- 13May
በኢራቅና በሶርያ የተሰቀሉ ክርስቲያኖች… ሴቶቻቸው ከተደፈሩና ልጆቻቸው ከተገደሉ በኋላ፣ ተሰቃይተው ሞቱ። የተደፈሩት፣ የተጨፈጨፋትና ተሰልበው ወይም አይናቸው ተነቅሎ የተረፉት ሳይቆጠሩ፣ በ2010 ብቻ የተገደሉ የክርስቲያኖች ቁጥር ከ 3000 እስከ 4300 ይደርሳል። በ2010 በባህር ውስጥ የሞቱ ሰዎች 2000 ናቸው። ስለዚህ በዐብይ ጾም ሰብከትና በፍኖተመስቀል ጊዜ፣ በመጀመሪያ የሞቱትን ክርስቲያኖች ማስታወስ ይገባናል፣ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ መናገር ይቻላል። ስለ ክርስቲያን ሰማዕታት ለምን አይነሳም?