ቤታችን በእሳት ላይ አይደለም

ቤታችን በእሳት ላይ አይደለም
  1. በCO2 እና በአየር ብክለት መካከል ውስጥ ያለው ግንኙነት ምንድነው?

CO2 ከአየር ብክለት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ደግሞ በአየር ንብረት ውስጥ የCO2 ብዛትና የሙቀት መጠን ግንኙነት እንዳላቸው የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማረጋገቻ የለም። እንዲያውም ባለፉት 5000 ዓመታት ውስጥ በአየር ንብረት ውስጥ አነስተኛ የCO2 መጠን ሲኖር ትልቅ የሙቀት ለውጥ ተመዝግበዋል።

  1. እውነት ለመናገር በምድር ላይ ያለው ሙቀት እየጨመረ መምጣቱ እውነት ነውን? የሰው ስራ በነዚህ ለውጦችላይ ምን ያህል ተጽዕኖ ያሳድራል?

በ1400 ዓ.ም. አካባቢ ሳይንቲስቶች “የበረዶ አነስተኛ ዘመን” ብለው የጠሩት የብርድ ዘመን ነበር። ከ1400 እስከ 1700 ዓ.ም. ድረስ የሙቀት መጠን እየወረደ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን በ1700 ተመዝግቦአል። ከ1700 ዓ.ም. ጀምሮ በምድር ላይ ያለው የሙቀት መጠን ደጋሚ ወደ ላይ ከፍ ማለት ጀምሮአል። ይህ የሚያመለክተው የተፈጥሮ የአየር ንብረት ስርዓት በአሁኑ ጊዜ “በሙቀት” ደረጃ ላይ መሆኑን ነው። ሆኖም፣ አሁንም ቢሆን ዘሬ የሚመዘገበው የሙቀት መጠን በመካከለኛው ዘመን (1200 ዓ.ም. አካባቢ) ከነበረው የሙቀት ደረጃ አይበልጥም። ከ2000 እስከ ዛሬ ባለው ጊዜ በምድር ላይ ያለው የሙቀት መጠን ቋሚ ሆኖአል (በእርግጥ በ 0.1 ዲግሪ ቀንሶአል)። ደግሞ የምድራችን ታሪክ፣ በተለይም ባለፉት 4000 ዓመታት፣ የሰው ልጅ ሰዎች በጣም ከባድ አደጋ የደረሰበት በቀዝቃዛ ወቅት እንደነበረ ይነግረናል። በተቃራኒው ሀብትንና ሕዝባዊ እድገትን ያመጡት የሞቃት ዘመናት ናቸው (ለምሳሌ ታላቁ የሮማ ግዛት መስፋፋት)።

  1. ያለማቋረጥ በስፋት የሚጻፍ ሌላ ዕንቁ የበረዶ ሀይቆች መቅለጥን ይመለከታል። ከዚህ በታች ያለው ግራፍ (National Snow and Ice Data Center – NSIDC) የአንዳንድ መግለጫዎችን ዋጋ ለመገምገም ያስችለናል።

ከ1979 እስከ 2016 የሁለቱ ንፍቀ አለም የበረዶ ሀይቆች ሽፋን ተቃራኒ አዝማሚያ ያሳያል። የሰሜናዊው ንፍቀ አለም በረዶ እየቀነሰ ሲሄድ፣ የደቡብ ንፍቀ አለም በረዶ እየጨመረ መጥቶአል። ስለዚህ በባህር ውስጥ እና በደሴቶች ላይ ጥፋት ሊኖር አይችልም።

  1. 95% የሳይንቲስቶች ቁጥር እንዴት ሊሳሳት ይችላል?

በጀርመን አገር ከ70% በላይ የሚያህሉ የሳይንስ ተመራማሪዎች በአየር ንብረት ንድፈ ሀሳብ ውስጥ በቂ ማስረጃ አያዩበትም። በቅርቡ ሳይንትስቶች፣ የጠፈር ተመራማሪዎችና የNASA አባላት፣ በፖለቲካ ውስጥ ሳይንስ እንዲጨምርና በሳይንስ ውስጥ ደግሞ ፖለቲካ እንዲቀንስ አቤቱታ አቅርበዋል።

  1. CO2 በአየር ንብረት ላይ ጠቃሚ ተፅእኖ አለውን?

CO2 ከፎቶሲንተሲስ (photosyntesis) ጀምሮ የሕይወት ምንጭ ነው። ስለዚህ እኛ ልንዋጋው የሚገባን የአለም ብክለት ነው እንጂ የCO2 መኖር አይደለም (መርዛማ ልቀቶች፣ ፕላስቲክ፣ ቆሻሻ፣ ወዘተ)። CO2 አረንጓዴ ጋዝ ነው፣ በምድር ላይ ያሉት 7.5 ቢሊዮን ሰዎች ምግብ የሚያገኙበት የሕይወት ጋዝ ነው። ይህን ጋዝ እንደ ዲያብሎስ ማድረግ፣ አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የፈጠሩት ሀይማኖት ነው።

  1. Greta Thunberg?

አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት አጠቃላይ የ ኢነርጂ ሃይል ለመቆጣጠር ይፈልጋሉ። Greta Thunberg የዚህ አጠቃላይ ስትራቴጂ አካል ናት። ደግሞ ይህች ልጅ ምንም የማታውቅ ልጅ አላግባብ እይተጠቀሙባት ነው።

Leave a reply