ባለፈው ሰኔ ወር ውስጥ ለአንድ ትልቅ የምዕራብ አገር ፓርላማ የአየር ንብረት ለውጥ (global warming) ምክንያት ሰው መሆኑ የመንደር አፈታሪክ ነው ብሎ የሚከራከር አቤቱታ ተልኳል። አቤቱታው ከፍተኛ እውቀት ባላቸው በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 200 የሳይንስ ሊቃውንት ተፈርሞአል።

ሰነዱ የሚከተለውን ይገልጻል፥

  1. ከ1950 እስከ 2000 ባነበሩት ዓመታት የታየው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ አስደንጋጭ ጉዳይ አይደለም፥ ቀደም ብለው በነበሩት ጊዜያት ይበልጥ ሞቀታማ ወቅቶች ተከስተዋል። ደግሞም ከ2000 ጀምሮ እስከ ዛሬ በምድር ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ቆሞአል።
  2. የአየር CO2 ማደግ የጀመረው ከፍተኛ ሰው ሰራሽ ልቀቶች ከመኖራቸው በፊት ነው (ማለትም ከ 1700ዎቹ ዓመታት በኋላ ከተጠቀሰው የአየር ልውጥ ጋር ተያይዞ ነው)።
  3. በተቃራኒው በኢንዱስትሪ ዘመን በአየር ንብረት ውስጥ የተከሰተው የCO2 ጭማሪ በአለም አቀፍ አማካይ የሙቀት መጠን ላይ ፋይዳ የለውም (የCO2 ክምችትና የሙቀት መጠን ተመጣጥነው አያድጉም)።
  4. የCO2 መጨመር በዓለም አቀፍ ዕፅዋት እንዲያድግና የግብርና ምርት እንዲጨምር አድርጎአል።
  5. ግግር በረዶዎቹ መቋረጣቸውና የባህሩ መጠን በ3 ሚሜ/በዓመት መጨመሩ እውነት ነው ግን ሁለቱም ክስተቶች የጀመሩት ከ1700 በኋላ ነው።

በዚህ ማስረጃ ላይ ተደግፈው፣ 200 የሳይንስ ሊቃውንት ሰው ሠራሽ የCO2 ልቀቶች ከአለም አየር ንብረት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸውና የአየር ንብረት የሚመራ ከቁጥጥራችን በላይ በሆኑት በተፈጥሮ ክስተቶች እንደሆነ መደምደም ይችላሉ።

በተለይም “ድህነትን ለመከላከል የሚደረግ ትግልና የአየር ንብረት ለውጥ በማሳሰር ድህነትን ለማስወገድ የሚደረገውን ትግል በከባድ ሁኔታ ያጎድፋል“። (Richard Lindzen, emeritus professor of Atmospheric Physics at MIT and member of the American National Academy of Sciences)

Leave a reply