- 31Jul
ሕይወትህን ሊለውጥ የሚችል ጥበብ
ብዙውን ጊዜ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት፣ ብዙዎቻችን ለመተግበር የሚከብደን አንድ ምግባር አለን፥ ንፅህና፣ ቸርነት፣ እምነት፣ ትዕግስት፣ ደግነት፣ ተስፋ፣ ምህረት ወይም ትህትና ሊሆን ይችላል። ደስ የሚለው ግን በተቃራኒው ብዙዎቻችን ከሌሎች ምግባሮች ይበልጥ በቀላሉ የምንለማመድበት አንድ ምግባር አለን። በተፈጥሮ፣ በአስተዳደግ፣ በባህርይና በጸጋ ጥምረት ምክንያት፣ ሳይከብደን የምንፈጽመው ምግባር አለን። የተጠቀሰውን መልካም ምግባር የተሻለ ለማድረግ ምን ያስፈልጋል? ያለህን ጥሩ ምግባር ማሻሻል አላስፈላጊ ነገር ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ጥንካሬህን ወደ ኦሊምፒክ ደረጃ ከፍ ማድረግ ከቻልክ፣ ወደ ውጭ ይንፀባርቃልና በሌሎች ምግባሮች ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል። ለምሳሌ፣ በደግነት ጎበዝ ከሆንክ ንጽሕና ቀላል ይሆንልሃል። በንጽሕና ጎበዝ ከሆንክ ደግነት ቀላል ይሆንልሃል። እኛ ሁላችንም ማበረታታት የሚገባን አንድ ልዩ ምግባር አለን የሚል እምነት አለኝ። ጥንካሬህን ለማወቅ ሞክር። ይህ መንፈሳዊ ጤንነትን የሚሰጥ ልምምድ ነው። የዚያ ምግባር ልምምድህ በጣም ጥሩ እንደሚያደርግህ ማሰብ ራሱ መልካም…