ጌታችን ሆይ፣ ስለ እኛ ሳይሆን፣ ስለስምህ ክብር ይሁን። (መዝሙረ ዳዊት)

ጌታችን ሆይ፣ ስለ እኛ ሳይሆን፣ ስለስምህ ክብር ይሁን። (መዝሙረ ዳዊት)

ጌታችን ሆይ፣ ስለ እኛ ሳይሆን፣ ስለስምህ ክብር ይሁን። (መዝሙረ ዳዊት)

ስለሚያቃጥለን ፀሐይ፣ ስለሚያርሰን ዝናብ፣ እንከን የለሽ ስለሆነው የጀግኖች ትግል፣ እናመሰግንሀለን።

ስለሚያሠቃየን ረሀብ፣ ስለሚያደርቀን ጥማት፣ እጅና እግር ሲዳከም፣ እናመሰግንሀለን።

ስለሚያሳውረን ነፋስ፣ ስለሚያነደን አሸዋ፣ በጭቃ ውስጥ ስለፈሰሰ ደማችን፣ እናመሰግንሀለን።

በውጊያ እያለን እንቅልፍ ባጣን ሌሊት፣ ልብን በእውነተኛ ደስታ ስለሚሞላ ጽሞናና ጸሎት፣ እናመሰግንሀለን።

ስለጠላታችን እንባ፣ በጦር ሜዳ ስንጋለብ፣ ድግሳችን በሆነው በውጊያ እልልታ፣ እናመሰግንሀለን።

በሰዎች ልብና በግምቦች ጫፍ ጎልቶ ስለሚታይ እምነት፣ ስለሚጠብቀን አዳኝ ሞታችን፣ እናመሰግንሀለን።

ከፊትህ ለመምጣት ስላለን አስደሳች ተስፋ፣ ደረታችን ቆስሎ ስንጸዳ፣ እናመሰግንሀለን።

በልባችን ውስጥ ስለሚያነቃቃን የጦር መሳሪያ ፍቅር፣ ስለታላቁ ክብርህ ክቡር ጌታችን ሆይ፣ እናመሰግንሀለን።

ጌታችን ሆይ፣ ስለ እኛ ሳይሆን፣ ስለስምህ ክብር ይሁን። (መዝሙረ ዳዊት)

(የቤተመቅደስ ፈረሰኞች መዝሙር Templars’ Hymn)

Leave a reply