የሦስተኛ አመት 29ኛ እሁድ (C OT-29)

የሦስተኛ አመት 29ኛ እሁድ (C OT-29)

ወንገል፥ ሉቃስ 18፥1-8 see here

ቁ3 “በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች”፥

ሙሽራው ተወስዶባት መቼ እንደሚመለስ የማታውቅ መበለት የሉቃስ ቤተክርስቲያን ናት ”(5፥35፤ ሐዋ 1፥9-11)። መመለሻውን በመመኘት ብቻዋንና በሐዘን የምትኖር ናት። ለዚህም “ማራናታ” (1ቆሮ 16፥22፤ ራዕ 22፥20) ብላ ትለምናለች።

መበለቲቱ ምንም ስጦታ የላትም። እንደ ሰው ምኞት ድሀ ናት። ፍላጎቷን ማሟላት የምትችለው አጥብቆ በመጠየቅ ብቻ ነው።

1ኛ ንባብ ዘጸአት 17፥8-13 see here

ቁ8 “አማሌቅም መጥቶ ከእስራኤል ጋር በራፊድም ተዋጋ”፥

አማሌክ ወደ ቅድስት ምድር የሚመራውን መንገድ ይክዳል። ሙሴ እጆቹን በክርስቶስ መስቀል መልክ  በመዘርጋት ይከፍተዋል። (AUGUSTINE)

ቁ12 “የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ጠነከሩ”፥

ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ግን በገዛ ኃይሉ በመስቀል ላይ እጆቹን ወደ ላይ ዘረጋ። ምስል እንዴት እንደተሰጠና እውነት እንዴት እንደሆነ አይተሃል? (CHRYSOSTOM)

እጆቹ በአሮንና በሖር ተይዘው በነበረበት ጊዜ፣ ነብዩ ሙሴ የመስቀል መልክ ጠብቀው እስከ ምሽቱ ድረስ ቆየ። እንዲሁ ከመቀበሩ በፊት ጌታችንም እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ እስከ ምሽቱ ድረስ ቆየ። ከዚያም በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ። (JUSTIN MARTYR)

አጭር ትምህርት

1 ጸሎት፥ “ሙሴ እጁን ባነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር፤ እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ድል ያደርግ ነበር”፥ የእስራኤል ሕዝብ በማይፀልይበት ጊዜ ይሸነፍና በሚፀልይበት ጊዜ ያሸንፋል። ነገር ግን ዛሬ እንደሚደረገው ደግሞ የሰዎችን ሁሉ ምኞት ወደሚያረካ አምላክ ሳይሆን፣ ወደ እውነተኛው አምላክ ዞር ማለት ያስፈልጋል። በራስህ አምሳል የፈጠርህ አምላክ አንተ ራስህ በመስታወት ውስጥ ነህ፥ ለማንም አይጠቅምም። በሰው ታሪክ ወደተገለጸውና ጦርነቱን ማሸነፍ መቻሉን ወዳረጋገጠው ወደ እውነተኛው አምላክ መጸለይ ያስፈልጋል። እሱ የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው።

2 እምነት፥ “ነገር ግን የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ በምድር ላይ እምነትን ያገኝ ይሆንን?”። የዛሬ ዓለምን በመመልከት፣ ሶስት መልሶች ሊኖሩ ይችላሉ።

  • አፍራሽ አይነት ሰው (pessimistic) “የለም ቶሎ ካልተመለሰ አያገኝም” ብሎ ይናገራል፤
  • ነገሮችን በሌለው ብርሃን የሚያይ ሞኝ ሰው (optimistic) “በሮች ለሁሉም ክፍት እስከሆኑ ድረስ፣ ከሁሉም ጋር በሰላም የምንኖር ከሆነ፣ ከሁሉም ጋር ከተሰማማን (ውይይት መገናኘት ንግግርና ሌሎች ተመሳሳይ ቃላት)፣ የክርስቶስ ከመሆን የሚገኘውን ማንነታችን እስከምንተው ድረስ፣ አዎ ያገኛል” ብሎ ይናገራል።
  • እኛ ግን ከዚህ በፊት አስበንበት የማናውቅ ሶስተኛው መልስ ዛሬ አለ። እሱም ነገሮችን እንደ እውነቱ ለማየት የሚችል ሰው መልስ ነው (realistic)፥ “አዎ፣ በታመመች ቤተክርስቲያን ውስጥ የታመመ እምነትን ያገኛል! እናም የእውነተኛውን ቤተክርስቲያን እውነተኛ እምነት የሚያገኘው በቀረው ጥቂት እስራኤል ውስጥ ብቻ ነው። “ባዓል ለተባለው ጣዖት ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለራሴ አስቀርቼአለሁ። እንደዚሁም በአሁን ዘመን ደግሞ በጸጋ ተመርጠው የቀሩ ጥቂት እስራኤላውያን አሉ” (ሮሜ 11፥4-5)። የሆነ ችግር አለ፥ የቤተክርስቲያን የነበረ የሁለት ሺህ ዓመት ትምህርት ተቀይሮአልና ይሁዳ ክህደት ለሁለተኛ ጊዜ ተፈፅሞአል፥ በአዲስ ኪዳን የተተነበየ ታላቅ ክህደት ነው (2ኛ ተሰሎ 2፥3)። በክርስቶስ የተቋቋመ እውነተኛ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሞታ ዳግም መወለድ ይኖርባታል።

Leave a reply