ይበልጠዋል”፥ …

ዮሐንስ “ድምፅ” ነው፣ ክርስቶስ “ቃል” ነው። ከድምፅና ከቃል የቱ ይበልጣል? ቃል ይበልጣል፣ ምክንያቱም የድምፅ ትርጉምና ዋጋ ከቃሉ ይመጣል። ቃል ከሌለው ድምፅ እስትንፋሽ ብቻ ነው። ከሁሉም ያነሰ ቃል ከማንኛውም ድምፅ ይበልጣል።

“ድምፅ” ማለት በእግዚአብሔር ስም የሚናገር ነቢይ ማለት ነው፣ ዮሐንስ ነብይ ስለነበረ ከሴት ከተወለዱት ሁሉ የሚበልጥ ነው። ዮሐንስ ከአብርሃም፣ ከሙሴና ከኤልያስ በላይ ነው። ሌሎች ነብያት ከሩቅ የተመኙትን፣ በህልም ያዩትንና በአፋቸው ያወጁትን መሲህ፣ ዮሐንስ በዐይኑ አይቶአል፣ በጆሮው ሰምቶአል፣ በእጁ ዳስሶአል። ነገር ግን ዮሐንስ ከቅዱሳን መካከል አነስተኛ ነው፥ እርሱ በውሃ ያጠምቃል፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉ ያነሰው ቅዱስ ግን “አባ” በሚል በልጅነት መንፈስ ቀድሞ ተጠምቆአል (ሮም 8፥15) ። ሆኖም፣ ዮሐንስ እንዲሁ ቅዱስ ስለሆነ፣ እርሱም በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ነው።

1ኛ ንባብ፥ ኢሳይያስ 35፥1-6.10

ማህሌት ለሰብከተገና

ከሌሊት ክንፎች ብርሃን ለብሰሽ / ከምድረበዳ በወርቅ ተግጠሽ በእልልታ ትመለሺያለሽ፤
ከጥልቀት ህያው ሆነሽ / ከዘለአለም ዝምታ ተደምጠሽ ትመጪያለሽ፤
ከውድመት ጥንካሬን አገኝተሽ / ከማይታየው ምስል ሆነሽ ትመለሺያለሽ።
(Gertrud Von Le Fort)

Leave a reply