
1. አንዳንድ ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ሁለት የተለያዩ አማልክት አሉ ብለው በማወቅ ወይም ባለማወቅ ያምናሉ። ሁለተኛው አምላክ የመጀመሪያው አምላክ “ዝግመተ ለውጥ” ነው ብለው ያምናሉ። አንዱ ህጉን የሚያስገድድ ብርቱው ፈራጅ የሆነው የብሉይ ኪዳን አምላክ ሲሆን፣ አንዱ ደግሞ የአዲስ ኪዳን አምላክ ነው። ሁለቱም ከምህረትና ይቅር ባይነት አንፃር እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ናቸው።
እስከዚህ ያብራራሁት “ግኖሲስ” ተብሎ የሚጠራ በክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው መናፍቅ ነው (በእንግልዝኛ Gnosis ወይም Gnosticism)። የመጀመርያ ክርስቲያን ግኖሲስ ኢየሱስን እንደ “አዲስ ሰይጣን” አድርጎ ያስበው ነበር። ምንም እንኳ የማይረዳ ቢመስልም፣ በግኖሲስ ትምህርት መሰረት፣ በክፉ ፈጣሪ (የብሉይ ኪዳን አምላክ) ለተፈጠረ ለአዳም ዕውቀትና ነፃነት በማሳየት (“ግኖሲስ” በግሪክ ቋንቋ “እውቀት” መለት ነው)፣ ሰይጣን የብርሃን ምንጭ ነው ይለዋል። እንደ ግኖሲስ አስተሳሰብ፣ ዓለም በክፉ አምላክ የተፈጠረች የሰው ዘር የታሰረባት እስር ቤት ናት ብሎ ያምናል። ስለዚህ የፈጣሪ አምላክ ሕግ የሰው አእምሮ እስር ቤትና የነፃነት እንቅፋት መገለጫ ነው። ያለመታዘዝ ኃጢአት (የአዳም ኃጢአት) የሰው እውቀትና ክብር መጀመሪያ ነው (የአዳም ኃጢአት የጥበብ መጀመርያ ነው)። የአዳም ኃጢአት ሰው በእግዚአብሔር ላይ መለኮትነቱን የሚናገርበት ውቅት ነው።
2. በዘመናችን ከድሮ ግኖሲስ ጋር የሚመሳስለው አዲስ አይነት ግኖሲስ ተስፋፍቶአል፣ በ አዲሱ ግኖሲስ ፈጣሪና ፍጥረት መልካም ሆኖ ይታያል። ነገር ግን ኃጢአት ከእንግዲህ ወዲህ የነፃነት የእውቀትና የክብር መገለጫ ለመሆን ሲቀር፣ ሁሉን በሚያቅፍ ምህረት ውስጥ ተሽሯል። በቅርብ ጊዜ ደግሞ የእግዚአብሔርን አምልኮ የሚተካ ሌላ የምድር አምልኮ መስመር ተጨምሯል፣ በተለይም በተፈጥሮ አምልኮና በሥነ ምህዳራዊ ትምህርት አማካኝነት።
3. በዚህ ጠማማ አካሄድ ክርስቶስ የእያንዳንዱን ሕገ-ቀኖናና ቅዱስ ነገር ማጥፍያ ይሆናል። የማይገደብና ማንነት የሌለው የአምልኮ አጋጣሚ መስራች ሆኖአል፥ ክርስትናና ማንኛውም ሌላ አይነት አምልኮ እንደ አንድ ሆኖ ይታያል። ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ዘር ስርየት የማያስፈልገው ዘር ሆኖአል፣ ምክንያቱም ኃጢአትና ፍርድ (እና ከርሱ ጋር የቅዱስ ቁርባን መስዋዕት) ቀርቶአል።
እንዲህ አይነት አስተያየት የክርስቶስን ማንነት ለማበላሸት ቢሞክርም፣ ክርስቶስ ማንነቱን በጭራሽ አይሽርምና አይተውም። ሕግንና ነቢያትን በሙሉና በትክክል የሚፈጽም እርሱ ነው። በእርግጥም ህጉ ይበልጥ ከባድ ነው፥ ለምሳሌ ጋብቻን ፍጹም በማድረጉ የእግዚአብሔርን መሠረታዊ እቅድ ያመለክታል፣ ከፈሪሳዊያን ሕግ እንድንበልጥ ይጋብዘናል፣ (ይህ ማለት ሕጋችን የበለጠ ሥር ነቀል ሕግ መሆን አለበት ማለት ነው፥ “ፍትሃችሁ ከሕግ መምህራን የሚበልጥ ካልሆነ…”)። የልብም ምኞት ዝሙት ነው፤ የሞት ፍርድም ግድያ ነው… ወዘተ። መቼም ክርስቶስ ያለፍርድ ምህረትን አያመጣም፣ ስለ ሲኦል ግልጽ በሆኑ ቃላት ይናገራል።
ክርስቶስ በእኛ ዓለማዊ ንድፈ ወጥመድ ሊታሰር አይችልም።
4. ደግሞ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ሁል ጊዜም በጣም ግልፅ ነው። እርሱ መረጣቸው እንጂ እነርሱ አልመረጡትም በማለት ግልፅ ያደርጋል። ፍሬ ካላፈሩና የምድር ጨው ካልሆኑ ልክ እንደማይረባ ነገር ይረገጣሉ። ብዙ ሰዎች ተከትለውት ሲሄዱ ኢየሱስ ዞር ይላል (ሉቃስ 14፥25)፥ የመዞሩ ሁኔታ ግን “የሚያስፈራ” ነው። ከሕይወት በላይ፣ ሁሉንም መተው፣ መስቀሉን መሸከም፣ ከልጅ ወይም ከአባት በላይ ክርስቶስን መውደድ ያስፈልጋል በማለት ከባድ መስፈርት ያስቀምጣል። ለሁለት የተካፈለ ልብ አይፈቅድም።
5. ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በጥብቅ ይጠይቃቸዋል፣ ለሁላችንም እንዲህ በማለት ይጠይቃል፥ “እናንተም ደግሞ መሄድ ትፈልጋላችሁ?”።
አንድ ሰው ይሄዳል፣ ሌላ ሰው ይቆያል። አንዳንድ ሰው ደግሞ ሳይሄድ ክርስቶስን በማጣመም ክርስቶስ እንዲሄድ ያደርጋል፥ ከክርስቶስ ጋር ይቆይና ክርስቶስን ወደ ህሊናው መስታወት ይቀይረዋል። እንደ ፍላጎቱ ወደ አዲስ Che Guevara ይለውጠዋል፣ ወደ New Age ቅዱስ ይቀይረዋል፣ ወደ አዲስ ዘመናዊ ጋንዲ ይቀይረዋል፣ ወደ ኦሾ ይቀይረዋል።
6. ጠባብ በር ይኸውላችሁ። ጠባብ በር የጉዞውን መከራና ወደ ጎልጎታ የሚያወጣውን ከፍተኛ ጥረት ያመላክታል። ብቸኝነትንና የዓለምን መሳቂያ ያሳያል። ክርስቶስ በአባትና በልጅ፣ በእናትና በልጅ መካከል፣ በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ፣ በተከፋፈለና ከራሱ ጋር በሚጋጭ ልብ ውስጥ ያመጣውን ሰይፍ ያሳያል።
የክርስቶስ መለያ ይኸውላችሁ፥ በሩ ጠባብ ነው፣ ምክንያቱም መጠባበቁ ቋሚ መሆን አለበት፣ ምክንያቱም በማይጠበቅበት ጊዜ ፍርድ ይመጣል። ምክንያቱም የተመረጡት ጥቂቶች ናቸው። ምክንያቱም የተሰጠ ገንዘብ ማብዛት ያስፈልጋል። ምክንያቱም የክርስቶስ ሕግ ይፈጸም ዘንድ ይገባል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፍቅር ወሰን የለሽ መሆን አለበት። የትግልና የውጊያ ጉዳይ ነው፥ ጠባብ በሩ በትጋትና በከፍተኛ ጥረትና ቁርጠኝነት የሚደረገውን ፍለጋ ያመለክታል።
ክርስቶስ አንድ ብቻ ነው። እሱም በሰው የተፈጠረ የግኖሲስ ክርስቶስ አይደለም። የጠባቡ በር ክሪስቶስ ነው።
Leave a reply