የቤኔዲክት መድሃኒት፥ ወደ እግዚአብሔር መመለስና ቅዱስ ቁርባንን መከላከል

የቤኔዲክት መድሃኒት፥ ወደ እግዚአብሔር መመለስና ቅዱስ ቁርባንን መከላከል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት ፲፮ በቅርብ ጊዜ ከጻፉት ማስታወሻዎች አጫጭር ትርጓሜን አቀርብላችኋለሁ። እዚህ ላይ የርሳቸው ፅሑፍ ሙሉ በሙሉ ማንበብ ትችላላችሁ (here)። ቤኔዲክት ፲፮ በተለያዩ የአሜሪካና የጀርመን ገዳማት ውስጥ የግብረሰዶማውያን ክለቦች የሚሰሩ እንደነበረና ቤት ውስጥ ተጽዕኖ ያደርጉ እንደነበረ ይገልፃሉ።

 

“ምን መደረግ አለበት? ለዚህ መፍትሔ ሌላ ቤተክርስቲያን መፍጠር አለብን ወይ? በሰው ልጅ ታሪክ እንዲህ አይነት ሙከራ አስቀድሞ ተካሄዶ ነበረ፣ ግን ስኬታማ አልሆነም። ይልቁንስ መንገዱን ሊያሳየን የሚችል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማፍቀርና ለርሱ ብቻ መታዘዝ ነው…”

“በዘመናችን ባለው የሥነምግባር ውድቀት ላይ ዋነኛው ተግባራችን ለእርሱ ብቻ በመኖር ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን የሕይወታችን መሰረት ለማድረግ እንደገና መማር ነው። እኛ ግን በተደጋጋሚ ጊዜ ፍሬ እንደሌለው ቃል አድርገነው እግዚአብሔርን ጥለን እንሄዳለን።

ስልክርስቶስ ስናጠና ክርስቶስ ራሱ የአስተሳሰባችን፣ የቃላታችንና የድርጊቶቻችን ምንጭ ካልሆነ፣ በስተጀርባውን የምንተው ጥላ ይሆናል…”

“ስለዚህ ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ስናስብ፣ በራሳችን የታቀደ ሌላ ቤተክርስቲያን እንደማያስፈልግ ግልጽ ነው። ይልቁንስ ከሁሉ በላይ የሚያስፈልገው በቅዱስ ኩርባን ምስጥር በሚሰጠን በእየሱስ ክርስቶስ ያለን እምነት ማሳደስ ነው…”

“ቤተክርስቲያን በሰው ነፍስ ዘንድ እየሞተች ነው። በእርግጥም ዛሬ ቤተክርስቲያን እንደ አንድ ፖለቲካዊ ተቋም ተደርጋ ትቆጠራለች። ብዙ ጳጳሳት እንኳን ስለ ቤተክርስቲያን ያላቸው አመለካከት ፖለቲካዊ አመለካከት ነው። የዛሬው ውድቀት ቤተክርስቲያናችንን አፍርሰን በራሳችን እቅድ እንድንቀርፀው ይገፋናል፣ ነገር ግን በሰው እጅ የተቀረፀ ቤተክርስቲያን ተስፋ ሊሰጥ አይችልም…”

“ዛሬም ቢሆን ቤተክርስቲያን የተገነባችው በመጥፎ ዓሣና በእንክርዳድ ላይ ብቻ አይደለም፥ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ዛሬም ሕያው ናትና ዛሬም በእውነት እግዚአብሔር በርሷ አማካይነት ሊያድነን ይፈልጋል።

የዲያብሎስን እውነት የሚመስለውን በመቃወም እውነትን ሙሉ በሙሉ በድፍረት ማስተማር በጣም አስፈላጊ ነው፥ በእርግጥ በቤተክርስቲያን ውስጥ ክፉና ኃጢአት አለ። ነገር ግን ዛሬም ቢሆን መፍረስ የማትችል ቅደስቲቷ ቤተክርስቲያን ትኖራለች። ዛሬም እውነተኛና አፍቃሪ አምላክ የሚገለፅባቸው በትህትና የሚያምኑ፣ መከራን የሚቀበሉና በፍቅር የሚኖሩ ብዙ ሰዎች አሉ። ዛሬም እግዚአብሔር በዓለም ላይ የራሱ ምስክሮች (ሰማዕታት Martyres) አሉት። እነርሱን ለማየትና ለመስማት ከፈለግን ሁልጊዜ ንቁ መሆን ይጠበቅብናል…”

 

እስከዚህ አንዳንድ የቤኔዲክት ፲፮ ማስታወሻዎችን አቅርቤላችኋለሁ። የሚቀጥሉትን የካርዲናል ሮበርት ሳራህ (Robert Sarah) ቃላት ከቤኔዲክት ፲፮ ፅሑፍ ጋር ልታነፃፅሩ ትችላላችሁ። የጊኒ ኮናክሪ ተወላጅ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ በቫቲካን ውስጥ በከፍተኛ ቦታ ላይ የሚገኙት ናቸው።

ካርድ ሳራህ፥ “በብሉይ ኪዳን ጊዜ ከበጎቻቸው ጠጕርና ስጋ ትርፍ ማግኘት የሚወዱ ብዙ መጥፎ እረኞች ነበሩ። በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሌም ክህደት ኖሯል። ያለ ፍርሃት መናገር እችላለሁ፥ ዛሬ አንዳንድ ካህናትና እንዲያውም አንዳንድ ጳጳሳትና ካርዲናሎች እግዚአብሔር የሚያስተምረውን ለመናገርና የቤተክርስቲያንን መሠረታዊ ትምህርት ለማስተላለፍ ይፈራሉ። ስለዚህ ከማንኛውም ክርክር ለማምለጥ፣ ግራ የሚያጋቡትና ግልጽ ያልሆኑትን ነገሮች በመናገር በዓለም ውስጥ ያለውን የማይነቃነቅ አስተሳሰብ ይቀበላሉ። ይህ ክህደት ነው፥ እረኛ መንጋውን በዕረፍት ውኃ ዘንድ ካልመራ፣ በለመለመ መስክ ካላሳደረና ከአውሬ ካልጠብቀው፣ ገዳይ እረኛ ነው። እምነትና ጸሎትን ካላስተማረ ተልዕኮውን አይፈፅምም። ‘እረኛውን እመታለሁ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’ (ማቴዎስ 26፥31)፥ ዛሬ የሚፈጸመው ያለ ይህ ነው። አማኞች የት መዞር እንዳለባቸው ግራ ተጋብተዋል”

Leave a reply