ችግሮችን ማስወገድ ወይስ ህፃናትን ማጥፋት? የ2030 አጄንዳ እና የህይወት መብት

ችግሮችን ማስወገድ ወይስ ህፃናትን ማጥፋት? የ2030 አጄንዳ እና የህይወት መብት

ህይወትን በተመለከተ፣ በተባበሩት መንግስታት ላይ ጥርጣሬ ውስጥ የምንወድቀው እኛ ብቻ አይደለንም። በ 1994 GC ካይሮ ውስጥ በተካሄደው የሕዝብና ልማት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ጀምሮ (International Conference on Population and Development)፣ የabortion ተሟጋቾች በተባበሩት መንግስታት ሰነዶች ቋንቋ በመጠቀም አጀንዳቸውን ማራመድ ከጀመሩ ቆይተዋል።

ብዙን ጊዜ በተባበሩት መንግስታት ሰነዶች ውስጥ በሚገኘው “የወሲብና የስነ ተዋልዶ መብቶችና ጤና አገልግሎት” (“sexual and reproductive rights” and “sexual and reproductive health care services”) በሚል ሀረግ ትርጉም ላይ እስካሁን ያልተቋረጠ ትግል ተካሄዶአል። የabortion ተሟጋቾች የወሲብና የስነ ተዋልዶ መብቶች የውርጃን መብት እንደሚያካትቱ ያምናሉ።

የተባበሩት መንግስታት በ2015 GC በጻፉት የዘላቂ እድገት አላማዎች አጄንዳ ዙርያ (Agenda 2030) ይህ ፊልሚያ አሁንም እንደገና ተፋፍሟል.። እንዲያውም በአጄንዳ ቁትር 3.7 እና 5.6 ውስጥ ከላይ የጠቀስኩትን ቋንቋ እናገኛለን።

ምንም እንኳን abortion የሚል ቃል በሰነዱ ውስጥ ባይኖርም፣ አጄንዳን 2030 የሚያዳብሩ ታዳጊ ሀገሮች ውርጃን ሕጋዊ እንዲያደርጉ ተጽዕኖ ይደረግባቸዋል። በእርግጥም ውርጃን ካልተቀበሉ ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ይቀነስባቸዋል።

የአፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት በጥሩ ሁኔታ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፥ “It can no longer be denied that under the euphemism of “sexual and reproductive health and rights,” such programs are plainly imposed as a condition for development assistance…  (ውርጃን ካልተቀበላችሁ አለም አቀፍ እርዳታ እንቀንሳለን) The agents of the civilization of death (የሞት ባሀል አናፂዎች) are using ambivalent language, seducing decision-makers and entire populations, in order to make them partners in the pursuit of their ideological objectives… We, African pastors, note today with profound sadness that the post-2015 agenda for global development, in its present state of elaboration, continues in this direction… (አጄንዳ 2030 በዚህ አቅጣጫ ይቀጥላል) and that the partnerships that have been established have become a powerful political and financial force”.

William Sanders በNational Catholic Bioethics Quarterly እንዳስቀመጠው፥ የሕይወት ደጋፊ ሀገራት ግልጽ ባልሆነ ቋንቋ (አሕዛብን በማያሻማ ቋንቋ) ይዋጋሉ።

አጄንዳ 2030 ለ15 አመታት በምድር ላይ ለሚገኙ በእያንዳንዱ ሕዝብ ተፈጻሚ ስለሚሆን፣ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አደጋ ላይ ይወድቃሉ።

Leave a reply