የአማዞን የጳጳሳት ጉባኤ (ሲኖዶስ)

የአማዞን የጳጳሳት ጉባኤ (ሲኖዶስ)

ባለፈወ ጥቅምት 4 በቫቲካን ጋርደን በአማዞን ሲኖዶስ መክፈቻ ስነ-ሥርዓት ላይ የሆነውን ነገር አስተውላችኋል? ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አረማዊ ንጥረ ነገሮችን ያካተተ ሥነ ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል። የተለያዩ የአማዞን ሕዝብ መሪዎች ለእናት ምድር ጸሎት አቀረቡ። አንድ ዛፍ ተተክሎአል። አንድ ሰው በጉልበቱ ተንበርክኮ የቆሻሻ አቧራ ስሞአል። ከዝግጅቱ በኋላ ተሳታፊዎች ነፍሰጡር ሴቶች እና እናት ምድር የሚመስሉትን ሐውልቶች በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው ሲሰግዱ ታይተዋል።

የእግዚአብሔር ቃልና የቤተክርስቲያን ትምህርትና ምስጥራት እስካሉ ድረስ፣ ወንጌልን መስበክ ይቻላል። ነገር ግን ወንጌላዊ ተልእኮ በአረማውያን ሥነ-አምልኮ ውስጥ መሳተፍን ያካትታል ብሎ የሚያስተምር መመሪያ አላውቅም።

ከአረማውያን ጋር መነጋገር አለብን ከሚሉ ሰዎች ጋር መሄድ አያስፈልግም። ሚሽነሪዎች በአማዞን አካባቢ ገብተው እግዚአብሔር ዓለምን ስለወደደ አንድ ልጁን አሳልፎ እንደሰጠ ከልብና በፍቅር እንዲናገሩ ይገባል። የቤተክርስቲያን ተውፊት ክርስቶስን እንድንሰብክ ያስተምረናል። ይሁን እንጂ ከአረማውያን ጋር እንድንወያይ፣ በአረማውያን አምልኮ ውስጥ እንድንሳተፍም አያስተምረንም።

እኛ ማን ነን? የምድር አምላኪዎች? የተባበሩት መንግስታት ተወካዮች? የአየር ንብረት ሰባኪዎች?

“እኛ ወይም የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለ ልማድ የለንም”። (1ቆር 11፥16) “ከአጋንንትም ጋር ማኅበረተኞች እንድትሆኑ አልወድም።  የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም፤ ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም”። (1ቆር 10፥20-21)

ይልቁንም በክርስቶስ ላይ ያለን እምነት ነፃ አውጥቶናል። “ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ”። (1ተሰ 1፥9-10)

እራሳችንን፣ አገራችንንና መላው ቤተክርስቲያንን ለድንግል ማርያም አደራ እንስጥ። በሰው ታሪክ ላይ የልቧ ድል ቶሎ እንዲገለጽ እንጠይቃት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው ልጆች ታሪክ እና በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ጣልቃ ስራውን ይግለጽ።

Leave a reply