የሦስተኛ አመት 28ኛ እሁድ (C OT 28)

የሦስተኛ አመት 28ኛ እሁድ (C OT 28)

ወንገል ሊቃስ 171119 see here

ቁ14 “እነርሱም በመሄድ ላይ ሳሉ ከለምጻቸው ነጹ”፥

እኛ ቅዱስ ጉዞውን ለሚመራን ለቃሉ በመታዘዝ እንነጻለን።

ቁ15 “ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ ተመለሰ”፥

ይህ “አንድ ብቻ” የእውነተኛው እስራኤል የቤተክርስቲያን ምስል ነው።

ቁ17-18 “አሥሩ አልነጹምን? ዘጠኙስ ወዴት አሉ? ከዚህ ከልዩ ወገን በቀር እግዚአብሔርን ሊያከብሩ የተመለሱ አልተገኙም?”፥

አንድ እና ዘጠኝ እናነፃፅር። ብዛትን በተመለከተ ዘጠኝ ከአንድ ይበልጣል፥ ዘጠኝ ለማግኘት ዘጠኝ ጊዜ አንድ ያስፈልጋል። ነገር ግን ጥራትን በተመለከተ አንድ ቁጥር ከዘጠኝ ቁጥር ይበልጣል፥ አንድ ቁጥር የሙላት ስሜት ይሰጣል። ዘጠኝ ቁጥር ግን፣ አሥር ለመሞላት አንድ ስለሚጎድለው፣ የእጥረት አምሳያ ነው። አንድ ሲባል ከሌላ ሁሉ የተለየ ነው።

እግዚአብሔር ከነፍስ ወደ ነፍስ ለያንዳንዱ ልብ ይናገራል። የክርስቶስ ፀጋ በእያንዳንዱ ሰው ነፍስ ውስጥ ይከሰታል እንጂ ለዘጠኝ ወይም ለአሥር ወይም ለጋራ አይከሰትም። ይህ ማለት በክርስትና ሕይወት ውስጥ ዋጋ ያለው ብዛት ሳይሆን ጥራት ነው።

ደግሞ ወደ ክርስቶስ የተመለሰ “ልዩ ወገን” ነው፥ ነገሮችን እንግዳ ወይም ልዩ በሆነ አመለካከት ማየት ያስፈልጋል፥ የእግዚአብሔር አስተያየትና የአለም አስተያየት ተመሳሳይ ሊሆኑ አይችሉም (የክርስቶስ አስተያየት ልዩ ወገን ነው)። በክርስቶስ አስተያየት ከዘጠኝ አንድ ያሸንፋል።

1ኛ ንባብ 2ኛ ነገሥት 51417 see here

አጭር ትምህርት

መዳን ከለምጽ መንጻት ማለት አይደለም፣ መዳን ከፈወሰን ከክርስቶስ ጋር መኖር ማለት ነው። የተጠማ ሰው በአንድ ብርጭቆ ውሃ ሊረካ አይችልም፤ ሊያድነን የሚችል ከክርስቶስ ጋር ያለን ግንኙነት ብቻ ነው፥ ስጦታዎቹ ሁሉ ከእርሱ ጋር እንድንዋሐድ መንገድ ናቸው።

1. በተአምራዊ መንገድ የታደመው ለምጽ በተንኮል ተመልሶ የባሰ ጉዳት እንዳያመጣ ማድረግ የሚችል ማነው? በሌላ አገላለጽ፥ ዳግሞ የተገኘ ጤና እንዴት ቋሚ የሥነ ምግባር፣ የሥራና የባህል መርህ ሊሆን ይችላል? ለምጽ ተመልሶ እንዳይዘን አስፈላጊ የበሽታ መከላከያዎችን የት ማገኘት እንችላለን? የበሽታ መከላከያዎችን ማገኘት የምንችለው፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈውስ ተዓምር በተከናወነበት ቦታና መሬት ውስጥ ዘልቆ በመቆየት ብቻ ነው።

በእግዚአብሔር መሬትና አፈር ዘልቆ መቆየት ያስፈልጋል። 2ኛ ነገሥት 5፥17 ይህንን ይገለጻል፥ “ንዕማንም፥ እኔ ባሪያህ ከእንግዲህ ወዲህ ከእግዚአብሔር በቀር ለሌሎች አማልክት የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት አላቀርብምና ሁለት የበቅሎ ጭነት አፈር እንድወስድ እሺ ትለኝ ዘንድ እለምንሃለሁ”። ከለምጽ ከነጻ በኋላ፣ ሁልጊዜ አፈሩ ከርሱ ጋር እንዲኖር፣ በሌሎች አማልእክት መካከል ለእስራኤል አምላክ ቤተመቅደስ ይሠራ ዘንድ፣ ንዕማን የተፈወሰበት ተአምራዊ ስፍራ አፈር በሁለቱ በቅሎዎቹ ላይ ለመጫን ይፈልጋል፥ ያ አፈር ተጠብቆ የሚቆይበትና አሁንም ሊነካና ሊረገጥ የሚችልበት ቦታ ሰው ለእውነተኛ እግዚአብሔር ራሱን የሚሰዋበት ቦታ ነው።

የሉቃስ ወንጌል በክርስቶስ መሬትና አፈር ዘልቆ መቆየት እንዴት እንደሚቻል ለመግለፅ ይበልጥ ጥልቀት ያለው አመለካከት ይጠቀማል። “ከእነርሱም አንዱ ከለምጹ መንጻቱን ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ተመለሰ፤ እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ” (ሉቃስ 17፥14-15)። የሉቃስ ወንጌል የልብ ቦታና አቀማመጥ ያሳየናል። የልብ አቀማመጥ ደግሞ ምስጋና ነው፥ “እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ”።

2. “ከዚህ ከልዩ ወገን በቀር እግዚአብሔርን ሊያከብሩ የተመለሱ አልተገኙም” (ሉቃስ 17፥18)። በዛሬው ዘመን ይህ “ልዩ ወገን” እኛ እራሳችንን ሆንን። በቤተክርስቲያን ውስጥ አሁንም ክርስቶስን ሳይረሱ ተመልሰው የሚሰግዱለት ልዩ ወገን ሆኑ፣ ምክንያቱም የአለም ወገኖች እንዳይሆኑ፣ አለም እንዳያመሰግናቸው፣ ራሳቸውን ለዓለም ያልሸጡ ጥቂቶች ናቸው። ብዙውቹ የአለም ወገኖች በመሆን እምነት እንደሌላቸው እንደ ዓለም አድርገው እንደሚያስቡ ሆነዋል። ዛሬ ለእውነተኛ የክርስቶስ ትምህርት ታማኝ ሆኖ መቆየት የሚፈልግ በገዛ ቤቱ፣ በማህበረሰቡና በቤተክርስቲያን ውስጥም እንኳ “ልዩ ወገን” ሊሆን ነው።

3. ምንም በአጋጣሚ 2ኛ ጢሞ 2፥8 “ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ” ብሎ ይፅፋል። ቤተክርስቲያንን በማስተዳደር ዛሬ ክርስቶስን አለማስታወስ እንዴት ቀላል ሆኖአል! ብዙ ሥራ አለ፣ አስፈላጊ ማህበራዊ ስራዎች፣ ከባለስልጣናት ጋር የፖለቲካ ግንኙነት… ሁሉም አስፈላጊ ናቸው፣ ግን “ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ”፥ እሱ ለሁሉም ነገር መሠረትና ምክንያት ነው። ትምህርቶቹን አትቀይሩ፣ ትንሳኤውንም አታበላሹ እንደማለት ነው። ደኅንነት የሚገኘው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል በመሆን ብቻ ነው እንጂ ንብረታችን እንደሆነ አድርገን በዘመናዊ አስተሳሰብና በልማዳችን መሰረት የተቀረፀ ቤተክርስቲያን አባል በመሆን አይመጣም። ምክንያቱም በክርስቶስ ወደማያምነው ሐሰተኛ “ቤተክርስቲያን” ማንም አይመጣም። በትክክል፥ ከዓለም ጋር ተመሳሳይ ወደሆነ “ቤተክርስቲያን” ለመግባት ምን ይጠቅማል? እንዲሁ በአለም ውስጥ መቆየት እንችላለን። “የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም” ( 2ኛ ጢሞ 2፥9)፥ የእግዚአብሔር ቃል በዘመናዊ አስተሳሰብና በልማዳችን መልክ ሊለወጥ አይችልም።

Leave a reply