የክርስቶስ ተቃዋሚ ትምህርት

የክርስቶስ ተቃዋሚ ትምህርት

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አዲስ ፈጠራ ሳይታይ አልፎአል። ርዕሱ “ዓለም አቀፉን የትምህርት ስምምነት እንደገና መገንባት” የሚል፣ “ከሁሉም አለምና ከሁሉም ሃይማኖት በትምህርት መስክ ውስጥ የሚሳተፉትን የህዝብ ቁጥሮች” ይጋብዛል።

በጣም የሚያስደንቀው ነገር ቢኖር፣ በዚህ ትምህርታዊ ስምምነት አጠቃላይ የክርስቲያን መለያ ምልክት አለመኖር ነው። ፍራንሲስ ስምምነቱን በሚያቀርቡበት የቪዲዮ መልእክት ውስጥ፣ የእግዚአብሔርም ሆነ የኢየሱስና የቤተክርስቲያን ዱካ የለውም። ዋነኛው የስምምነቱ ቅመር “አዲስ ሰብአዊነት” “የጋራ ቤት” “ሁለንተናዊ አንድነት” “ብልጽግና” “ትብብር” እና “ተቀባይነት” የሚሉ ናቸው።

እና ሀይማኖቶችስ? እነሱም ባልተለየ “ምልልስ” ውስጥ ተቀላቅለው የቀሩ ናቸው። “የመድልዎ ቦታን ለማፅዳት”፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት “የሰው ወንድማማችነት” የሚለውን በየካቲት 4 2019 (EC) ከአል-አዝሀር ታላቁ ኢማም ጋር የተፈራረሙትን ሰነድ ያስታውሳሉ። ሰነዱ “የሃይማኖት ብዛትና ልዩነት” በ“መለኮታዊ የእግዚአብሔር ጥበብና ፈቃድ” ይመሰረታል በማለት ይገልጻል።

በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አንድ የሮማ ሊቀጳጳስ እንዲሀ ሆኖ አለማዊ የትምህርት ስምምነት የራሳቸውን አድርገው ሲደግፉ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። ምክንያቱም በእውነቱ የክርስቶስ ስም የሌለው “አዲስ ሰብአዊነት” በምዕራባዊ ታሪክ አዲስ አስተሳሰብ አይደለም። ሆኖም ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ አዲስ ነገር ነው።

በምእራብ ታሪካዊ አስተሳሰብ ውስጥ ክርስቶስ በሰው ፍቅር ተተክቶ ይሚጠፋበት ብዙ ዓይነት ፍልስፍናዎች አሉ (የዚህን አስተሳሰብ መግለጫ በFedor Dostoevskij፣ Lev Tolstoj፣ Vladimir Solovev እና ሌሎች ጽሑፎች ውስጥ እናገኛለን)።

በዚሁ አዲስ ሰብአዊነት ግብዣ በእንግዶቹ መካከል እንደ አንድ እንግዳ ሆኖ የሚቀመጥ ከሆነ እግዚአብሔርም በዚህ ስምምነት መሳተፍ ይችላል።

ይህ የክርስቲያን አስተሳሰብ ውድቀት ነው።

Leave a reply